አንዱ እየሞተ ሌላው ይጨፍራል!
አንዱ እየሞተ ሌላው ይጨፍራል!
ይች ቃል ቀድሞ የታለመባት የተሸረበች ሴራ እንጅ
በድንገት የተከሰተች አይደለችም! አንድም የአማራ ብሄርተኝነት እያቆጠቆጠ
ስለመጣና የአማራ ተወላጁ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ኢትዮጵያዊነትና አማራነት
የባንዴራው ጨርቅ እና ቀለሙ ተዋህደው የሚፈጥሩት ውህደት ፡ የደም ውጤት
መሆኑን ስለሚውቁ ከላይ የተጠቀሰችውን ቃል በመሸረብ ህዝቡ በማይረባ አሉባልታ ተጠምዶ እርስ በእርሱ እንዲናከስ ወዳጅነታችንን በማጠልሸት እንድንፈረካከስ የታለመ ሲሆን ፣ ሁለተኛ አንድ ማይክ ባንሳ ቁጥር መድፍ ወድሮ ጦር አሰልፎ የመጣባቸው ይመስል በሱሪያቸው የሚያሸናቸውን ብላቴና ጥላቻ ያድርበት ዘንድ
የተጠነሰሰ ነው፡፡ ይህን ባያስቡ እና ባያቅዱ ኖሮ የሀገራችን
ቦለቲካ እንዲህ በተጨማለቀበት ሰአት በምንም አይነት ምክንያት ኮንሰርቱ አይፈቀድም ነበር፡፡ ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ አሁን ባለው ስርዓት ላይ በፍረቻም ይሁን በሌላ የጥቅም
መንገድ ተገፋፍተው የትግራይ ህዝብ የስርአቱ ደጋፊ መሆኑን ቢገነዘብም እንኳን አርቀው ነገን የሚያስቡ የትግራይ ልጆች ይሄን ጭቆና
እንደማይደግፉ ስለሚያውቅ የአማራው ህዝብን እየገደለ ከትግራይ ህዝብ ጋር ያለው የጥላቻ ጣርያ ላይ ማድረስ እና ትግራይ ሙሉ
በሙሉ የተለከፈ ብሔርተኛነት ነግሶ በየትኛውም ግዜ ከጎኑ እንዲሆኑ ባይሆኑ እንደሚጠፉ እንዲስቡ ማድረግና የሳይኮሎጂ ጨዋታ
መጫወት ይፈልጋል፡፡ አሁንም የሆነውም ይሄ ነው ፡፡ የወልድያ
እንቁ ወንደሞቻችንን ገደሉ ከዚያም ደም ያሰከረው ወጣት በቁጣ ተነስቶ ቁጣውን ገለጸ ከሰው ህይወት ባይወዳደርም ከህዝቡም ሆነ በጸጥታ
ስም ከሚነግደው አካላት ሞተ ከዚያም በሁለቱ ህዝብ መሀል የመረረ
ጥላቻ ነገሰ ! እንዲህ እየሆነ 3 አስርት አመታት ተጠጋ ፡፡ ከዚያም በአሻገር ‹‹ በአስራ ሰባት መርፌ በጠቆመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ስልጣን ላይ ሲወጣ አዲስ ንጉስ እንጅ ለውጥ መች መጣ ! ብሎ ከብት ጥበቃ እንጅ ሀገር ማስተዳደር የማይገባቸው መሆኑን በተሰጠው ጥበብ በግልጽ ቋንቋ የነገራቸውን ብላቴና ደመኛ ለማድረግ የሚጣጣሩ ስህተት የሆኑ ወረኞችን በመጠቀም በህዝቡ ዘንድ
እንዲጠላ ለማድረግ ሲውተረተር አስተዋልን፡፡ አውነት እላችኋለሁ ይሄንን ያናፈሳችሁ እና በደማችን ጨፈረ ያላችሁ በሙሉ አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ የወያኔ ልጓም የሚመራችሁ ፈረሶች መሆናችሁን
አወቁ ›› የፈለገውን አሉባልታ እየሸረበ በስሜት እያሰጋለበ
ወደአሰበው ቦታ የሚነዳችሁ፡፡ አሁን አላለሁ የአማራ ህዝብ መሞት ብርቁ አይደለም ሚሊዮኖች በተመሳሳይ ሴራ ተቀጭተው
ከመቃብር በታች አሉ ፡፡ እነ ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደ እየሱስንና መሰሎቹን ጨምሮ !! በየትናውም የጦር አውድማ ለነጻነት እና ለሀገር ብለን ሞተናል ብሎ እራሱን
የደፋና ድንኳን ደፍቶ እጁን አጣጥፎ የመቀመጥ ታሪክ የለውም ፡፡
አድዋንና ሌሎቹን ተመልከቱ የጦር ጀቶች እንደ ትንኝ እየለቀማቸው ከማልቀስ ይልቅ በዜማ በሽለላ ታጅበው ነበር እንደ ጧፍ ነደው
ለኛ ብርሀን ያበሩት ስለሆነም ኮንሰርቱን ህዝቡ መታደሙና ለመሰባሰብ ባገኜ አጋጣሚ ተጠቅሞ ስሜቱን መግለጹ
አንድለትን ሊያጎለብትለት የሚችል የትግል አካል ነው፡፡ ስለዚህ ቴዲ አፍሮ አሁንም ምርጥ መሆኑን የተረዳው የዘመኑ ቦለቲካ የገባው
ህዝብ ስለነበር ነው ይሄን ያደረገው ፡፡ እያወራን ያለነው ደግሞ ፈጽሞ ሰነልቦናውን ሊያዳክሙት ስላልቻሉት የአማራ ህዝብ
ነው፡፡ ስለዚህ አንዱ እየሞተ በደማቸው መጨፍር የሚል ካለ እሁንም
አደግመዋለሁ ከላይ የጠቀስሁት ፈረስ ነው!!! አማራን እንደመናቅም ነው ! የሰው ልክንም አለማጤን ነው ! ይሄን ያለ በሙሉ
በመቶ ሽ ህዝብ ስም ቅርታ ሊጠይቅና አንደ ሆኖ ወልድያ ስለሞቱት ፍትህን መፈለግ አለበት!! አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎቹም ለህዝብ ፊት ቆሞ ከማልቀስ ይልቅ ወጥተው
የወንድነት ስራ መስራት እንዲችሉ ከባላቴናው ውጡና ንገሩት !! በዘሩ አልቃሽ ሳኖረው የእሳት ልጅ አመድ አያለቃቅስብን፡፡ የሱ
ህይወት ከሚሊዎኖች አይበልጥም ፣ካልሆነለት ለሚሆንለት ወንድ ያስክብ ፡፡ አሊያም ለማ መገርሳን ያማክረው ያኔ ምን ማድረግ እንዳለበት
ይነግረው ይሆናል፡፡ ካስፈለገም የለማ መገርሳን የክቡር ዘበኖች ይጤቃቸውና የሰሩትን መንድነት ከእነሱ ይማር ፡፡ 40 ሚሊዮን
ህዝብ ይዞ የማልቀስ ታሪክ የለንም፡፡ ስለዚህ
እያንዳንድህ እናቷን እናዳጡ ጫጩቶች መደማመጥ ሳይኖር
አትንጫጫ፡፡
ልቦና ይስጣችሁ ፍትል ለወልድያ እና መሰሎቻቸው፡፡



Comments