እርጅናን አምኖ የማይቀበል ትውልድ ጊዜ ባገነነው ውሸት እውነትን ለመጨፍለቅ ሲታገል አገር ይገድላል ትውልድ ቀብራል !


እርጅናን አምኖ የማይቀበል ትውልድ  ጊዜ ባገነነው ውሸት እውነትን ለመጨፍለቅ ሲታገል አገር ይገድላል ትውልድ ቀብራል ! እርጅናውን አምኖ የማይቀበል አንበሳ ጅብ ሲያሯሩጥ እራሱ ይበላል ! ለጅቦችም አምበሳነትን አስደፍሮ ለቀጣዩ የአንበሳ ተውልድ ፈተና ጥሎ ያልፋል!
ሀገር በአሮጌው መሰረትነት  አዲስ አቋምና ግድግዳ አድርጋ ብትገነባ  ፋኖስ እና ብርጫቆ ማለት ነበሩ፡፡  አሁን ግን ሀገራችን ላይ እርጅና እና ወጣትነት ትግል ውስጥ ስለገቡ ንፋስና ብርጭቆው የተሰበረ ፋኖስ ሆነዋል! አንደኛው ከአንደኛው በባህሪም እንዳይስማሙ የተፈጠሩ መስለዋል (የሰውነት ባህሪ) ሁሉም ነገር ወቅት እና ጊዜ አለው ብረት ከዛገ እና ብል ከበላው በኋላ ምሶሶ ቢሆን ከእንጨት በቀደመ ፍጥነት አፈር ይጎርደውና ለህንጻው መውደቅ ምክንያት ይሆናል ፡፡ ጠንቃራውን እና ለቤቱ ውበት የተሰደሩትን ሌላም ሌላም ነገሮች ከንቱ አድርጎ መሰረት አልባ ያደርግና  የተደረመሰው ህንጻ  የሚል ያጋራ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡  ኢትዮጵያ ሀገራችን  ዘረኝነት እና መነጣጠልን አላማ አድርገው በተነሱ አዛውንቶች ተጠምዳ አባያነት የገነነበት ወጣት እያሳደገች ቁልቁለቷን ቀጥላለች! ይህ ነው የከፍታ ዘመን !!!! የሰው ልጅ እድሜው እየበሰለ እሳትነቱን እያቀዘቀዘ በሄደ ቁጥር ድሮ ድሮ አስተዋይ እና እራስ ወዳድነቱን እየተወ ሀገር እና ትውልድን ያስብ ነበር! አሁን ግን  ሀገራችን በእነ ብቻ እንብላው ተከባ  ትውልድ ማሰብ የሚባለው ታላቅ ሀሳብ በጫት እና በሽሻ ተከልሎ ልክ እንደጥርሳቸው ጭንቅላታቸውም ከበለዘ አመታት አስቆጥሯል!! እንዲህ ነው እንግዲ ትውልድ ማሰብ! የሚፈልጉትን ለማድረግ ሆዳቸውን የሚጋፋ ከመጣ የመብራቱ መጥፋት ሳያሳስባቸው የፋኖሱን ብርጭቆ ይከረሽሙታል (ልክ ወልድያ፣ ባህር ዳር ፣ደብረዘይት፣ጎንደር ወዘተ እንደተደረገው) ሲፈልግም በራሱ ትንፋሽ ብርሀኑን ማጥፋት ካስጠላው በባእድ ነፋስ ውጭ አውጥቶ ያስጠፋዋል(ከሱዳን ወገን ያልሆነ ወታደር አምጥተው ባህርዳር እና ጎንደር እንደገደሉን) ይህ ነው እንግዲ የመገርጀፍ ውጤቱ ምክንያቱም  በትክክል ማሰብ ማለት ለአሁኖቹ ሽማግሌውች(መሪ ነን ባዮችን ነው ! ለሀገር እድሜያቸውን ሰጥተው መንገድ የወደቁትን አላልሁም) የራስ ዳሸንን ተራራ በ90 አመታቸው በእግር እንደመውጣት ነውና!  ከስፈለገም የሀይማኖት ፖለቲከኞችንም ብል ቅር አይለንም (የሀይማኖት አባቶችን አላልሁም)በምኩራቡ ላይ ወጠው  ከታቦቱ ስር ዳጎን(ጣኦት) የሆኑብንን ነው ያልሁ፡፡ ሽጉጥ እና መስቀል በባህሪያቸው የማይስማሙትን በአንድ ማህደር የተሸከሙትን ነው ያልሁት ! አሁንም እላለሁ እነዚህ ሰዎች ከምኩራቡ ወርደው ባልገረጀፈ አስተሳሰብ በታሪክ መሰረትነት ነባራዊውን ሁኔታ  ከዘመኑ ዴሞክራሲ ጋር ሳያጋጩ አስማምተው እንደ ፋኖሱና ብርጭቆው አንዱ ለአንዱ አስፈላጊነቱን  ማስገንዘብ ካልተቻለ ገና ብዙ ብርሀኖችን ያጠፋሉ እና ቆም ብለን እናስብ፡፡
የግርጌ ማስታወሻ ፡-
መብራቱ እንዳይጠፋ እንከላከለው ዘንድ  እንድአንድ ጽንፈኛ የትግራይ  ወንድሞቻችን እልክ እና ፍርሀት ሆድና የብቻነት ሳይነግስ በትክክለኛው በወንድማዊነት አስቡና የፍቅር ሀውልት መገንባት ትችሉ ነበር ፡፡ ገንብታችሁ  መሄድ የምትችሉበት 27 አመትም የኢትዮጵያ ህዝብ ሰጥቷችሁ አንድም የፍቅር ሀውልት ሳይገነባ የጥላቻ እና የጥል ሀውልት ገነባችሁበት፡፤ አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ እጇን ዘርግታ ለመነቻችሁ ብዙዎቻችሁ ግን የመስማት እዝናችሁን ደፍናችሁ እንዳታደምጧት ጀርባ እንጅ ጀሮ አልሰጣችኋትም ፡፡ አንደም  ይሄ መንግሰት ከተነሳ የሚመጣው ቂም ስላለበት ይጎዳናል በሚል አጉል ፍራቻ ሁለትም ይሄ መንግስት በፈጠረው አጉል እራስ ወዳደነትና በአጉል ትቢት ተሞልታችሁ ፡፡ እኔ ግን እላለሁ ይሄ ሁሉ የተባለው ከሀገር አየብልጥም ሰው እና መንግስት ዘላለም አይኖርም ! የሂትለር ሰራዊት እንኳን ወድቆ ታሪክ ተቀይረዋል ፡፡ ብታውቁት የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ በተጨነቃችሁ ጊዜ ቀድሞ ደሙን የሚያፈስላችሁ ወንድማችሁ ነበር አሁን ግን በገዛ እኩይ ተግባራችሁ መንድማዊነቱን እየገፋችሁ ወደጠላትነት እየቀየራችሁት ነው ፡፡ ይህ ደግሞ የአውሬነት ባህሪ እንጅ ሰብዓዊነት አይደለም ፡፡ ስለዚህ አሁንም ድረስ በግትርነት እና በአጉል ትቢት ተሞልታችሁ ከምትገፉበት ነገ የሚኖረውን ትግራይ ህዝብ ማሰቡ መልካመ ነው እላለሁ፡፡  ምክንያቱም ብታዉቁስ  እራሱን የሚጠላ ማንም የለምና!!
የግርጌ ማሰታወሻ ሁለት
ውድ የተገፋፋኸው እምዬ ኢትዮጵያ ልጅ አማራ እና ሞሮሞ ድምጻችሁ ከተሰማ ሌሎችም !
በስሜታዊነት ከመነዳት ወትታችሁ እራሳችሁን በማያስጠቃ መልኩ ለውጥ ይመጣ ዘንድ መትጋቱ በየትኛውም ሀገር እና ዘመን ያለ ነገር ሆኖ ሳለ ፡፡ አሁን ግን የምትቃወሙት ስርአት በሚፈልገው መልኩ እንጅ በምትፈልጉት እንዳይሄድ ብዙ እንቅፋቶች እየገጠሟችሁ ነው ይህ ደግሞ ፍሬ የሌለውና መሰረት የሎለው በስሜታዊነት ብቻ የታገዘ ተቃውሞ ስለሆነ ይመስለኛል ፡፡ ስለዚህ እራሳችሁን ከጅብ አጋዚ በጠበቀና በጠበቀ መልኩ አላማችሁ ግብ ይመታ ዘንድ መንቀሰቀሱ መልካም ነውና አስተውሉ፡፡
ከመካከላችሁ አንድ ጠንቃራ እና ለስርአቱ ደህንነት የሚያሰጋው ማለትም ኢሀዴግን የማይደግፍ ተቃዋሚ  ህዘብን የማሳመን ችሎታቸውና የማገናዘብ ሐቅማቸው ከፋ ያሉ ሰዎችን በምን አይነት መልኩ ከህዝቡ ጋር አቃቅሮ ከጨዋታ ውጭ ምድረግ እንደላባቸው የተካኑበት ነውና ከስሜት በጸዳ መልኩ እራሳችሁን ቤታችሁን መመርመር መልካም ነው ፡፡ ምክንያቱም አንድ የሆነ ሰው ሶሻል ሚድያው ላይ አንዱን ከፍ ካደረገው አብሮ አብሮ ከፍፍፍፍ አንዱ ድንገት አንዱን ከዘረጠጠው አብሮ ዝርጥጥጥ መልካም አይደለምና ከዚህ ተቆተቡ እንቆጠብ !! መልካም ጊዜ ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!