አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ
(አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
(አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
(ዘላለም በላይነህ)
አማርኛ እና አገውኛ ሁለቱም የአንድ ህዝብ አንድ ደም ያለው ህዝቦች ባለቤት ነው አማርኛ ቋንቋ አገውኛን አያጠፋውም አገውኛም አማርኛን አያጠፋውም በተለያዩ ዘመናት በዘአገው ስሮ መንግስት ስንመለከት አማርኛ ጎልብቶ የታየባቸውን ዘመናት መመልከት እንችላለን አገው አማርኛን የራሴ ንብረት በራሴ የተሰራ ታሪኬን መዝግቤ የምይዝበት ቋንቋ ነው ብሎ ያስባል ፡፡ ይሄ ባይሆን ኖሮ ከሶስት መቶ አመት በላይ የአገው ስርዎ መንግስት ኢትዮጵያን ባሰተዳደረበት ሰአት አማርኛን እንደ ዋና ቋንቋው አድርጎ ባልተጠቀመ ነበር ፡፡ ፡፡ ምንም እንኳን የቋንቋ ምሁራን አማርኛን ሴማዊ ብሎ ቢመድቡትም ህዝቡ ግን የደም ትስስሩ አንድ ሀረግ ያለው ህዝብ ነው የሁለቱም ቋንቋ ፈጣሪም እራሱ ህዝቡ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ የኩሽ ምድር ነች ሆኖም የግዕዝም ሆነ የአማርኛም ሆነ የአገወኛ ፈጣሪ ይሄ አንድ ህዝብ ነው በቤተክርስቲያን ዋና ቋንቋነት የሚጠቀመው ግእዝን ስለሆነ አማርኛ እና ግእዝ ደግሞ በእጅጉ የተቀራረቡና ብዙ የቃላት ወህደት ያላቸው ናቸው ከዚህ አንጻር አማርኛ ከአገውኛ በገነነ መልኩ ገኖ መውጣት ችሏል ፡፡ አገውኛም ሆነ አማርኛ ፈጣሪዎቹ አንድ ህዝብ ነው ያልሁበት ምክንያት ፡፡ ለምሳሌ አገውኛ ልክ እንደ አማርኛ የግዕዝን ፊደል የሚጠቀም ሆኖ ሳለ አማርኛ የሚጠቀምባቸውን በሙሉ አገውኛ ቢጠቀምም እንኳን ከዚያ በዘለለ የራሱ የሆኑ ፊደላትን የያዘ ነው ለምሳሌ ያህል እኒህን መጥቀስ እንችላለን አናቶሚካሊ እነዚህ ፊደሎች ከግእዝ ጋር አንድ ናቸው ቕ፤ ጝ፤ ⶓ'
ለምሳሌ ታሪኮቻችንን ላይ ሰፍረው የምናገኛቸው ቋንቋዎች ትርጉማቸው ሳብዕያዊኝ አገውኛ ግእዝ እና አማርኛ ትርጉምና ይዘት ላቸው ናቸው፡፡ እንደምሳሌ አክሱምን መጥቀስ እንችላን (አኹ -ሱም ) የመጀመርያው ቃል በአገወኛ ሲሆን የሚቀጥለው ደግሞ ሳብዕያዊንን በመጠቀም ነው ) ትርጉሙሙ የውኃ ሹም የሚለውን ትርጉም እንደሚሰጥ ታሪክ ይናገራል፡፡ የአገወኛ እና የአማርኛ ቋንቋ ባለቤት አንድ ህዝብ መሆኑን ለመረዳት የኪነ ህንጻ ጥበቦቻችን የአገውኛ እና የአማርኛ ቋንቋ ሽብልቆች መሆናቸውን ማጤኑ በራሱ አንድ ማጠናቀሪያ ሀሳብ ነው፡፡ እሴቶቻችንን ቆፍረን ማውጣት እንችላለን። የኢትዮጵያን ታሪክ በትክክል ቆፍሮ ላማውጣትና ለማወቅ ግዕዝ አማርኛ እና አገውኛን መናገር መሰረታዊ እና ወነኛ ነገር ነው ፡፡ አንዳንዴ አማራ እና አገው የተላያየ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ጋር አልስማማም ይሄ አገው አማርኛን ያለመጠቀም ችግር የራሱ የሆነውን ንብረት እንደመተው ነው አማርኛ ተናጋሪውም አገውኛን አለመናገር እና አለመቻል የራሱን ማንነት መሸሽ ነው ፡፡ ስለዚህ ይሄ ህዝብ አንድ ህዝብ ግን ሶስት ቋንቋ ፈጣሪ የሆነ ባለምጡቅ አእምሮ ህዝብ ነው በሚለው እስማማለሁ፡፡ አማራ ነኝ እኔ አገው አይደለሁም ወይም አገው ነኝ እኔ አማራ አይደለሁም የሚለው ወሬ የተፈጠረው በእኛ የጠለቀ የታሪክ እውቀት በሌለን ሰዎች የመጣ ነው ባይ ነኝ ፡፡ በእርግጥም ብዙ አማረኛ ተናጋሪዎች በቅድም አያተቻቸው አገውኛን በበለጠ ይጠቀሙ የነበሩ መሆናቸው ግልጽ ነው ለምሌ በላስታ አካባቢ የሚገኙ ህዝቦች በሙሉ ማለት ይቻላል ቅድመ አያቶቻቸው አገውኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነበሩ ሆኖም ግን አሁን ልጆች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ አይችሉም፡፡
ስለዚህ ይሄ ህዝብ መሰረቱ ኩሽ የሆነ የሶስት ቋንቋ ባለቤት ህዝብ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰለሞናዊ ስሮ መንግስት ነን ብለው የተነሱት ነገስታቶቻችን በሀገሪቱ የስራ ቋንቋነት ይጠቀሙበት የነበረው በአማረኛ ከመሆኑ የተነሳ ፡፡ አገውኛው እየተጨፈለቀ እና የቀድሞ ይዘቱን እያጣ መጥቷል ፡፡ ስለዚህ እኔ አሁንም ለበለጠ መረጃ ዶክተር አለማየሁ ሲሳይ መጽሐፍቶችን ማንበብ ብዙ ስለዚህ ህዝብ ሊያስጨብጠን ይችላል፡፡
ስለዚህ ከላይ እንደጠቀስሁት ይሄ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤት ከሆነ እኒህ ቋንቋዎችን በአንዱ አካባቢ አንዱን በአንዱ አካባቢ ደግሞ አንደኛውን ቋንቋ አብልጦ በአንዳንዱ ቦታ ደግሞ ሁለቱንም አጣምሮ የመጠቀም ሁኔታ ከጊዜ ብዛት ትውልድ እየሰፋ በመሄዱ ተፈጠረ ማለት ነው፡፡
ኁለጸኛ ፡-ግዕዝን ሁለቱንም የሚናገሩ (አገውኛንም ሆነ አማርኛን )ሰዎች በእምነት ተቋማት የሚናገሩት ቋንቋ መሆኑ በራሱ የዚህ ህዝብን አንድ ቤተሰብ መሆንና የዚህ ቋንቋ ባለንብረት መሆኑን ይገልጻል፡፡
ብዙ ጊዜ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ አገውን ከሌላ ፕላኔት እንደመጣ አስበው እራሳቸውን ከቋንቋው ባለቤትንነት የአባቶቻቸው ቋንቋ መሆኑን አሽቀንጥረው ሲጥሉ እንመለከታለን ፡፡ ይሄ ፍጽሞ ስህተጽ ነው፡፡

ስለዚህ
እኔ ሁለቱ ህዝብ አንድ ህዝብ የሆነ ግን የሶስት ቋንቋ ባቤት ነው እላለሁ ፡፡ ለዛ ነው አገው አማራ ነው አማራ አገው ነው የምንለው፡፡ ከሰሜታዊነት በጽዳ መልኩ መወያየት እና መነጋገር የምንችል መሆኑን አሰምርበታለሁ፡፡ ለሚሳደብ እና እኔ ያልሁት ካልሆነ ለሚለው ቦታ የለኝም ፡፡
እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!
ዘላለም በላይነህ

Comments