**የቱ ነው ሰማዕት****
(ዘላለም በላይነህ)
ማንነት ሲነካ-- ታሪክ ሲጨፈለቅ-- ያልወደዱት ጀግኖች
ሀገር ስትደፈር---- ትኩሱ ደማቸው---- ገነፈለ ወንዶች
የተቆጣ ስሜት--- ከፋላ ደም ጋራ---- በአንድነት ቀይጠው
ሀውልቱን አቆሙ---- በደም ባጥንታቸው፡፡
የአርበኞቹ ገድል---- አድዋ ያየነው ---- ያሳመመው ፈረንጅ
ሊበቀለን መጣ ------በቀሉን ሊወጣ ----ሊገዛን እጅ በእጅ
የግራዚያኒ ----መንፈስ ተቆጥቶ--- ሽንፈቱ ሞርሙሮት
አእላፍ ገደለ--- በሀበሻ ምድር --- ታሪክ አሳምሞት
ባዶዋን ሊያስቀራት ---- ሀገሬን በይፋ
አድማሱን ለማስፋት---- መለከት ሲነፋ
የእማማ ኢትዮጵያ ----- የቁርጥ ቀን ልጆች
በረሀ ሸፈቱ -- እምቢ ላገሬ አሉ---- ተነሱ ደጅ አዝማች
ማንነት ሲነካ--- ታሪክ ሲጨፈለቅ---- ያልወደዱት ጀግኖች
ሀገር ስትደፈር--- ትኩሱ ደማቸው------ ገነፈለ ወንዶች፡፡
የተቆጣ ስሜት --ከፋላ ደም ጋራ ---በአንድነት ቀይጠው
ሀውልቱን አቆሙ-- በደም ባጥንታቸው፡፡
እንዳሁኑ ትውልድ !!!!
በራስ ሜዳ ቆሞ--- ጀግና ነኝ እያለ--- ዘላለም ያይደለ
ከገዛ ማንነት ---ከስርአቱ ጋር---- ተጣልቶ በኖረ
ሰማእት እያለ---- ሰማእት ነን ብሎ -- በባዶ ማንነት ---መለከት ነገረ
እስኪ መልሱልኝ ሰማእቱ ማነው ?
ቂም ያዘለ ፈረንጅ--- በባእድ ማንነት--- ተናዶ ሲመጣ
የሰላሳ ሽ ደም ---- በግራዚኒ ---- እንደ ጁስ ሲጠጣ
እምቢ ለሀገሬ---ሀገሬ እናቴ ናት ብሎ የሸፈተው
ማቄን እና ጨርቁን----- ዞር ብሎ ያላየው
ወይስ!!!
ከወንደሙ ጋራ---- ከአንድ አብራክ በወጣ
በዱድም ቢላዋ---- የሰው ደም በጠጣ ?
በተጨነቀ ቀን----ችግር በገባበት----- በተራበ ጊዜ
ያጎረሰውን እጅ------ እንደገና ዞሮ---በመንከስ አባዜ?
ለኔ ግን ሰማዕተ
ማንነት ሲነካ ---ታሪክ ሲጨፈለቅ--- ያልወደዱት ጀግኖች
ሀገር ስትደፈር --- ውድ ህይወታቸውን--- ለከፈሉ ወንዶች
የተቆጣ ስሜት ---ከፋላ ደም ጋራ-- በአንድነት ቀይጠው
ሀውልቱን ላቆሙ ------ በደም ባጥንታቸው፡፡
ይህ ነው ሰማዕትነት !!!!
በደምና ባጥንት የቆመ ምንነት!!!
ቀጥሉበት--------
(ዘላለም በላይነህ)
የብእር አይኖች ይከፈቱ

Comments