#ዘመድኩን_በቀለ_እንደፃፈው
#እናም_ጉዞ_ወደ_ቴዲ_አፍሮ_ደጅ_ጥናት አማላጁ ደግሞ ብአዴን ነው ጨፋሪው ደግሞ የዐማራው ህዝብ ቴዲሻ ደግሞ ያው እንደተለመደው [ ቂም በቀል ይቅር እርስ በርሳችን እንዋደድ እንፋቀር እያለ ዐማራውን ይሰብክ ዘንድ ተመርጧል ]
ቴዲሻ መቼ ፈቃድ እንደጠየቀ ሳንሰማ ሳናውቅም ራሱ ቴዲ አፍሮ በባህርዳር ኮንሰርት እንደተፈቀደለት ይፋ አደረገ ድንገቴ ዜና ነበር ልብ አድርጉ ፈቃጁ ደግሞ #ብአዴን ነው ብአዴን ደግሞ የህወሓት ኮንዶም ነው በህወሓት ፈቃድ የሚንቀሳቀስ በድን በህወሓት ሳምባ የሚተነፍስ አሳ ወዲያው ብዙም ሳይቆይ ከደቂቃዎች ልዩነት በኋላ የብአዴኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ጉራጌው የዐማራ ባለሥልጣን አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስ ቡክ ገፁ የምሥራች ምስር ብሉ ብሎ ከቴዲሾ ጋር የሚመሳሰል መግለጫ አስተላለፈልን ህዝቤ ዜናው እንደተሰማ በደስታ ሰከረ ለማገናዘብና ግራ ቀኝ ለማየት እንኳ ጊዜ አላገኘም ጭራሽ በኮንሰርቱ ቀን ላይ የጦፈ ሙግት ተጀመረ
#ፀረ_በጋሻው_ደሳለኝ_ፀረ_ተሃድሶ የተባለ የፌስ ቡክ ፔጅ በቃና ዘገሊላ በቅዱስ ሚካኤል ቀን እንዴት ህዝብን ከእምነት ሥፍራው ለማስቀረት ወጥመድ ታጠምዳለህ ብሎም ቴዲን ሞግቶና ሰቅዞ ያዘው እነ ሀጎስም የኽቺን ሲሰሙ አብረው ተንጫጩ እነሱ እንኳን ስላልገባቸው ነው የገባቸው ሴራውን የሚያውቁ እነ ዳንኤል ብርሃነ እነ ዳዊት ከበደ ጮጋ ነው ያሉት ከዚህ በፊት ቴዲ ዝግጅት ሊያቀርብ ነው ሲባል በፌስቡክ ላይ የሚያስታውካቸው የህወሓት ልጆች በሙሉ ጭጭ ነው ያሉት ምክንያቱም ተልእኮውን ያውቁታላ ትንሽም እንኳ የተፈቀደው ሊከለከል ይችላል ያለችው ሰናይት መብራህቶም የተባለች ፌስቡከር ብቻ ናት እሷም ምስኪን ጥሬ ካድሬ ስለሆነች ነው እንጂ እስከ አሁን ከህወሓት መንደር የቴዲ አፍሮን የሙዚቃ ኮንሰርት በግልጽ የተቃወመ ታዋቂ ሰው ማንም የለም የሆኑ በትግሬ ስም የሚንበጫበጩ መንገደኞች ካልሆኑ በቀር የምናውቃቸው ሁሉ ጮጋ ብለዋል እንዲያውም ይባስ ብለው እነ ፋና ጭምር በዜና መልክ ዘግበውታል ተብሏል። የህወሓት መሥራቹ ሪፖርተርም አቶ ንጉሡን አናግሮ የኮንሰርቱን ጉዳይ ዘግቦታል ማን ቀረ ማንም
ቴዲም ይኽቺን የቃና ዘገሊላ ታሪክ ሲሰማ " ይቅርታ ቀኑን ቀይሬዋለሁ አለ ጥር 13 በባህርዳር እስታዲየም አንድም ሰው እንዳይቀርብኝ አለ ትኬቱም ጎንደር ጎጃምና አዲስ አበባ በህብረት ባንኮች ውስጥ ታገኙታላችሁ አለ
አሁን የቀረው የፊታችን እሁድ የጥምቀት ማግስት አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከዐማራ ክልል የገጠር ከተሞች ጭምር ግልብጥ ብሎ የሚመጣውን የዐማራ ነገድ ወጣት አዛውንት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ማስከር ማሳበድ ማስጨፈር መቀስቀስ ነው አፄ ቴዎድሮስ ሲነሱ ዐማራው ያብዳል አጼ ሚኒልክ ሲወሱ ዐማራው ጨርቁን ይጥላል ኢትዮጵያዊነት ሲወደስ ዐማራው አቅሉን ይስታል እነ እንትና ደግሞ ይስቃሉ ይገለፍጣሉም። [ ሞኝ ዐማራም ] ይላሉ
እንደኔ እንደኔ ወደ ኮንሰርቱ መግባቱን ግቡ እንዲያውም ካልሰረዙት ለዐማራው ነገድ ጥሩ አጋጣሚ ነው ባይ ነኝ ገብታችሁ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን ዘምሩ በአጋጣሚውም ተጠቅማችሁ ዕለቱን ጎጃም ጎንደር ወሎ ሸዋ መባባሉን ትታችሁ ልክ እንደ ኦሮሞው እንደ ትግሬው እንደሱማሌና ስልጤው ዐማራነት ላይ በደንብ አድርጋችሁ ሥሩ ዐማራነት ላይ ጩኹ ቃል ኪዳንም ግቡ እሱ ነገር ነው ሻአቢያንም ህወሓትንም ጤና የነሳቸው ዐማራው ዐማራ ነኝ ማለት መጀመሩ ጤና ንስት ነው ያደረጋቸው ዐማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲልም ዐማራ ነኝ ሲልም ያማቸዋል ሽንት ቤትም ያመላልሳቸዋል ወዳጄ ኢትዮጵያዊነታችሁን እንደሁ የሚቀማችሁ የለም ዘመኑ የሚጠይቀው ነገድህን ማዳን ነውና ዐማራነትህን አድን ውደደው አስተዋውቀው ልክ ትግሬው ትግሬ ነኝ ኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ እንደሚለው አንተም ባህርዳር ላይ ኢትዮጵያዊ ዐማራ ነኝ ብለህ ዘምር ጎጃም ጎንደር ሸዋ ወሎ ብለህ አትከፋፈል ትግሬው አዲግራት ሽሬ አደዋ አክሱም መቀሌ ነኝ ሲል ሰምተህ ካላወቅክ ኦሮሞው አርሲ ሐረር ባሌ ወለጋ ሰላሌ ጅማ ነኝ ሲል ሰምተህ ካላወቅክ አንተስ ለምን ዐማራ ነኝ ማለት ታፍራለህ ዋሸሁ እንዴ ? እበድ እንግዲህ ወዲ ሀጎስ
ቴዲዬ ታዲያ በቪአይፒ 1000 ብር ከፍሎ ከሚገባው ሰው ከሚያገኘው ብር ሌላ በቀላሉ 80 ህዝብ ላይ ከእያንዳንዱ ዐማራ ላይ 350 ብር ሂሳብ ጥሬ 28 ሚልየን ብር ወደ ኪሧ ከትታ ከባህርዳር ትመለሳለች እስፖንሰሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስለሆነ ቴዲ ብሩን መሸከምም አይጠበቅበትም።አከተመ።
~ በማግስቱ ታዲያ ከኮንሰርቱ መልስ ማለት ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስቸኳይ እና አጣዳፊ የወታደር ቅጥር ማስታወቂያ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በዐማራ ክልል ያስነግራል በቴዲ አፍሮ ዘፈን እንዲያብድ የተደረገው ዐማራ ሆዬ ዘራፍ እኔ ወንዱ እኔ የመይሳው ካሳ የአጼ ሚንልክ አሽከር ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ አተተተተተተተተተ እምቢኝ እምቡርርር እያለ በሰልፍ ለወታደርነት ይመዘገባል። ጨዌው ይኸው ነው አከተመ
#ማስተዋሻቴዲም ጨዋታው ውስጥ እንዳይኖር እኔ በበኩሌ እጸልያለሁ ከምሬ ነው እጸልያለሁ ምክንያቱም ቴዲ በፌስ ቡኩ ላይ ያለው የዐማራ ክልልን ጠይቆ እንደተፈቀደለት ሲሆን መረጃዎች ግን ቴዲ የተናገረውን አይነት ነገር አያመለክቱም እጅግ አስገራሚው ነገር ቴዲ አፍሮ ኮንሰርቱን ባህርዳር እንዲያቀርብ አዲስ አበባ ድረስ ሄደው የለመኑት እና ያግባቡት አቶ #ንጉሱ_ጥላሁንና የአቶ ገዱ ተወካይ አቶ #ምግባሩ_ከበደ መሆናቸውን ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት ከታች የፎቶ ማስረጃውን መመልከት ትችላላችሁ ህወሓት በብአዴን በኩል ቴዲ እግር ላይ ተደፍታ እንደለመነችው ነው የምቆጥረው የዚህ ዓይነት ጥያቄ በዘመነ ህወሓት ታሪክ ያልታየና በተአምርም ያልተለመደ ብቻ ሳይሆን ጥያቄም ጭምር የሚያጭር ነው
ግን ግን አሁንም ልጠይቅ
፩ኛ የኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት አቀንቃኙ የምንወደው እና የምናከብረው አዝማሪ ቴዲ አፍሮ በድንገት [ አስመራ ላይ መዝፈን እፈልጋለሁ ] ለምን አለ? ስለ ዳኽላክ መዝፈኑን ሳንዘነጋ
፪ኛ በቤቱ ውስጥ ሲበላና ሲጠጣ ሲተኛም ጭምር በህወሓት የደኅንነት የስለላ መረብ ውስጥ ወድቆ በገዛ ሀገሩ ሠርቶ እንዳይበላ ማዕቀብ የተጣለበት ቴዲ አፍሮ በድንገት የኬንያ ናይሮቢ ዝግጅቱን ሰርዞ በዐማራ ክልሏ በባህርዳር ከተማ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲያዘጋጅ ለምን ተደረገ ? እንዴትስ ተፈቀደለት ብቻ ብአዴን ልክ እንደ ኦህዴዱ አቶ ለማ መገርሳ ሆኖ ነው እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ
የቴዲን ኮንሠርት የሚቃወሙ በዐማራ ስም ተደራጅተናል የሚሉ ወገኖችም እየተሰሙ ነው እነዚህ ግለሰቦች ኩኩ ሰብስቤን ቦንብ ወርውረው ስተዋታል አረጋኸኝ ወራሽን አስቀርተውታል ኤፍሬም ታምሩ ማዲንጎ አፈወርቅንም ፕሮግራማቸውን አሰርዘውታል ቦንቡን ከየት እንደሚያገኙ ባይታወቅም ቦንብ ግን አላቸው
የጸጥታውን ጉዳይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው ነበር " ቴዲን ሁሉም ሰው ስለሚፈልገው በኮንሰርቱ ላይ ችግር አይኖርም የፀጥታ ስጋትም አይኖርብንም ሲሉ ቢደመጡም እኔ ግን ፍራቻ አለኝ ቢሾፍቱን ያየ ጨለንቆና ጎንደር ባህርዳር ላይ የረገፈውን ኢትዮጵያዊ ያየ ባይሰጋ ነው የሚገርመኝ ነገር ግን ልጁ ቴዲ ነው ብለን እንጽናናለን [ ወዳጄ ላንቃህ እስኪ ሰነጠቅ የምትጮኽላት የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅህ ] አሜን
አንድ የፌስቡክ ጦማሪ ወዳጆቼ እንዲህ ይላል [ እየሆነ ያለውን ነገር በትኩረት ዐይተን እና መርምረን ለዚህ የጦርነት ድግስ ዋና ሞተር የዐማራ ህዝብ እንዲሆን ስለተፈለገ ነው ይህ ሁሉ እሽሩሩ የሚካሄደው ብለን ብንደመድም የተሳሳትን አይመስለኝም። ከህዝቡ የጦርነት ታሪክ አኳያ፤ ከጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ እና ከሃገሪቱ የአንድነት መንፈስ አስኳልነቱ አንጻር በውጭ ያሉት እነ አሜሪካ ሆነ የሀገር ውስጦቹ ወያኔዎች የዐማራን ህዝብ ለዚህ ወጥመድ መሪ እና ዋና ተዋናይ ሊያደርጉት ቢፈልጉ የሚገርም አይሆንም...]
ንስሮች ሆይ በዙሪያችን እየተካሄደ እያለውን ነገር ቆም ብለን እንመርምረው፤ ሁሉንም በትኩረት እንከታተል፤ የአማራ ደም መፍሰስ ካለበትም ለራሱ እና ለማንነቱ እንጂ ለሃገር ውስጥ ቀኝ ገዥዎች እና ለውጭ ኢምፔሪያሊስቶች ሊሆን አይችልም ይላል #Yohannes_Amhara
በዚህ ዙሪያ አንድ ሁለቴ ብቅ ብል ደስ ይለኛል ለማንኛውም ይኼ ዐማራው ዐማራ ዐማራ እያለ መሰባሰቡ በራሱ በፍጹም አልተወደደለትም በህወሓትም በሻአቢያም በኦነግም አልተወደደም አከተመ ዐማራ ሆይ ንቃ የዕለቱ መልእክቴ ነው በተለይ የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ለዐማራ ብሔርተኝነት እንደ ሰደድ እሳት መቀጣጠል ምክንያት ነው የሆነው እናም በአገዛዙ ዘንድ የዐማራው ክለቦች በፍፁም አልተወደዱም
እነ ወዲ ጅጋኑ ውስኪና ቢራው አላስተነፍስ ብሎ ጮማው አንቆ ቁንጣኑ አንቆራጥጦ መያዣ መጨበጫ አሳጥቶ ምቾት ባንገላታቸው ሰዓት ይኼ ፈተና መምጣቱ በህወሓት ካምፕ በፍፁም አልተወደደም አስደንግጧቸዋልም ከምር አስደንግጧቸዋል እናም በኢትዮጵያ ጉዳይ ዐማራው ብቻውን የምን ዕዳ ነው ያለበት የህወሓት ሰዎች የጦር አዛዥ ሆነው በሚመሩት ጦር ውስጥ ዐማራው ፈንጅ አምካኝ ለምን ይሆናል አረ ሼም ነው እንዲያውም ሰሞኑን የኦሮሞና የዐማራ ጀኔራሎች ሊሾሙ ነው አሉ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ያለው ማን ነበር በእናታችሁ
ከዚህ ይልቅ በአስቸኳይ የብሔራዊ ዕርቅ ጉባኤ በኢትዮጵያችን ይጠራ ሁሉን አቀፍ ውይይት ይካሄድ እርቅ ይፈጸም ከዚያም ጎን ለጎን በአስቸኳይ የዐማራ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ! የኦሮሞም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ! በሔር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ! ቅድሚያ የውስጥ ችግር ይፈታ ከዚያ ሌላው ቀላል ነው እንደ አመጣጡ ይመለሳል ይኸው ነው
እንዲያው ለነገሩ የሆነስ ሆነና ቴዲሻ በባህርዳሩ ኮንሰርት ላይ #17_መርፌ_በጠቀመው_ቁምጣ
#ለለውጥ_ያጎፈረው_ስልጣን_ላይ_ሲወጣ
#እንዳምናው_ባለ_ቀን_ይኼኛው_ሲመጣ
#አዲስ_ንጉሥ_እንጂ_ለውጥ_መቼ_መጣ
እያለ ያስተሰርያልን ይዘፍን ይሆን? እንዲህ ብሎስ ብሎስ ያንጎራጉር ይሆን.? ወይስ አስመርጠውታል ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ መቐለ ባህርዳር ኦሮሞ ሱማሌ አፋር ጋምቤላ ምናምን ብሎ የኢትዮጵያን ከተሞች እየጠራ ይመለስ ይሆን
ቴዲ በባህርዳር ኮንሰርቱ ያስተሰርያልን ካልዘፈነ ጥርጣሬያችን ሀቅ ነው ማለት ነው አከተመ
ፅሁፉን ለኔ የተመቼኝን ቆርጨ ስላመጣትሁ ሙሉውን ማንበብ ከፈለጋችሁ
https://www.facebook.com/ZemedkunBekeleB/ ገብታችሁ አንቡት


Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!