ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ

ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ
(ዘላለም በላይነህ)

አንዳንዴ የቴዎድሮስ ካሳሁንን ዘፈን አጋነናችሁት የሚል ሰው እሰማለሁ እኔ እየቆየሁ ዘፈኑን ባደመጥሁት ቁጥር እይታዎቹ ይገርሙኛል፡፡
ብዙ ጊዜ ስለ ዘፈኑ ግጥም መራቀቅ እንጅ ስለርዕሱ አስተውለን የማናውቅ ብዙዎቻችን ነን፡፡ ርእስ ሀይል አለው ርእስ አንባቢን አድማጭን የመሳብ ሀቅሙ ከባድ ነው፡፡ ጸሐፊ ግጥሙን ጽፎ ሲጨርስ ርእስ በማጣት የሚያምጥበት ጊዜ ብዙ ነው ፡፡ ለጸሐፊ ከባዱ ነገር ከጽሁፉ ይልቅ ርእሱ ይመስኛል፡፡ ምክንያም የጣፈውን ጽሑፍ ባንድ ቃል ወይም አርፍተ ነገር ማስፍር ነውና ፡፡
ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ
እነዚህን አቻ ቃሎች እስኪ በታየኝ ልክ እንያቸው ፡፡
ፍቅርን ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ስንት ፈግታ ታታሪዋ ንብ ከብዙ ነገሮች ውህድ ፈጥራ በምትቀምመው ማር ሲመስለው - ለፍቅር በሚከፈል መስዕዋትነት ውስጥ ያለውን ሂደት ደግሞ ሰፈፉ ቀልጦ ለብዙዎች ብርሀን በመሆን እራሱን አመድ በሚያደርገው ጣፍ መሰለው ፡፡ ለፍቅር በተከፈለ መስዋዕትነት መቃብር መውረድን ደግሞ ጧፍ ሆኖ ለሌሎች ብርሀን መሆንን ማር ከነደደ በኋላ አመድ ምንም የማይጠቅም ያበቃለት ጉዳይ መሆኑን አመሰጠረበት ፡፡
ለዚህም ነው ቴዎድሮስ ካሳሁን ይችላል የሚሉ ድምጽች የበረከቱት፡፡ እሽሸው ገዳዬ በበዛበት ሰአት እንዲህ በግጥም ጥበብ በሰምና ወርቅ የጎለበተ የሙዚቃን እረቂቅነት የሚያሳይ ዛፋኝ ለምን አናድንቅ! እስኪ አንድ ዘፈን ጥሩልኝ እና ከዚህ የዘፈን ግጥም ከርእሱ እስከ ግጥሙ ተንተን አድርጎ ለውድድር የሚያቀርበው ሰው ይገኝ!!!! የሚችል ሰው የማይወደስባት ሀገር ላይ ቁጭ ብለን እንጅ ቴዎድሮስ ካሳሁን ብሄራዊ ኩራታችን ነው ፡፡ እነሀይሌ ገብረ ስላሴ እነቀነኒሳ በቀለ ሌላም ሌላም አትሌቶቻችን ባንዴራችንን በአለም አደባባይ ከፍ እንዳደረጉት በዚህ ውድድር በበዛበት አለም የሚያመልካቸው የሚዚቃ ኮከቦች በበዙባት አለም የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአለም ደረጃ ከፍ አድርጎ ያሳየን ንጉስ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ያውም ኢትዮጵያ በሚል አልበም ፡፡
ታዋቂነት ካባድ ነው ዝናን ይዞ ለማስቀጠል እጅግ እልህና ታታሪነት ይጠይቃል ፡፡ ይሄ ዘፋኝ ሁሉንም ይዟል ፡፡ እንደዚህ ልጅ በሀገራችን ፓለቲካ ምክንያት ብዙ እንዳይራመድ ማነቆ የሆነበት ግን ማነቆው ያላስቀረው ዘፈኝ የለም፡፡ እሱ ግን እስር ቤት ሆኖም መዝፈኑን አላቆመም ወህኒ ወርዶም ከመቀኜቱ የገታው ችግርና መከራ የለም፡፡ ታሪኩን እና ክብሩን ጠንቅቆ የሚያውቅ ምርጥ ያያቱ ልጅ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ የአያቱ ልጅ የአያቱ ልጅ የምለው አባቴ ሳላልወለደኝ ሳይሆን ኢትዮጵያ ብዙ ጀግኖችን ያየችበት በአያቶቻችን እንጅ ዛሬ ላይ በሚበዘብዟት አባቶቻችን እንዳልሆነ ስለሚሰማኝ ነው አሁን ላይ በመሞትና በመዳን ላይ በመኖርና ባለመኖር ላይ የምትታገለው ኢትዮጵያ በአባቴ ሳይሆን በአያቴ ምሶሶዋ መሰረቷ የቆመ እንደሆነ ስለሚሰማኝ ነው፡፡
ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ ያያቱ ልጅ እያልሁ የምጽፈው፡፡
ብዙ ጊዜ ፍቅር እስከመቃብርን ባሰብሁ ቁጥር ለኔ ገኖ የሚታየኝ ከበዛብህ እና ከሰብለወንጌል ይልቅ ፊታውራሪ መሸሻ ነው ፡፡ አሁን ይህ ታላቅ ዘፋኝ የሰራውን አዲስ የዘፈን ክሊፕ ስመለከት በቃ ፊታውራሪ መሸሻን በህሌናይ እስለው የነበረውን በምናቤ ይመላለስብኝ የነበረውን ወኔውን እንኳን ሳይቀንስ በቃ ገልጾልኛል ፡፡ የእውት አምለሰት ለቴዲ ትገባዋለች በእረግጥ ከአንድ ጀግና ሰው ጀርባ ጀግና ሚስት እንዳለች የሚነገረውን ብሂል እውን ማድረግ የቻለች ምርጥ የቴዲ አፍሮ ሚስት ናት፡፡
እርዥም እድሜና ጤና ለምርጡ ወንድማችን ቴዎድሮስ ካሳሁን!!እና ለባሌቱ ፡፡
(ዘላለም በላይነህ)

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!