ዝክረ አድዋ ቁጥር ሶስት የብእር አይኖች
ዝክረ አድዋ ቁጥር ሶስት የብእር አይኖች (ዘላለም በላይነህ) የካቲት ወር የጥቁር ህዝቦች ወር ለዘመናት በባርነት ተጨቁነው የኖሩት የአፍሪካ ወር ይባላል፡፡ ይህን ወር ወር እንዲህ ለመባል ያበቃው ብቸኛ እና ዋናዉ ቁም ነገር በእኛ በኢትዮጵያውያን በአፄ ሚኒሊክ የራስ ቅልነት በተመራው የዓድዋ ድል ነው፡፡ ነጮች አፍሪካውያንን በግፍ በሚረግጡበት፣ በባርነት በሚገዙበት፣ ያሻቸውን ያለከልካይ በሚፈፅሙበት በዚያን ወቅት " እምቢኝ ! ሀገሬን በቅኝ አላስገዛም " ብሎ በጀግንነት የተነሳ፣ተነስቶም የቅኝ ገዢዎችን በትር በሀይል መስበር የተቻለበት ያልተደረገውን ያደረግንበት ኢትዮጵያውያን አይነኬና አይደፈሬነታቸውን ያሳዩበት ወር ይህ የካቲትወር ነው፡፡ እንደሌሎቹ የአውሮፓ ሀገራት አፍሪካን ለመቀራመት በዚህ ዘመን ኢጣሊያም ኢትዮጲያን በቅኝ ግዛቷ ለማድረግ መንገድ ለማመቻቸት አዲስ እቅድ አቅዳ የውጫሌ ውል ከአፄ ምኒልክ ጋር ውጫሌ ከተማ ላይ በተወካይዋ አንቶሌኒ መሰረት ተዋዋለች፡፡ ኢጣልያኖች አላማቸውን ለማሳካት ስጋ ያየ አንበሳ መስለው እያሰፈሰፉ ቢመጡም የቆያቸው ግን የተቆጣ የአንበሳ መንጋ ነበር፡፡ ከተደረገው ውል አንቀፅ 17 ግን የአማርኛ እና የኢጣልያንኛ ትርጓሜው የተለያየ ነው፡፡ በአማርኛ የተፃፈው ‹‹ ግርማዊ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ መንግስታ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም ለመነጋገር ሲፈልጉ በግርማዊ የኢጣ...