#አማራ--ይድመቅ--ኢትዮጵያ--ትድቀቅ--ብሎ--የሚያስብ--ስብዕና--የለውምም--አይኖረውምም
#አማራ--ይድመቅ--ኢትዮጵያ--ትድቀቅ--ብሎ--የሚያስብ--ስብዕና--የለውምም--አይኖረውምም
ግብረ ገብነት ምግባራቸው የሆኑ ሰዎች በውስጣቸው
ታላቅ እምነት አለ ይህ እምነት ደግሞ ጽናትና ብርታት ሲደመር ማስተዋልና
ማገናዘብ ዋና መርሐቸው ሆኖ አዕምሮቸውን ነጻና የህሌና ህግን ለመጣስ ድፍረት የሌላቸው እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ለሀማኖታቸው ተገዥ ናቸው ሀይማኖታቸውንም
የሚከተሉት ከቤተሰብ እንዲሁ በመወለድ ስለወረሱት ሳይሆን አንብበው መርምረው አምነውት ተቀብለውት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በአዕምሮአችን
ውስጥ የሚመላለሰው ነገር መጥፎ ከሆነና ፍርሀት የሚፈጥርብን ሲሆን እራሳችንን ለመከላከል ስንል በዙ ጥፋቶችንና ብዙ ከእውነታ የራቁ
አውሬነት ባህሪያቸው የሆነ ነገሮችን እናደርጋለን ፡፡ አንዲህ አይነት ስህተት ውስጥ ከገባን ደግሞ እራስ ወዳድነታችን እንጅ ሀገር፣ወገን፣ትውልድ
ትዝ አይለንም፡፡ እራሳችንን ከምንሰራቸው ፍርሐት ከፈጠራቸው ነገሮች ለመሸፈን ከዘራናቸው መጥፎ ነገሮች እያጨድን እና እየወቃን
ትውልድ እንገድልበታለን ፡፡ አሁን አሁን ይሄን ስርአት የሚመሩትና ጅራቶቹ ገና ከደደቢት በረሐ ሲነሱ በማኒፌስቶአቸው እንደገለጹት
አንድ ሀይልን አማራን ጠላት አድርገው በመደጋገም በዚህ ብሄር ላይ እጅግ የመረረ ፍርሐት የፈጠራቸው ጥላቻዎች ገዝፈው ይታያሉ፡፡
ትግራይ በተጨነቀች ጊዜ ቀድሞ የሚደርስ አማራ መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ ጭፍን ጥላቻን ፈጥሮ ህዝቡ ትግላቸውን እንዲያጧጡፍ ማድረግን
መረጡ፡፡ በወቅቱ በኤርትራ በወያኔና በኢሀፓ ሲደመር በደርግ የተፈጠረው መርመስመስ ጥሩ አጋጣሚ ሆነላቸው፡፡ በወቅቱ ህዋሀት ከሽሬ
ማልፍ አልቻለም ነበር ተደባብሶ እንጅ አሸሸ ገዳሜ ብሎ ያመጣቸው
እና ያስቀመጣቸው እንዲህ ለጥፋት የተዘጋጁበት አማራ ነበር ፡፡ በወቅቱ የነበረው የደርግ ፖለቲካ ያንገሸገሸው አማራ ከደርግ ይልቅ
እንዚህን የጥፋት ውሀዎች መደገፉ ለጊዜውም ቢሆን ትንፋሽ ሰጥቶት ነበር፡፡ ብዙ ብሄሮች እራሳቸውን ከማነኛውም ነገር ለመከላከል
እኛ ጉራጌ እኛ ኦሮሞ እኛ ትግራዋይ ወዘተ እያሉ ቤታቸውን ለመጠበቅ ሲሯሯጡ በሳለፍናቸው አመታት ተመለከትን ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን
አማራ የአንድነት ምንፈስ ይሰፍን እና ኢትዮጵያ የምትባለዋ ሀገር ትቆም ዘንድ እራሱን እንዲረሳና የጥፋት ዉሃ የሆኑት የዘመኑ መቅዘፍቶች
እስኪያንሰራሩበት ድረስ በኢትዮጵያዊነት ፍቀር ተለክፎ ጀሮውን ደፍኖ ቆይቶ ብዙ የመከራና የስቃይ አመታትን አሳለፈ፡፡ አሁንም እያሳለፈ ነው ፡፡ መርዝ በጥብጠው ሲግቱት ወተት ሞት ሲደገስለት ጤፍና በርበሬ እየመገበ ስለሀር አንድነት እራሱን ማንነቱን
ሊያጠፉት በተነሱ አውሬዎች ሲበላ እና ሲበዘበዝ ኖረ አሁን ግን ይሄ
የሚያስኬድ እና የሚያዋጣ ህልውናውን ለመጥፋት የሚያደርስ ተግዳሮትና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲደርስበት እየገባው እና እራሱን ለመጠበቅ
መደራጀት እንዳለበት የሚያቀነቅኑ በደልና ሰቆቃ የፈጠራቸው እሳቶች
ተነሱ ፡፡ ይሄ ደግሞ ለብዙዎች የሚያስደነግጥ ነው ይሄ ደግሞ ለወያኔዎች እንቅልፍ የሚያሳጣ እረፍት የሚነሳ ነው፡፡ ስለዚህ ድሮ
ኢትዮጵያን እያለ እራሱን የበደለበትን ዘመናት ተመልሶ እንዲኖር / የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን የሚል / ለበሬ አሞሌ ጨው እያሳዩ
እንደማስከተል የሆነ የጅላጅል ስራ ሊሰሩ ሞከሩ ይሄ ደግሞ የህዝቡን የማገናዘብ ሀቅምና ስነልቦና ካለማወቅ የታቀደ የጨዋ /ያልተማረ/
አስተሳሰብ የፈጠረው ባዶነት ነው፡፡ እርግጥ ነው ባንዴራውን እና ቀለሙን መለያየት እያቻልምና አማራ የኢትዮጵያን ከፍታ ሁሌም ይናፍቃል
ያልማል ፡፡ ይሄ የሚሆነው ግን አማራ እንደአማራነቱ ተደራጅቶ እራሱን ሳያጠፉት መቆም ሲችልና ማሰብ ሲችል ብቻ ነው ፡፡ አማራ
ይድመቅ ኢትዮጵያ ትድቀቅ ብሎ የሚያስብ ስብዕና የለውምም አይኖረውምም ! ሆኖም ግን ብዙውን እንዳየነው እራሱን ለመጠበቅ እንጅ
ኢትዮጵያን ለመገንባት የተቋቋመና ብሔሬ ትቅድም ያለ ዬለም፡፡ ብቻ የሚያስቀድሙት ብሄር ደና ይሁን እንጅ እትዮጵያ ገደል ብትገባ
አይጨነቅም ! ስለዚህ ኢትዮጵያ እንደኢትዮጵያ ትቀጥል ዘንድ ለዚህች ሀገር ክብር ባህል እና ስም የሚጨነቅ አንድ ታላቅ ብሄር እራሱን
ማጠንቀር አለበት እርሱም /አማራ/ ሌላም የሚደግፍ ብሄር አለሁ የሚል ካለ በተግባር ከሳዬ ይበርታልን ከማለት ውጭ ምንም አንልም
ምክንያቱም ኢትዮጵያን ማትረፍ የዚህ ታላቅ እና የባለብዙ ታሪክ ባለቤት
የሆነ ብሄር ህልም ነውና፡፡ በአማራነታቸው ተደራጁ ብለው የሚያላዝኑ ከአንገት በላይ የማስመሰል የኢትዮጵዊነት ፍቅር ስርአቱ ከበቀል
ፈቅፍቆ በሰራው ሴራ የሚዋኙ ጅላጅሎች ናቸውና ፡፡ እዳው ወሬ ነው ቦታም መስጠት አያስፈልግም ፡፡ለቀባሪ አረዱት ነው የሚሆነው
፡፡ ከድጥ ወደማጡ እንድንገባ እየጎተጎቱንም ነው ፡፡ ይሄንን የሚያደርግ ስነልቦና ደግሞ አባቶቻችን አላወረሱንም ! ስዚህ ላሽ …… ግዮናዊነት የኢትዮጵዊነት መሰረት አንደሆነ አይደለም እኛ እራሳችን
አውሮፓውያንም በተለያዬ ጊዜ ከውንዶቹ ተረድተዋል ተሸንፈውም ለአለም ተናግረዋል ፡፡ ወደድህም ጠላህም ኢትዮጵያን ወደቀድሞ ማንነቷ
ለመመለስ ግዮናዊነትን መደገፍ አንድ እና አንድ ያውም ትክክለኛው ስሜት ነው፡፡ ቤቱን ሳይገነባ ባልሰራው ቤት ሊጠለል የሚመኝ ሰብዕ
የለምና፡፡ ቤቱን አስቀድሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
አስተያያት መስጠት መብት ነው ! ይሄ የሚያስብና
የሚያገናዝብ የተማረ ሰው ምግባር ነውና ! በጭፍን መነዳት ግን መንጋነት ነው እንዲህ አይነት ሰው ከብትነት ባህረው ነውና ፡፡ቻው
ከዚህ መጨረሻ ከጠቀስሁት ቃል የትኛው እንደሆንህ ይሄንን አንብበህ የጨረስህ ሁሉ እራስህን መርምር፡፡ ምርጫው በእጅህ ነው፡፡ ቻው
ዜዶ ነኝ
https://www.facebook.com/zelalembelayne/
Comments