የአማራ ህዝብ ፀቡ ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን እውነተኛዋን ኢትዮጵያን ከሚጠሉ ጋር ነው! | የቴዲ ኮንሰርት ለአማራ ህዝብ ያለው ጥቅም (አያሌው መንበር)
እኔ እስከማውቀው ድረስ የአማራ ብሄርተኝነት አንዱ ልዩ መለያው የኢትዮጵያ እሴቶች የሚባሉትን የኢትዮጵያውያንን ታሪክ፣ ወግ፣ ባህል በመውደድና በማክበር እንዲሁም ለማስከበር እንደ እቅድ መያዙ ነው።በዚህም የኢትዮጵያ ታሪክ ተጭኖብን ነው፣ የአንድ ብሄር የበላይነት ተጭኖናል፣ የውሸት ታሪክ ነው…ወዘተ ከሚሉት ይለያል። እናም ስለኢትዮጵያ ታሪክ ሳይበረዝ ሳይደለዝ ለሚያከብር እና እታገላለው ለሚል ሁሉ ቀና እይታ ብቻ ሳይሆን እኔነት ባህሪይም አለው ማለት ነው።አማራና ኢትዮጵያዊነት አይጋጩም የምንለውም ለዚህ ነው።
በዚህ መስፈርት ብቻ ተንተርሰን ቴዲ አፍሮን ብንለካው የአማራው እሴት የምንለውን አክብሮ የሚጓዝ ብቸኛው አርቲስት እና የልጅ አዋቂ ያደርገዋል።ቴዲ ሌሎች የሚጠሏቸውንና የሚከሷቸውን አፄዎችንና ታሪካቸውን አይዘልፍም።አይዘልፍም ብቻ ሳይሆን ታሪክ አገላብጦ ታሪካቸውን ገድላቸውን ያወድሳል።በዘመነ ህወሃት ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት የውልደት ቀን ያነሰ ክብር የተሰጠውን በተግባር ግን የጥቁር ህዝቦች የገናናነት ምሳሌ የሆነው አድዋና የድሉ ባለቤቶች ከፍ ብለው እንዲታወሱ አድርጓል።ክንደ ብርቱ የቋራው ካሳን ዋልታና ማገርነት ሲገልፅ ለብዙዎች በማይገባን ቅኔው ነው።
በዚህም ከሁሉም ያልተናነሰ ፈተናን ተቀብሏል።ቴዲ በህወሃት ዘንድ እንድትጠፋ የምትፈለገውንና እኛም የምንታገልላትን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ታሪኳን ጠብቃ እንድትቀጥል ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመፈቃቀር እንድንኖር የሚሰራ ገራሚ ወጣት ነው።እርግጥ ነው ቴዲ አማራ ዘሩ ጠፋ፣ ከብልቱ ውሃ ተንጠልጥሎ ተሰቃየ አይልም።ይህም አማራውን ካለመውደዱ ሳይሆን ፍትህ የሚገኝበትን ስልት የሚያይበት የራሱ እይታ ስለሚኖረው እንጅ ሰብአዊነት ስለማይሰማው ቀርቶ አይመለኝም።(እዚህ ላይ ቴዲ በሚደያ እንዲመልሳቸው የምፈልጋቸው እንዳሉ ይያዝልኝና)
ስለሆነም ቴዲ በቀጥታ ነፍጥ አንስቶ አይታገል ወይም አማራ አማራ አይበል እንጅ የአማራ እሴት እንዲከበር ከማንኛችንም በላይ እየሰራ ያለ ታጋይ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።ብዙዎቻችን ዛሬ የምንጮህለትን አማራነት በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ብንፈልገው ቴዲ ካሴት ውስጥ አለ።ቴዲ አስተሳሰብ ውስጥ አለ።የእርሱዋ ኢትዮጵያ መኖር የማትችለው ህወሃታውያንና ኦነጋዊያን ጋር ብቻ ነው።
ስለ ቴዲ መዘርዘር ለእኔ ጥሩ ስሜት አይሰጠኝም።ምክንያቱም እርሱ ከእኔ አገላለፅም በላይ ነውና።የሆነው ሆኖ ግን ቴዲ በአዲሱ አልበሙ ላይ አማራን በስም ልክ እንደ ሌሎች አለመጥቀሱን በወቅቱም አሁንም ቅሬታ እንዳለኝ ሳልገልፅ አላልፍም።
በሰሞኑ ኮንሰርት ላይ ደግሞ በመፈቀዱ ከተደሱት ውስጥ አንዱ ነኝ።የቴዲን ጉዞ ከተራ ዘፈን ጋር ሳይሆን ከፖለቲካዊ ጥቅም አንፃር ነው የማየው።የመጀመሪያው ህወሃት አዲስ አበባ ላይ የከለከለችውን ዘፋኝ ባህር ዳር ላይ ስትፈቅድለት የአይደፈሬነት የአማራን ስነ ልቦና መላበስን ማሳያ ነው።አማራው እምቢ ባይ ነው።ቴዲን ባህር ዳር ላይ ኮንሰርት እንዲያዘጋጅ ሲታሰብ የብአዴን አመራሮች እንኳን ተከፋፍለው እንደነበር ይታወቃል።የተቃወሙት ሰዎች ህወሃትን ለማስደሰት የሚጥሩ አመራሮች የነፍጠኛ አቀንቃኝ ነው ሲሉ ነው የከሰሱት።ኮንሰርቱ ግን ከአማራ ህዝብ የታሪክ ወዳጅነትና መሪዎቻችን ተካዱ ጥያቄ ጋር ተዳምሮ ትክክል ነው ባይ ነኝ።
እስከሚገባኝ አማራ ኢትዮጵያን አልጠላም።የሚጠላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የጠላን ነው።ይህ ሀይል ጉልበቱ ስለደረጀ ያንን ሀይል በኢትዮጵያዊነት የትግል ስልት ማሸነፍ አይቻልም የሚል ነው።አማራው ሌላው የማይወደው ኢትዮጵያን ዳግም ብቻህን ተሸከም መባልን ነው።
ሁለተኛው ጉዳይ የአማራ ህዝብ ስለ ታሪኩ ሲዘፈንለት የሚወድ ታሪክ ወዳድ ህዝብ ነውና ራሱን ቢያወሰድው ይወዳል እንጅ አይጠላም የሚለው ነው።ስለ ጎጃም፣ ስለ ወሎ፣ሸዋ፣ ጎንደር እና ታሪካቸው በ100ሺህ ህዝብ ፊት ከበሮ ቢደለቅ ልቡ ሀሴት ይሞላል።
ይህንን ተትከሎ የኮንስረቱን ጥቅም በአጭሩ ላስቀምጥ።
1.ቴዲ ስለ እውነተኛዋ ኢትዮጵያ ከልቡ ይቆረቆራል
2.በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ስለሚገኘው የአማራ እሴት ባህል ወግ ያቀነቅናል
3.የነፃነት ታጋይ ነው።
4.ስለነገስታቶች እና ስለእነርሱ ገድል ሲዘፍን የአማራን ታሪክም እያወደሰ ነው።ስለምኒልክ፣ ቴዎድሮስ፣ ፍቅር እስከመቃብር፣…
5.በፀረ ኢትዮጵያውያን የነፍጠኛ ወኪል እየተባለ ይጠላል
6.በእናቴ አማራ ነኝ ብሎ ተናግሯል።ይህ ከጎንደሬና ጎጃሜ ከሚለው በትንሹ ይለያል
7.ሌላ ቦታ ስለተከለከለ እኛ ጋር መዝፈኑ ጥሩ ነው።
8.ህዝቡን ለማስተባበርም ይጠቅማል
9.የአማራ ትግል አንዱ የተካደውንና እንዲጠፋ የሚፈለገውን የእኛ ታሪክ ማስከበርና ማስመለስ ነው።ቴዲም በዚህ ዘንድ እየሰራልን ነው።
10.አማራ ዘፋኝ በሌለበት/ውስን በሆነበት እርሱን ብቻ ስለአማራ ዝፈን ማለት ትክክል አይደለም
11.ለከተማውና አካባቢው ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አለው
12.ብአዴን ከህወሃት ጥገኝነት ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት ማሳያ አንዱ አካል ነው
13.ህዝቡ ከመንግስትም በላይ ይወደዋል
14.ቴዲ አማራ ምድር በኢንቨስትመንት አይኑን እንዲገልጥም በር ይከፍታል።
2.በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ስለሚገኘው የአማራ እሴት ባህል ወግ ያቀነቅናል
3.የነፃነት ታጋይ ነው።
4.ስለነገስታቶች እና ስለእነርሱ ገድል ሲዘፍን የአማራን ታሪክም እያወደሰ ነው።ስለምኒልክ፣ ቴዎድሮስ፣ ፍቅር እስከመቃብር፣…
5.በፀረ ኢትዮጵያውያን የነፍጠኛ ወኪል እየተባለ ይጠላል
6.በእናቴ አማራ ነኝ ብሎ ተናግሯል።ይህ ከጎንደሬና ጎጃሜ ከሚለው በትንሹ ይለያል
7.ሌላ ቦታ ስለተከለከለ እኛ ጋር መዝፈኑ ጥሩ ነው።
8.ህዝቡን ለማስተባበርም ይጠቅማል
9.የአማራ ትግል አንዱ የተካደውንና እንዲጠፋ የሚፈለገውን የእኛ ታሪክ ማስከበርና ማስመለስ ነው።ቴዲም በዚህ ዘንድ እየሰራልን ነው።
10.አማራ ዘፋኝ በሌለበት/ውስን በሆነበት እርሱን ብቻ ስለአማራ ዝፈን ማለት ትክክል አይደለም
11.ለከተማውና አካባቢው ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አለው
12.ብአዴን ከህወሃት ጥገኝነት ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት ማሳያ አንዱ አካል ነው
13.ህዝቡ ከመንግስትም በላይ ይወደዋል
14.ቴዲ አማራ ምድር በኢንቨስትመንት አይኑን እንዲገልጥም በር ይከፍታል።
ሲጠቃለል የአማራ ህዝብም ኢትዮጵያዊ ነውና ቴዲ ስለኢትዮጵያ ቢዘፈን ሊከፋን አይችልም።አማራውስ ለምን ይቀየማል?አማራውን የበደለው እኮ የእኛዋ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ ህወሃት ወለድ ስርዓት ነው።
ብሄርተኝነትን ይጎዳል የሚለው ትርክት ውሃ አያነሳም።እኔ የማምነው ስለአማራነቱ የሚሞት ትውልድን መፍጠር ይቻላል በሚል ነው።አማራነትን ያስታጠቅከው ሰው በዘፈን አይሟሽሽም።ይልቅስ ከዘፈኑ እየመረመረ የሚጠቅመውን ለትግል ግብአት ያውለዋል ባይ ነኝ።መድረኩንም ለመገናኛ ይጠቀምበታል።
ትግላችን ፀረ አማራውን/ ፀረ ኢትዮጵያውን መታገል እንጅ ፀረ ኢትዮጵያ መሆን አይመስለኝም።መሆንም የለበትም።
የቴዲ አፍሮ የባህር ዳር ጉዞ ሰላማዊና የተሳካ ይሆን ዘንድ የአማራ ህዝብ የተለመደ ተግባሩን እንደሚፈፅምም እምነቴ ነው።
ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር ወደፊት!!!

Comments