የጥምቀት በዓል እና ሎሚ ውርውሮ ምን ያገናኛቸዋል???
የጥምቀት በዓል እና ሎሚ ውርውሮ ምን ያገናኛቸዋል???
በዓላችን ጌታ በነብዩ ኢሳይያስ እንደ ወቀሳቸው የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ ፣ የክፉዎች ዘር ፣ ርኵሰት የምታደረጉ ልጆች ሆይ ፣ ወዮላችሁ! እያለ ይወቅሳል ። ምክንያቱም እግዚአብሔርን ትተዋል እስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኃላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል ። ደግሞስ ዓመፃ እየጨመራችሁ ለምን ገና ትቀሰፋላችሁ? ይላቸዋል (ኢሳ 1፥ 1-5)።
የጥምቀት በዓል የተመሰረተበት ዋና ምክንያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ስለመጣ (ማቴ 3 :13) የጌታ የኢየሱስ ስም የተፃፈበትን ታቦት በጌታ ምሳሌ ይዞ ወደ ተከተረው ውኃ መሄድና ማዘከር ፣ በደስታ እየዘመሩ ታቦቱን አክብሮ የመጠመቀኑ በዓል ማሰብ ፣ በነጋታውም በተባረከው ውኃ ተረጭቶ የበዓሉን በረከት መሳተፍና ለበዓሉ በተቀጋጀው መዝሙር ሲዘምሩና አምላክን ሲወድሱ መዋል ነበር ።
በዚህም ብዙ የውጪ ሀገራት ዜጎች መንፈሳውያን ባህል ለማየት ይመጣሉ ይቀርፃሉ ፣ አገራቸው ሄደው ያስተዋውቃሉ ፣ በመንፈሳዊ ነገር ተማርከው ስማችንን በዓለም ያስጠራሉ።
በዚህ መንፈሳዊ አሰራር የተበሳጨው ሰይጣን ደግሞ በተቃራኒው በአገራችን መጥፎ መጥፎ ባሕሎችን ወደ መንፈሳዊው በዓላችን በማስጠጋጋት የሃይማኖታችንን በጎ ትውፊት ለማጠልሸት ሲሠራ ይታያል ።
ብዙዎች በቀደመው በደላቸው ንስሐ ገብተው እንደማስወገድ ፈንታ ፣ በተቀደሰው በዓላችን ቀን ሎሚ የመወርወርና የዘፈን ስርዓታቸውን ማጠጋጋታቸው በእውነት ያበሽቃል ፣ ያሳዝናልም።
በበዓሉ ቀን የተዘጋጁ መምህራን የሚሰብኩት ስብከት ፦ የመጥምቁ ዮሐንስን "ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ"
የሚለውን ነው (ማቴ 3:8) ዘማውየን ደግሞ ሎሚ መወርወር
በሚል በሰይጣን ትምህርት ተስበው ፣ የዝሙት ዓይናቸውን ሲወረውሩ ይውላሉ ።
በዕለቱ የሚተላለፈው ቃል ፦ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል የሚለው ነው (ማቴ 3፥ 10)።
ኃጢአተኞች ደግሞ ሎሚ ለውርወር እያሉ ከቤታቸው ወጥተው፤
በአርሞሪካ ማሣሪያ ወሲብ እየቀሰቀሱ በማይጠፋ እሳት ለማቃጠል ይዘጋጃሉ (ሉቃስ 3 ፥17) ለበዓሉ የተመረጠው የወንጌል ቃል የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ
እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸ ሰው ድምፅ ፣ ዐዝቀቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል ፣ ጠማማውም የቀና ይሁን፣ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን ፣ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተፃፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወደላችው አገር ሁሉ መጣ የሚለው ነበር (ሉቃስ 3 : 3-6)።
ዳግም የተወለዱና ልጅነታቸውን ያፀኑ ወጣቶች በማህበር የሚሰበክ ቲሸርት ለብሰው በመዝሙርና የታቦቱን መንገድ ምንጣፍ በማንጠፍ ሳር በመጎዝጎዝ እያከበሩ በረከት እያገኙ እንደገና ለንስሃ የሚሆን ፍሬ ለማፍራት ተግሳጽ ሊሰሙ ተገኝተዋል ሎሚ ለወርወር ባዮቹ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ምን አመለከታችሁ?
ሊባሉ የመጡ ሳይሆኑ ፤ በአይን አምሮታቸው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቁጣ በራሳቸውን ለማምጣት ወደ በዓሉ የተሰበሰቡ ናቸው (ሉቃስ 3:7)
ጌታ በዓላትን ስለማክበር ተቃውሞ የለውም ። እንደውም ሕዝቦቹን ከባርነት ያወጣው በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ ብሎ ነው (ዘፀ 5:1)።
በኋላም በቃሉ ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ ብሎ አዝዟል (ዘኁ 29:12)።
ስለሆነም በመፃሕፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር በዓል በያዓመቱ አለ (መሳፍ 21:19)።
ጌታ ኢየሱስ ፣ እናቱ ከድንግል ማርያም እና አሳዳጊው ዮሴፍ በያዓመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር (ሉቃስ 2: 41) ሐዋርያው ጳውሎስም በበዓሉ ቀን ስለ ማግኘት የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል ብሎ ሲያቅድ ያስተውላል (ሐዋ 18:21)።
ነገር ግን እግዚአብሔር ላይ በጥምቀት ወልዶ በፀጋ ያሳደገቸው ልጆቹ ሲያምፁበት ፣ ክርስቲያኖች አምላካቸውን በመዝሙር እንደማወደስ ፈንታ ሰውነታችሁንም ሳያነፁት በዓልን ሊያከብሩ ፣ የስራቸውን ክፋት ከአምላክ አይን ፊት ሳያስወግዱ ፣ ክፉ በበዓል ቀን ሲሠሩ ሲያይ ፦ በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች ሸክም ሆነውብኛል ይላል( ኢሳ 1:14-17)።
በዓል እንዲያደርጉለት ተናግሮ (ዘፀ 5:1) ለምን በዓላችንን ጠላው? ቢባል ፣ ዝሙት እያደረጉ በዓል ሲያከብሩ ስለተመለከተ፤
በቃሉ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ እንዲደረግ ተፅፎ (መሳፍ 21:19) ፣ ለምን በዓላችንን ጠላው? ቢባል በበዓሉ ቀን እንደ ሎሚ ውርወራ አይነት ዝሙት ነግሶ ፣ ከመዝሙር ይልቅ ዘፈን በዝቶ ሲያየው ተፀየፈው።
በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን አጥብቃ ይህንን ሎሚ ውርወራ ልታወግዘው ይገባል ። በተቀደሰው ታቦት አከባቢ ርኩሰት ይሠራል ። ይህ የመጨረሻ ዘመን የመሆን ምልክት ነው ።
ስለሆነም የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፣ አንባቢው ያስተውል ይለናል (ማቴ 24:15)
በበተቀደሰው ስፍራ ፣ የከበረ ታቦት ባለበት አከባቢ ፣ ይህንን የርኩሰትን ስራ የሚፈፅሙ ሁሉ ፣ ንስሐ ይግቡ ቀኑ መንግሥት ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ የተባለበት በዓል ነውና ።
ይህንን የንስሐ ጥሪ ችላ የምትሉ ሁሉ የሥጋ ስራም... እርሱም ... ስካር ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል የሚያደርጉ
የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም (ገላ 5:16-21) በሚለው መሰረት ከወራሽነት ትወጣላችሁ ። በዘፈናቸው እግዚአብሔርን አይደሰትም ፤ ስለት ስለ ነበረብኝ ለዚህ ነው የምዘፍነው የምትሉ የጌታን ስም በከንቱ እየጠራችሁ ነው ። አትሳቱ እግዚአብሔር በዘፈን አይደሰትም በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን ፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን (ሮሜ 13:13)። በጥምቀቱ በዓል የንስሐን
ጥሪ እንደመስማት ፈንታ በተቀደሰው ስፍራ ሰክራችሁ ለመዋል ለርኩሰት ስራ የምትሰበሰቡ ንስሐ ግቡ። ተመለሱ!

Sourece :
meron የማሪያም ልጅ

Comments