በሬውን አረዱት ከቀንበሩ ፈተው ሞፈሩን ፈለጡት የስጋ መጥበሻ ዝም ብሎ ማየት ነው የዚን መጨረሻ !


በሬውን አረዱት ከቀንበሩ ፈተው
ሞፈሩን ፈለጡት የስጋ መጥበሻ ዝም ብሎ ማየት ነው የዚን መጨረሻ !
 እያልን የበደልን ጽዋ አብዝተን ተጎነጨን ! ለም መሬት እያለን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ እትብታችን የተቀበረበትን ቦታ ጥለን ተሰደድን፤ምርቱ  የአማራን ህዝብ አይደለም ኢትዮጵያን የሚያጠግብ ሆኖ ሳለ ተራብን ፤የንነገስታት ዘር ሆነን ሳለ ባርያ አገልጋይ ሊያደረጉን ጣሩ፤ ይሄም ሁሉ ሆኖ ግን አልጠፋንም ይሄም ሁሉ ሆኖ ግን በአባቶቻችን የተገነባ ታላቅ ስነ ልቦና አለን፤ በየትኛውም ዩኒቨርስቲ ባለምጡቅ አዕምሮ ሁነን እያለ እንደ እውቀት ድሀ ቆጠሩን ይህም ሆኖ እያለ ግን በስቃይ እና በድህነትም አልፈን ተምረን በየዩኒቨርስቲዎች የዋጫ ክብር ባለቤት ነን ! እና እንዴት አይነት ድፍረት ነው ይሄን ህዝብ ለማጥፋት መሞከር ፈጽሞ የማይቻል እውነት ! ይሄ ህዝብ ድሮም አሁንም ለወደፊትም በአለት ግርግዳ የተገነባ ጠንካራ ሀውልት ነው የኢትዮጵያ መሰረት ነው ፡፡ ተወደደም ተጠላም አማራ የኢትዮጵያ  የማእዘን ድንጋ ነው፡፡
(ዘላለም በላይነህ)

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!