አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ ( አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ ! ( ዘላለም በላይነህ ) አማርኛ እና አገውኛ ሁለቱም የአንድ ህዝብ አንድ ደም ያለው ህዝቦች ባለቤት ነው አማርኛ ቋንቋ አገውኛን አያጠፋውም አገውኛም አማርኛን አያጠፋውም በተለያዩ ዘመናት በዘአገው ስሮ መንግስት ስንመለከት አማርኛ ጎልብቶ የታየባቸውን ዘመናት መመልከት እንችላለን አገው አማርኛን የራሴ ንብረት በራሴ የተሰራ ታሪኬን መዝግቤ የምይዝበት ቋንቋ ነው ብሎ ያስባል ፡፡ ይሄ ባይሆን ኖሮ ከሶስት መቶ አመት በላይ የአገው ስርዎ መንግስት ኢትዮጵያን ባሰተዳደረበት ሰአት አማርኛን እንደ ዋና ቋንቋው አድርጎ ባልተጠቀመ ነበር ፡፡ ፡፡ ምንም እንኳን የቋንቋ ምሁራን አማርኛን ሴማዊ ብሎ ቢመድቡትም ህዝቡ ግን የደም ትስስሩ አንድ ሀረግ ያለው ህዝብ ነው የሁለቱም ቋንቋ ፈጣሪም እራሱ ህዝቡ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ የኩሽ ምድር ነች ሆኖም የግዕዝም ሆነ የአማርኛም ሆነ የአገወኛ ፈጣሪ ይሄ አንድ ህዝብ ነው በቤተክርስቲያን ዋና ቋንቋነት የሚጠቀመው ግእዝን ስለሆነ አማርኛ እና ግእዝ ደግሞ በእጅጉ የተቀራረቡና ብዙ የቃላት ወህደት ያላቸው ናቸው ከዚህ አንጻር አማርኛ ከአገውኛ በገነነ መልኩ ገኖ መውጣት ችሏል ፡፡ አገውኛም ሆነ አማርኛ ፈጣሪዎቹ አንድ ህዝብ ነው ያልሁበት ምክንያት ፡፡ ለምሳሌ አገውኛ ልክ እንደ አማርኛ የግዕዝን ፊደል የሚጠቀም ሆኖ ሳለ አማርኛ የሚጠቀምባቸውን በሙ...