********አፄ ምኒሊክና ኢትዮጵያ አፄ ምኒሊክና አደዋ ፋኖስና ብርጭቆዎቹ****
(ዘላለም በላይነህ)
(ዘላለም በላይነህ)
ነጋሪት እየተጎሰመ ሰራዊቱ እየተመመ ሲሄድ ፈርጠም ባሉ እጆች የእናት አገር ሰንደቅ በክብር መሪነት እየተውለበለበ ወደ ድል ገዞ፡፡ ፍቅርና መስዕዋትነትን ጀግንነትን በቀዩ ቀለም ውስጥ እያነበቡ የምድሩ እሾህ እና ፈለግ ሳይበግራቸው ወደ ምድር አድዋ ሲተሙ ማየት ትክክለኛው ኢትዮጵያዊነት ለመሆኑ ድርጊቱ ያስተምረናል፡፡
እንዳሁኑ ትውልድ ለነገር እንጅ ለተግባር የታነፁ ነዳይ ያይደሉ ይልቁንም ዘር ማንዝሬ ሳይሉ ዳር ድንበርን ለመጠበቅ ጠላትን ለመሞገት ወደ ድል የሞት ሽረት ጉዞ……በምርጡ የቁርጥ ቀን ልጅ በአፄ ምኒሊክ እና ለሀገራችን መከታ እና ማጣበቂያ ጭቃዋ ሁነው ባስዋቧት ባስከበሯት ፣ንፋስ እንዳይገባና መሰረቱ እንዳናጋ መከታ በሆኗት ውድ ልጆቿ ፡፡
ከምድሯ ፍሬ ህይወትን የምንጎነጭባት ከውሆቿም ወተት እየጠባን የምታሳድገን ሀገር ፍቅሯ በአጥንትና ስጋ ገብቶ የማይጠፋ እናት ሀገር ኢትዮጵያ….. ህዝቦቿም በትውልድ በቋንቋ መገናኜት ብቻ ያልተወሰነ የኑሮን ደስታና መከራ ባንድነት በመሮር የተሳሰረ ማንነት የገባቸው ስልፍቅሯ ስለክብሯ ስለታሪኳ ብዙ ሆኑላት ብዙ ተሰውተው ታሪክን ለትውልድ አቆዩ፡፡
የፈረንጅ ውሻ ሊነክሰን ከዘመን ዘመን ሲፈታተነን በውስጣችን እየገባ ሲዘርፈን በልጆቿ ደም እና አትንት ዘበኛነት በእግዚብሄር ረዳትነት ኢትዮጵ ኖራለች እዚህም ደርሳለች፡፡ አለምን የገዛችውን ሮምንም በአፄ ምን ይልክ እና በጣይቱ እራስ ቅልነት ድል አድዋ ላይ ድል ተቀዳጅታለች፡፡ ነፍሳቸውን በገነት በክብር በቸርነቱ ያስቀምጥልን እንጅ ሽዎች ወድቀው ለሚሊዮኖች ቀና ማለት መሰረት ሆነውናል ወደ ድል ጉዞ በባዶ እግር አምስት እና ስድስት ወር ገስግሰዋል ፡፡ ክብር አድዋ ላይ ለተሰው ሰማእታት እና ለንጉሳችን አፄ ምንይልክ፡፡
አሁን ግን ከሁሉ የባሰ ትልቅ በሽታ በልባችን እንደመቃብር መዝጊያ ተወሽቆ ይዞን ሰው የሚከብርበት አዕምሮችን በጠባብነት አመለካከት ላሽቆ ወደ እንሰሳዊነት መቀየር ስለጀመርን አለም ያደነቀውን ለአፍሪካ ነፃነት እንደሰንደቅ በኩራት የተሰራውን ሀውልት ለመቀበል የእራስ ምታት ሆኖብን እንኖራለን፡፡ መጥፎ ነገርን እንጅ ትሩ ነገርን ለመዘከር ያልታደልን ምንዱባኖች ሆነናል፡፡
የክፉ ሰው ስሙ ሁልጊዜ መጥፎ እንደሆነ አናውቅምን? ስለምን በጭፍን እተመራን ማንም ትላንት የተወለደ የኔ ቢጤ ወጠጤ ታሪካችንን ለማጥፋት መርዙን እንደባብ ውስጥ ለውስጥ እየሄደ ስለተፋ ስለምን ጭንቅላታችንን በመርዙ እየበከልን ለዛ ሰው የመጥፎ አላማ ስኬት ሜዳ እናደረገዋለን ፡፡
እንደኔ እንደኔ አፃ ሚኒሊክን የሚቃወም ሰው ካለ የእባቡን መርዝ ቀምሶ ለእባቡ መርዝ ጭንቅላቱን፣አስተሳሰቡን እንደፈለገ ይፈነጭበት ዘንድ ያስረከበ ምስኪን ነው ባይ ነኝ፡፡
አፄ ምኒሊክ ይሄን አላደረገም እንጅ ቢያደርግስ እንኳን እንደሌላ የአፍሪካ ሀገሮች ፈረንጅ ለሞራላችን፣ ለክብራችን ሳይጨነቅ እንበፈለገ የጭቃ ውስጥ አይጥ ይመስል ከፈረስ ቆጥሮ እንደፈረስ ለጉሞ ከሚጋልበን አንድነትን ኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ተላብሶ ወደ ድል ጎዳና ያገሰገሰን ምርጥ እና ታሪክ የማረሳው ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን እንዴት ዘንግተን ወደ ጨለማ እናስባለን፡፡
በሌላ በእፍሪካውያን ቀን ጨልሞባቸው በበታችነት ስሜት እየላሸቁ አፍሪካውያን ሰው አይደሉም ናቸው በሚል ክርክር ሲዘባበቱባቸው ባርሴሎና ድረስ እንደ ዝንጀሮ እና ጦጣ ተቆጥረው አፋቸውን ተለጉመው ወተራቸውን ተቆርጠው እርስ በእርስ ግመል ይመስል በሰንሰለት ታስረው እንደ እንስሳ የ አፍሪካ እንስሶች ተብለው ሲጎበኙ እኛ ኢትዮጵውያን ግን በአባቶቻችን መስዕወትነት ቀና ብለን ሄደናል እንሄዳለነም ፡፡
ምንም እንኳ በእናት ጡት ነካሽ አንገታችንን የደፋን ብንመስልም ፡፡ ደጆቿ የማይወድቅ መሰረቶቿ የማነቃነቅ የብረት ምሶሶ እና አቋም የገነባው ነውና ከፊታችን ብርሀን እንዳለ እናውቃለን፡፡
ምክንቱም የደረሰ አዝመራ ውርጭ ባዶ አድርጎት በቀጣዩ አመት ውርጩ አልፎ ሌላ ጥሩ አዝመራ ማምረት ይቻላልና፡፡ ውርጩ የአመቱን ምርት እንጅ መሰረቱን አይደለምና የገረፈው ፡፡
ስለዚህ የሀገሬ ኢትዮጵያ ዉርጩም ርሀቡም አንገታችንን ያስደፋን ከልዋሳ ስርአትም በልጆቿ ደም እና አጥንት ያልፋል ቀዩን የባንዴራ ቀለም እያየን ወደፊት እንሄዳለን ታሪክም ይቀጥላል፡፡
ወደነገሬ ልመልሳችሁና ይህች ወር ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ብሎም ለአፍሪቃውያን ታላቅ ቀን እንደሆነች ልባችን ውቀዋል፡፡
ነጋሪት እየተጎሰመ ሰራዊቱ እየተመመ ሲሄድ ፈርጠም ባሉ እጆች የእናት አገር ሰንደቅ በክብር መሪነት እየተውለበለበ ወደ ድል ገዞ፡፡ ፍቅርና መስዕዋትነትን ጀግንነትን በቀዩ ቀለም ውስጥ እያነበቡ የምድሩ እሾህ እና ፈለግ ሳይበግራቸው ወደ ምድር አደዋ የተመመሙት ጀግኖች በመሬት መድፍ በሰማይ አውሮፕላን የቦንብ ዝናብ እዘነበባቸው እስከመጨረሻው ህቅታ እስከ ህይወት ፍፃሜ ድረስ ተዋደቁ ሞቱ ደማቸው እንደጎርፍ ተናጠ ፣ወንድም ወንድሙን ቀና ብሎ እንዳያይ የሀገር ፍቅር እና ድል ናፍቆት ሬሳ እየረገጡ እሬሳ መስለው ሀገራቸውን ጠበቁ ፡፡ ውድ አንባብያን እውነት እላችኋለሁ የአሁኑ ትውልድ አድዋን እና ንጉስ ምኒሊክን አይደለም መሳደብ እና በመጥፎ ልናነሳቸው ቀርቶ ስለነሱ ለመናከር ክብሩም የለንም፡፡ ሆኖም በተቻለን እና በተሰማን መጠን የወደቁትን የክብር ሰማዕታት እየዘከርን ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችንን ስም እያወሳን ታሪክን አባቶቻችን ለኛ እንዳቆዩልን እኛም ለቀጣዩ እናስቀጥላለን፡፡ምክንያቱም
ወደድንም ጠላንም አፄ ምኒሊክና ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ ፋኖስና ብርጭቆ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያውያን ሙሴም ናቸው፡፡ ውስጥ ለውስጥ እንደ እባብ እየተሸሎከሎኩ ሀገሬን ታሪኳን ከማሱ በኋላ ተዝካር ቢያወጡላት አርባ ቢደግሱ ታሪኳ ከጣፋ ምን አፈር ቢምሱ ምን ይፈይዳል፡፡ እና ውድ አንባብያን
ነጋሪት ጎሰመን ወደ አድዋ ዛሬ ባንጔዝም ዝክራቸውን በየአመቱ እንዘክራለን፡፡ የእነሱን ደም እና አጥንት እሰብን ፈርጠም ባሉ እጆች የእናት አገር ሰንደቅ በክብር መሪነት እየተውለበለበ ወደ ድል ገዞ አድዋ ባንሄድም ባሀሳብ እና በዝክር ሰማእቶቹን በማስታወስ በለንበት ሁነን አድዋን እና ሰማእቶቹን እናስባለን ፡፡ ፍቅርና መስዕዋትነትን ጀግንነትን በቀዩ ቀለም ውስጥ እያነበብን የምድሩ እሾህ እና ፈለግ ሳይበግራቸው ወደ ምድር አደዋ የተመመሙት ጀግኖች በመሬት መድፍ በሰማይ አውሮፕላን የቦንብ ዝናብ እዘነበባቸው እስከመጨረሻው ህቅታ እስከ ህይወት ፍፃሜ ድረስ የተዋደቁትን እየዘከርን አደዋ እና አፄ ምኒሊክ ታሪክ የማይዘነጋቸው ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች ለሀገራችን ፋኖስና ብርችቆ ሆነው በዝክረ መስዕዋትነት በአፍሪካ ይወሳሉ ፡፡ መልካም ቀን
(ዘላለም በላይነህ)
በብዕር አይኖች ላማየትም ሆነ ለማሣየት የሚፈልግ ከታች ያለውን ገፄን ላይክ ትሉ ዘንድ ግብዣየ ነው
....የብእር አይኖች ይከፈቱ
የፀሀፊ እጆች ስራ አይፍቱ/

Comments