አንዳንዴ የሆነ ! ህልም የመሰለ እውነት ይገጥምህና እንደመራህ እንጅ እንደመራኸው መጓዝ ታቆማለህ ! ህይወት ግን አጋጣሚዋ ሲገርም
፡፡ ሰዎች ስንባል በቃ በፊታችን ላይ የተደገሰውን ድግስ አልታዬን ብሎ ማማረር የህይወታችን አንድ አካል ነው፡፡ ሁሌም ትልቅ ፀሐይ የመሰለ ብርሐን ፊታችን ላይ ተደቅኖ አይናችን ላይ ያለው
ቅርቡ የወጣትነት መነጸር ይጋርደንና ማስተዋል አንችልም፡፡ ወገቧ እንደ አንዝርት
የሾር ኮረዳ ባዬን ቁጥር የአይናችን ማነጣጠሪያ ከልጀቱ አረማመድ
ጋር እንጅ ከቀልባችን መሆኑን ይዘነጋል፡፡ ካስፈለገም በዳሌዋ ፈገግታ ገልመጥ አድርጋን ካለፈችም ዜብራ ላይ ቆመን በባለሀብት ገንዘብ
ቀልቧ የጠፋ እንስት ከቤቷ ግድግዳ የሰቀለችው መስታወት ይመስል አስር ጊዜ በመኪናዋ መስታወት ፊቷን እየተመለከተች በምታሽከረክረው ቪትስ ፍትፍት
ልንሆን እንደርሳለን!(አልዋሸሁም አይደል እያንዳንድሽ) ይሄ ሁሉ ግን መጨረሻውን መገመት ያዳግታል! በዚህች አቅማዳ በማትሞላ እድሜዬ( እድሜህ እህል ነው እንዴ በአቅማዳ የሚሰፈር
እንዳትሉኝ ማገናኜትደስ ስለሚለኝ ነው!)ስንቱን ውጣ ውረድ አየሁት አንዱም ግን የሆነው የለምክንያት አልነበረም፡፡ መጥፎው አስተምሮህ
ያልፋል ጥሩው ደግሞ አበርትቶህ አንድ እርምጃ እንድትራመድ ወደፊት ይጎትትሀል፡፡ በዚህ ሁሉ ትግል ግን ውሳኔ ! ከባዱ እና ቆራጥነትን
የሚጠይቅ ነው ፡፡ እኔ ደግሞ ለውሳኔ የሚቀድመኝ ሁሉ ያለ አይመስለኝም ፡ በቃ መወሰን ደስ ይለኛል፡፡ ታዲያ ውሳኔዬ ሁሉ ግን
አንዳልጸጸትበት ለአፍታም ቢሆን መገናዘብን አልረሳም ፡፡ አንዳዴ
ግን ድንገት ውስጥህ ሰው በናፈቀበት ሰአት ! በቃ የእውነ አንተነትህ እንዲሰማህ የሚያደርግህ ሰው ! የሆነ ትንፋሻችሁ የሚመሳሰል
! የሆነ እንደመልዓክ ውርድ ብሎ ልብህን ትንፍስ የሚያደረግልህ ሰው ይከሰታል! እሁሁሁሁ … ያኔ በውጣውረድ የባዘነው ዱካክህ በሙሉ
እርግፍ ይልና የሆነ ቀለል እያለህ አጠገብህ ያለውን ሰው ብቻ ትዘምራለህ
! ድስስ ይላል በእውነት … ደግሞ ይሄ የደስታህ ምንጭ የሆነ ሰው ከግራ ጎንህ ተነትቃ የመጣችሁ ሄዋንህ ስትሆን ያች ከኤደን ገነት
ከጎንህ የተቀመጨችው እጸበለስን ከእሷስ ጋ ከሆነ ይሁን ብለህ ያመንካት ሄዋንህ ስትሆን ! አሸሸ ገዳሜ አትጠይቀኝ ቀልብህ ይጣፋል! በዚህ አለም ላይ በሙሉ ከዛች እንስት ውጭ ሴት ያለ ሁሉ አይመስልህም! ሰውነትህ
ትንሽ ፈርጠም ብሎ ትከሻህን አየደቃህ የምትሄድ እሳት ወጣትነትህ ያላለፈ ወንድ ከሆንህ ደሞ ! ቀና ብሎ የገላመጣትን ሁሉ በአይንህ
አፈር ዱቤ እያስጋጥኸው ትራመዳልህ! ደስስስስ ይልሀል! ምን ለማለት
ፈልጌ ነው ! በቅርቡ አንድ ትልቅ ውሳኔ ወስኛለሁ ይሄ ውሳኔ ይፋ
ሆኖ ለገሐዱ አለም ሲገለጥ ምድረ …. እንትን ሁላ … አይመለከተንም (ሀሀሀሀሀሀሀ) እንዳንድሽ እርምሽን አውጭ ! አጠገቤ የሆነ
ጀርባ የሆነ ሰው ትከሻዬ ላይ ድግን ብሎ መግቢ መንገድሽ ሁሉ ተዘግቷል! እስከአሁን ያላየሁት ብርሀን እያየሁ እንደሆን አልገባሽም
…. ገሀድ እስኪወጣ ምጽአት የምትጠብቂ ሁላ …. ለማውራት አፍሽን በተልባ አሟሽና ጠብቂ … እኔ ከሆን የጨው ሀውልት ይመስል መቅለጥ
ጀምሬያለሁ…. ቻው ..
(ዘላለም በላይነህ)
Comments