አይኗ በልጆቿ የታወረች ሀገር፣የሚጠቅሟት ልጆቿን መብላት የጀመረች ኢትዮጵያ!


አይኗ በልጆቿ የታወረች ሀገር፣የሚጠቅሟት ልጆቿን መብላት የጀመረች ኢትዮጵያ!
ይህች ታሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ብዙ ደም የተከፈለባት ለብዙ አፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት አለም ፊታቸውን  ወደኢትዮጵያ አድርገው በውስጧ ያሉ ታሪክ ያስቀመጣቸውን ቅርሶቿን  ለመጠቀም ከልጆቿ በተሻለ መልኩ የሚጥሩባት ሀገር ኢትዮጵያ ! አሁን ህዝቧ ሰባዊ መብታቸው እየተደፈረ ባላሰቡት እና ባልጠበቁት መንገድ ወደ ወህኒ ቤት እየተወረወሩ  በህገ መንግስቱ መግደል በስርአት የተደነገገ ይመስል የሰው ሞት የዶሮ ደም የመሰለባት ሀገር! ኢትዮጵያ ! የሰው ልጅ የመናገር መብቱ የታፈነባት  መረጃ በኢንተርኔት የመለዋወጥ መብታቸው በአፍሪካ በአንደኝነት የታፈነባት ሀገር! በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማንሳትም ሆነ ስለመብት መከራከር እንደወንጀል ተቆጥሮ የባርነት ህይወት ልጆቿ የሚኖሩባት ምድር  ፡በእውነት ያሳዝናል ሰሞኑን ባህርዳር ላይ የተሰሩ ወጣቶችን በአንድም በሌላም መልኩ ማህበረሰባዊ ግዴታችንን በምንወጣበት ሰአት አውቃቸዋለሁ፡፡ ምንም አይነት የስነምግባር ችግር የማይታይባቸውና ከኪሳቸው ገንዘባቸውን አውጥተው የሀገርን ስራ ከሌላቸው ከአፋቸው ቀንሰው የሚሯሯጡ ናቸው አሁንም የታሰሩበት መንገድ በየትኛውም መልኩ ቢሆን የመት ጥሰት ነው የሚመለከታቸው ሲቪክ ማህበራትም ሆነ ሌላው አለም አቀፍ ተቋማት ፈጽመው ሊያወግዙት የሚገባ ነገር ነው ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ልጆች በፍጥነት መለቀቅ የለባቸው እና ያለምንም ጥፋት መጎዳት የሌለባቸው መሆኑን ህዝቡ ሊጠይቅና ይፈቱ ዘንድ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል

https://www.facebook.com/zelalembelayne/?timeline_context_item_type=intro_card_work&timeline_context_item_source=100003629901604&pnref=lhc

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!