ኢጋድ ኢትዮጵያዊውን አማካሪ ከሥራ አሰናበተ
የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ የተቋሙ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩትን ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አሰናብቷል። በኢጋድ ዋና ፀሐፊ በአምባሳደር ማሕቡብ ሙአሊም የተፈረመ ደብዳቤ ባለሥልጣኑ የኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አገልግሎት ማቋረጡን ይናገራል። ይህ ሰኞ፣ ሰኔ 18/2010 ዓ.ም. የተፃፈ ደብዳቤ ስለኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ መሰናበት ዝርዝር አላሰፈረም። ይሁን እንጂ ሥራቸውን ያስቆማቸው በዚያኑ ቀን መሆኑን አስታውቆ የአደጋን ንብረት ሁሉ ከትናንት በስተያ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል በፊት እንዲያስረክቡ አዝዟል።