እረ ወገን በስሜት ከመነዳት እንውጣ እንዴ!!


እረ ወገን በስሜት ከመነዳት እንውጣ  እንዴ!!

ቆይ እርስበእርሳችን ተቃቅረን ለጠላት ልብ ልብ እንድንሰጥ አትፍቀዱ፡፡ አክቲቢስቶች አሁንስ አበዛችሁት ! ህዝቡ እኮ የማሰቢያ አእምሮ አለው ! ፌስቡክ ላይ ቁጭ ብሎ ከማውተርተር ያለፈ ህይወቱን የሚሰጠው ትውልድ ! ህዝብን ለችግር እና ለሞት የሚዳርግ ስርአት ተንሰራፍቶበት ጨለማ በሆበት ላይ ህዝቡ ለሁለት ተከፍሎ ይነታረክ ዘንድ መንገድ አትሁኑብን ! በቃ  የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ምናምን እያላችሁ ወጣቱን ለሁለት አትክፈሉ ፡፡ ቀንድ ያበቀለብህ እና በህልውናህ ላይ እየተረማመደብህ ያለውን ጠላት ትተህ ! አንድ ቴዲ አፍሮ ላይ ምላስ ማርዘም ተገቢ አይመስለኝም ! እስኪ በምን ቋንቋ ሲተረጎም ነው የወልድያ ወንደሞቻችን ሞት ሀላፊነት ቴዲ አፍሮ ሊወስድ የሚችለው! በየትኛው ፖለቲካዊ እይታ!  ጭፍን አንሁን እንጅ ጎበዝ!!  ቆይ መች ነው ሳናዝን የኖርንበት ዘመን ! የቴዲን ኮንሰርት ድሮውንም ወያኔ ነው የፈቀደው! ማለት ምን ማለት ነው ! ኮንሰርት የመጣው ይምጣ ብለህ የምትወታበት የተቃውሞ ሰልፍ መሰለህ ሰላማዊ ሰልፍ መሰለህ እንዴ ! እስኪ አሁን  ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ወያኔ ሳይፈቅድ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ የሚችል ዘፋኝ ጥሩልኝ እንዴትስ ይቻላል! ለምን የማይገናኝ ነገር አያገናናችሁ እኛ በእኛ እንድንባላ የወሬ ርእስ ትፈጥራላችሁ! በእውነት ያሳፍራል!!  ጠላትን ልታሸንፍ የምትችለው ወደድክም ጠላህም እርስ በእርስክ የሚከፋፍልህ ነገር እየቆሰቆስህ ሳይሆን አንድ የሚደርግህን ሻማ እያበራህ ነው!!  ወልድያ ላይ የተከሰተው ሞት በወያኔ ሀይል መሆኑን እያወቅን እንዴት የቴዲ ነው እንላለን ! ምንአልባት ከብዙ ጊዜ በኋላ ለቴዲ ኮንሰርት የፈቀደው እኝና እርስበእርስ ለማነታረክ ያቀደው የአላማው ማስፈጸሚያ ፈረስ ቢሆንስ ! እና በተዘጋጀልን የጠላት ፈረስ ጋልቦ አዘቅት መግባት ወይስ ፈረሱን መቅጨት ይሻላል !! በእውነት አውሮፓ እና አሜሪካ ሆናችሁ ከህዝብ ወገን ነን የምትሉ አክቲቢስቶች አገናዝባችሁ ጻፉ !  አማራነትን ማቀንቀን ኢትዮጵያዊነትን መጥላት እንዳልሆነ መዘንጋትም የለብንም ! ስለዚህ አስበን እንራመድ አላለሁ መልካም ቀን፡፡
(ዘላለም በላይነህ)

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!