ለአየሁ ልጆች እና ለአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አመራሮች
ለአየሁ ልጆች እና ለአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አመራሮች
ውድ የአየሁ እና አካባቢዎ ልጆች እንደምን አላችሁ እንደሚታወቀው በባለፈው ማህበር ለማቋቋም ወሬው ተዛምቶ ብዙ
ልጆችም እጅግ ተደሰትን አሁን ግን ህጋዊ ፈቃድ በማግኜት እና ባለማግኜት በተፈጠረው መጓተት ምክንያት ሁሉም ሰው ቀዝቀዝ ያለ መስሏል
፡፡ ሆኖም ይሄ ማህብር ሲቋቋም ማህበሩን ለማቋቋም የተሰየሙትን ሰዎች ብቻ ያስፈጽሙ ብሎ መጠበቅ ትክክል አይደለምና ሁላችንም ተጽኖ
መፍጠርና ወረዳው ማለትም አየሁ ጓጉሳ ወረዳ ፈቃዱን ይሰጠን እና ህጋዊነቱን በሰላም እና ያለምንም መተዛዘብ ይፈቀድልን ዘንድ መግፋት
አለብን፡፡ ምክንያቱም በአመራር ቦታ ላይ ቁጭ ያሉ ሰዎች የማህበረሰቡን ችግር እና የወጣቶችን ቅን ስሜት መረዳት እንዳለባቸው ይሰማኛል፡፡
ከዚህ ባሻገር በውስጣቸው ያሌለ እና ያልሆነ ፍራቻ እና ጥርጥር አስበው የሚያጓትቱት ትክክል እንዳልሆነ ልናስረዳ ይገባል ፡፡ አመራር
ላይ ቁጭ ያሉት ሰዎችም ቢሆኑ ከዚህ ማህበረሰብ የወጡ በዚህ ችግር ውስጥ ያለፈ አሁንም እያሳለፈ ያለ ቤተሰብ ያላቸው እና የተገኙ
በመሆናችው እራሳቸው ከኛ ከጠያቂዎቹ ባሻገር ሊያስፈጽሙልን እንደሚገባ ደጋግምን እንጠይቃለን ጠይቀናልም ፡፡ በተደጋጋሚ በስልክም
ሆነ በሌላ መንገድ ስንጠይቃችሁ የምትሰጡን መልስ አጥጋቢ ባለመሆኑ እንደታስቡበት እና እንድታስፈፅሙልን እንጠይቃለን፡፡
ዘላለም በላይነህ የአየሁ ልጅ
Comments