****ለአሉላ አባ ነጋ ለዶጋሊው ንጉስ የተጻፈ ደብዳቤ**
****ለአሉላ አባ ነጋ ለዶጋሊው ንጉስ የተጻፈ
ደብዳቤ**
//
በ18 79 አንድ ቁጡ የዛር ፈረስ የመሰለ ኢትዮጵያዊ
ጅግና ከትግራይ ተነሳ የጥልያንን ጅቦችም አሳፍሮ ወንድ የወንድ ልጅ አራቸውን አብልቶ ኢትዮጵያዊነት ወኔውና ጀግነት ምን እንደሚመስል
አሳያቸው አስተማራቸው ጀግናው አሉላ አባ ነጋ ይህ ጀግና እንዳሁኖቹ የእሳት ልጅ አመድ የወገኑን ደም ለማፍሰስ እና ከርሱን ከወገኖቹ
የሚያስበልጥ ሳይሆን እራሱን ለሀገሩ እና ለክብሩ ለወገኑ አሳልፎ የሚሰጥ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዚህ አሉላ በተወለደበት ታሪክ
በሰራበት
‹‹ አሉላ አባ ነጋ የወንዶች ወንድ ነው ያውም ሰማዕት
ደምጹ እንደነጎድጓድ አይኑ እንደመብራት
ያስፈራ ነበረ ዶጋሊ ሲዘምት ›› የተባለለት ምርጥ
ነበር፡፡
ይድረስ ለጀግናችን ስጋህ ከምድር በታች ታሪክህ ከምድር በላይ ላለኸው ጀግናው አሉላ አባ ነጋ
የውነት በልጆችህ ብንከፋም ብናፍርም ብናዝንም
ባንተ ደም ግን እንኮራለን ! ምክንያቱም እንደአሁኖቹ ልጆችህ ባንዳ አይደለህምና ፣እንዳሁኖቹ ሀገርህን አሳልፈህ ለባዕድ የምትሸጥ
ሳትሆን እራስህን ለሀገርህ አሳልፈህ የምትሰጥ ጀግና ነህ፡፡ ኣኛም ታሪካችንን ጀግናችንን እናወድስ ዘንድ የተፈጠርን የኢትዮጵያ
ልጆች በባንዴራው ስር ለመሞት የተዘጋጀን በደማችሁ ያቆያችኋትን ባንዴራ ልንሞትላት ተዘጋጅተን የጠፈጠርን ነንና ልባችን አይደነግጥም
፡፡ ግን ልጆችህ ይችን ሀገር ሊያጠፉ የጠላትህን ደም ባፈሰስህበት
መሬት ተማምለው የወገኖችህን ደም እንደቫምፓየር ባከበርኸው በታቦቱ ስፍራ እየመጠጡን ነውና አጥንትህ ይውቀሳቸው ብያለሁ ፡፡ ለማንኛውም ነፍስህን በገነት ጀግንነትህን በልጆችህ ውስጥታሳድር ዘንድ አጠይቅሀለሁ፡፡
አፈሩ ይቅለለህ የዛሬ አመት አንገናኝ፡፡
እያንዳንድሽ ባንዳ ሁላ አያትሽን ተመልከች ….
!
(ዘላለም በላይነህ)

Comments