"ተ ዋ ከ በ ና ... "

"ተ ዋ ከ በ ና ... "



የሀገራችን ሥልጣኔ ሲነሳ ወደ አእምሯችን ቀድመው የሚመጡት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ናቸው። ምን አልባት ምኒልክ የመሰልጠንን መንፈስ ከልጅነት አባታቸው አፄ ቴዎድሮስ ወርሰዋል።
...
ሥልጣኔ ማለት ለሰው ልጅ መልካም ሕይዎት መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችሉ ቁስ አካላዊና ሕሊናዊ ጉዳዮችን ማሟላት ነው። ይህ ማለት በቁሳዊ መልኩ ሲታይ የራቀውን ማቅረብ፣ የከበደውን ማቅለል፣ የተራራቁትን ማቀራረብ፣ ጨለማውን ብርሃን ማድረግ፣ ሙቀቱን ማቀዝቀዝ፣ ቀዝቃዛውን ማሞቅ፣ አድካሚውን ማቃለል፣ ጥቂቱን ማብዛት፣ የጠበበውን ማስፋት፣ ተፈጥሮን መግራት እና ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ ጥቅም ማዋልን ሁሉ ያካትታል። በሕሊናዊ መልኩም... ክፋትን በደግነት፣ ጠላትነትን በወንድማማችነት፣ ቂምን በይቅርታ የመተካት... ሂደት ነው። 
...
እንግዲህ "የሥልጣኔን መንገድ እየጠረግን ነው" የሚሉትን ሁሉ ከዚህ አንፃር መመዘን ይገባል። በቁስ አካላዊም ሆነ በሕሊናዊ ሚዛን ሲሰፈሩ... እየሄዱበት ያለው መንገድ ከዚህ በተቃራኒው ከሆነ እነዚህ ለሰው ልጆች ሰቆቃን እንጅ የተሻለ ዓለምን ያመጡ ዘንድ አይቻላቸውም።
...
እንደምን ሰነበታችሁ ክቡራትና ክቡራን!
እኔ ቅድስት ሥላሴ ይክበሩ ይመስገኑ ደህና ነኝ።
ከሥላሴ ጋር በተያያዘ... ዛሬ የደብረ ብርሃን ሥላሴ ንግሥ በዓል በድምቀት ተከብሯል። በሰሜን ሸዋዋ መዲና በደብረ ብርሃን ከተማ ሕዝቡ ጎዳናዎችና አደባባዮችን ሞልቶ ቅድስት ሥላሴን አንግሷል።
የደብረ ብርሃን ሥላሴ ታቦት ከሰሜን ሸዋዋ ደብረ ብርሃን በተጨማሪ በሰሜነኛዋ የአማራ የቅርስ ማኅደርና የኢትዮጵያ መናገሻ ጎንደር ይገኛል። የጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ስሙን የወሰደው ከሰሜን ሸዋው ነው። ለስሙም በወቅቱ በቂ ካሳን ከፍሏል። (የያኔው ሥልጡን ሥርዓት ለሚወስደው ስም ለባለቤትነት መብት ካሳ ይከፍል ነበር።)
ካሳ......
የልጅ ካሳ ኃይሉ (አፄ ቴዎድሮስ) 200ኛ ዓመት የልደት በዓል ትናንት በጎንደር ተከብሯል። የታሪካዊው ንጉሥ ልደት በታሪካዊቷ ጎንደር ታሪካዊ ሆኖ ተከብሯል። ወጣቶች ለንጉሣቸው ክብር አስፓልት አጥበዋል። ያያኔውን የመይሳውን ንጉሣዊ ስሜት በሕሊና የሚከስት ትእይንት ኣሳይተዋል። ጎንደሮች በቴዎድሮስ መንፈስ ተነሳስተዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከፍ አድርገው አማራነትን እየዘመሩ ነው። የጎንደሩን ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ ቴዎድሮስን "የአማራ ንጉሥ ናቸው" ይላቸዋል አዲሱ "ግዮናዊነት" የሚል መጽሐፍ። በወቅቱ የተከፋፈለውን የአማራን ኃይል በማሰባሰብ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ... አልፎም ኢየሩሳሌምን ነፃ ለማውጣት ርእይ የነበራቸው ንጉሥ... በአማራ ታሪክ ልዩ ቦታ አላቸው ሲልም ያትታል።
.
ንጉሥ ቴዎድሮሥ ታላቋንና ሥልጡኗን ኢትዮጵያን በአእምሯቸው ሥለው ወዲያ ወዲህ እንደተዋከቡ በሀገር ውስጥም በውጭም ኃይል በተደረገባቸው ክህደትና ዘመቻ ይህችን ዓለም በራሳቸው ተሰናብተዋል።
...
"ተዋከበና..."
በጥር 13ኛው ቀን በግዮናዊቷ ከተማ ባሕር ዳር ከሚሰሙ ሙዚቃዎች አንዱ...
ተወከበና...
ወዲህ ዞር ቢል
ወዲያ ዞር ቢል
ሰው የለምና...!
...የአንድ ሰው ብርቱ መንፈስ ብቻውን ሀገር አይገነባም። ከፊትም ከኋላም ከግራ ቀኝ ጎንም ሰው ያስፈልጋል። የልብ ሰው። ከፍታን ማየት የሚችል... ሰው! ነገን አርቆ የሚያይ ተራማጅ ሰው! ራእይን የሚጋራና ለተግባር የሚሰለፍ፣ ሀገርን ሕይወትን እስከመገበር የሚታመንላትና ጊዜ አይቶ የማይከዳት ሰው...!!!
መይሳውማ ሰው ነበር። ጥቂት ሰዎችም ነበሩት(እነ ገብርዬ)፡፡ ችግሩ ሁሉም ሰው ሰው አልሆንለት አለና ህልሙ ባጭር ተቀጨ። ትቂት ሰዎቹ(እነ ገብርዬ) ረጅሙን ጉዞውን ያሳኩለት ዘንድ አልቻሉም። ምክንያቱም ለረጅምና ብርቱ መንገድ ብዙ ሰው የሚያስፈልገው። ራእይን ተቀባብሎ ለትውልድ የሚያሻግር እልፍ አእላፍ ሰው......!!!!
...
(ቴዲን በባሕር ዳር ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር›› የሚል የሙዚቃ ድግስ እንዲያቀርብ የጠየቁት/የለመኑት የአማራ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና የአቶ ገዱ ተወካይ አቶ አቶ ምግባሩ ከበደ ናቸው የሚለውን በፎቶ የተደገፈ መረጃ ግን እንዴት አያችሁት? እውን ብአዴን የአማራ ብሄርተኝነትን ለማለዘብ ቴዲን ሊጠቀምበት ወይስ ቴዲ ስለሚወደድ ሕዝቡን ለማስደሰት?)


source :-melaku alamirew

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!