ስለማንነቱ የሚሞግትን ትውልድ ደንቆሮ ብሎ መሳደብ በሀይማኖታዊውም ሆነ በየትኛውም መንገድ የሀሳብ ልእልና የለውም ከአንድ ትለቅ ሽማግሌ በፐሮፌሰርነት ደረጃ ካለ አዋቂ ነኝ ባይም የሚጠበቅ አይደለም !

ስለማንነቱ የሚሞግትን ትውልድ ደንቆሮ ብሎ መሳደብ በሀይማኖታዊውም ሆነ በየትኛውም መንገድ የሀሳብ ልእልና የለውም ከአንድ ትለቅ ሽማግሌ በፐሮፌሰርነት ደረጃ ካለ አዋቂ ነኝ ባይም የሚጠበቅ አይደለም !
**ዘላለም በላይነህ**
ስለማንነቱ የሚሞግትን ትውልድ ደንቆሮ ብሎ መሳደብ በሀይማኖታዊውም ሆነ በየትኛውም መንገድ የሀሳብ ልእልና የለውም ከአንድ ትለቅ ሽማግሌ በፐሮፌሰርነት ደረጃ ካለ አዋቂ ነኝ ባይም የሚጠበቅ አይደለም !
ማቴዎስ አምስት ሃያሁለት
እኔ ግን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጋባዋል፡፡ ይላል
ፕሮፌሰር መጀመሪያ ይሄንን ተውልድ ባለጌ እና ደንቆሮ ብለው ከመስደብ ይልቅ በትእግስት እና በእውነተኛው መንገድ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ወጣቱን ከስሜታዊነት በጸዳ መልኩ ሀሳብዎን በማስረጃ በመደገፍ ቢያስረዱት የእርስዎንም ክብር ከፍ የሚያደርግ ልዕልና ነበር ፡፡ ስድብን በአውራ ስድብ እየመለሱ እንዴት ከእርስዎ ታላቅነትን ልንማር እንችላን
በአንደበቱ ውስጥ ካለው መጥፎ መዝገብ መጥፎ ነገር እያወጡ መናገር ታላቅን ህዝብንም መዝለፍና መድፈር ነውና ይሄ በየትኛወም መንገድ ባለጌነትን እና አላዋቂነትን እንጅ ታላቅንትን አይገልጽም፡፡የወጣቱን የሀሳብ ተቃርኖ ማስረዳት ቢችሉ እና ፕሮፌሰርነትዎን የእውነት መሆኑን ቢያስመሰክሩ ታላቅ እንልዎታለን ፡፡
የጎሳ፣ የብሔር ወይንም የዘውግ ፖለቲካ ለሀገር ጠንቅ መሆኑን ማሳ ምንገድ ቢያጡ አንድን ታላቅ ህዝብ “የለህም” ብሎ ሙግት ውስጥ መግባት ትክክል አይደለም እርስዎ እንዳት
(ብልግና ከደንቆሮነት ደንቆሮነት ከብልግና ይወለዳል፤ አነዚህ ሰሞኑን የሚንጫጩት ዱሮ አሳዳጊ የበደላቸው ሲባሉ የነበሩ ዛሬ ግን አሳዳጊያቸውን የበደሉ በማያውቁት ነገር ሁሉ ከልክ ያለፈ ኩራት የሚሰማቸው ናቸው፤ እውቀት በየመንገዱ ወድቆ የሚለቃቀም ነገር ይመስላቸዋል፤ እውነት በጫጫታና በማደናበር የሚተከል ይመስላቸዋል፤ እንደዚህ ዓይነቶቹን አንድ ጊዜ አንድ መምህር በቲቪ ሲናገር ፊደላውያን ሲላቸው ሰምቻለሁ፤ ፊደልን በመከራ ተምረው ትምህርት የሚባል ነገር የጨረሱ የሚመስላቸው ናቸው፤ ያሳዝናሉ፤ የወደፊትዋ ኢትዮጵያ ይበልጥ ታሳዝናለች፤ ሆኖም በነዚህ ሰዎች ተስፋ አልቆርጥም! የእነሱው ዓይነት ሰዎች ወይ በገንዘብ፣ ወይ በዱላ ያስተምሯቸዋል፤ ትምህርት የሚገባቸው በነዚያ መንገዶች ብቻ ነው! ወያኔ ሲዘለዝላቸው መቼ ይናገራሉ፤ ምን አፍ አላቸው! )
እስኪ ሌላ ትችትዎን እንመልከት
(ሰለጎሣ ማወቅና መረዳት የፈለጉ በጎሣነት የታወቁ ማኅበረሰቦች እያንዳንዳቸው አባሎቹን ሁሉ የሚያያይዛቸው የጋራ መሪ እንዳላቸው መገንዘብ፣ በዘፈናቸው፣ በስክስታቸው፣ በምግባቸውና በመጠጣቸው፣ በልብሳቸው … መመሳሰል እንዳሉባቸው ማወቅ ይጠቅማል )
ብለዋል ትክክል ሆኖም አሁን አማራ የሚባል ጎሳ በየለም አለ የሚከራከሩት ህዝብ መገንዘብ፣ በዘፈናቸው፣ በስክስታቸው፣ በምግባቸውና በመጠጣቸው፣ በልብሳቸው አይመሳሰሉም ብለው ያምናሉ ፡፡ ሁሉም አማራ ነን የሚሉ እርስዎ በጭፍን አይደላችሁም የሚሏቸው ሻዋ ጎጃም ጎንደርና ወሎ በባህል ከሚለያያቸው እኮ የሚያመሳስላቸው ነው የሚበልጠው ፡፡ ጥቃቅን ልዩነት ካሉ እኮ በጎሣነት የታወቁ ማኅበረሰቦች ከሚባሉት ጉራጌን ላንሳ ቸሃ ፣ኧዣ ፣ምወሕር፣ ጉራ፣ ጐማረ ፣እነሞር ፣ግየታ ይባላሉ እነዚህ የጋራ የሆነ አንድ የጎሳ ስም አላቸው‹‹ ጌራጌ ››ሆኖም ግን በውስጣቸው በጣም ብዙ የሚያመሳስሏቸው እንዳለ ሁሉ የሚለያያቸውም አለ ለምሳሌ የቋንቋ ልዩነታቸው ጎልቶ ይታያል
ስለዚህ ስለጎሳ ሰውን እውቀት አልባ ብለው የኮነኑበት መንገድ እጅግ ያፈነገጠ እና የእርስዎን ያለመረዳት የገለጡበት ነው
ለእውቀትና ለእውነት ደንታ የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውን፣ ሌላው ቀርቶ የተጻፈውን እንኳን በትክክል ሳያነቡና ሳይገባቸው እንደየበር ላይ ውሻ የሚጮሁ መሆናቸውን ለማሳየት ሁለት ማስረጃዎችን አቀርባለሁ፤ አንደኛ አማራ የለም አላልሁም የትም ቦታ አላልሁም፤ ያልሁት አማራ የሚባል ጎሣ የለም ነው፤ በዚህ ትርጉሙ ድርጅቶች ተቋቁመው ሲፈልጉት ሁለት ዓመታቸው ነው፤ ገና አላገኙትም፤ አማራ የሚለውን ቃልም ሆነ ጎሣ የሚለውን ቃል በትክክል የማያውቁት ፊደላውያን ጩኸታቸው የብዙ ሰዎችን ጆሮ ስለጎዳ ለማብራራት ወሰንሁ፤ የኔ የግል አስተያየት እንዳልሆነም ለማሳየት ታላላቅ ሊቃውንትን በአስረጂነት ደርድሬ ነበር፤ ስሕተቴ ሊቃውንቱን ከድንጋይ ራሶች ጋር ለማስተዋወቅ መሞከሬ ነው፤ አይለምደኝም፤ የለመዳችኋቸው እንደለመዳችሁት ያስተምሯችኋል፡፡
ሌላው ፕሮፌሰር
ሁለተኛ፣ አማራ ለሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም ለመስጠት አልሞከርሁም፤ ግን ሊቃውንቱ ከጻፉት ውስጥ ይነበብ ነበር፤ ከድንጋይ ራሶቹ አንድም የተጠቀሱትን አንብቦ የተረዳ የለም፤ ያሳዝናል፤
ብለዋል እስኪ ከሊቃውንቱ መካከል አንዱን እንጥቀስ
የንቡረ እድን መዝገብ እንደ ማጣቀሻ ወስደው አማራ የሚባል የለም የሚለውን የእልህ አስተሳሰብ ለማጽናት ሲጠቀሙበት እና እንደመከራከሪያ ሲያቀርቡ
ንቡረ እድ ኤርምያስ ዐማራ ማለት ‹‹በነጻነት የመኖርን ጸጋ ከእግዚአብሔር በቃል ኪዳን ላገኘው ከየነገዱና ከየጎሣው በጋብቻ፣ በልደትና በኅብረተሰባዊነት ተዋህዶ አንድ ፍጹም ሙሉ ዘር ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ የኅብረ ነገድ መታወቂያ ነው ይላል፡፡
‹‹አንድ ፍጹም ሙሉ ዘር ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ›› ይሄ ቃል ይሰመርልኝ ! አንድ ሙሉ ንጹህ ህዝብ ካለ ህብረ ብሄራዊነት ጋር የሚጻረስ ቃል ነው ህብረ ብሄራዊነት ማለት ብዙ አይነት ህዝቦች በአንድነት ተከባብሮ በህብር የሚኖር ህዝብ ሲሆን አንድ ፍጹም ሙሉ ዘር የሆነ ካለ ግን ይሄ ህዝብ ህብረ ብሄራዊ ሊሆን አይችልም ቃሉም ይጋጫል ፡፡ ከየነገዱ ከየጎሳውም እንኳ የተገኜ ቢሆን ይሄ ህዝብ በመጨረሻ አማራ የሚለውን ትርጉም ሊይዝ የሚችለው እና ቃሉ ሊጽና የሚችለው ከየነገዱ የተገኜው ህዝብ አንድ የጸና ሙሉ ሲሆን ነው ስለዚህ አማራ ከየነገዱም የተገኜ ብሎ ይበለው ምንም ይበለው አንድ ንጹህ ሙሉ ህዝብ ነው ይሄ ቃል ደግሞ የአማራን መኖር በደንብ በአጽንኦት ያጸና ነው ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከላይ የዘረዘራቸው ማጣቀሻዎች የአማራነትን ክብር ከፍ የሚያደርጉ እና ጎልቶ የወጣ ማንነት ለው ህዝብ መሆኑን ያጽናሉ፡፡
አሁን አማራ የሚባል ጎሳ አለ ያሉት ወይስ የለም ያለው ነው እርስዎ እንዳሉት ድንጋይ እራስ የሆኑት ፡፡ ቢያውቁትስ ድንጋይ መሰረት የሆነውን ሀውልት መገንቢያ እንጅ መስደቢያ ባላደረጉት ነበር፡፡
ስለዚህ ፕሮፌሰር እርስዎ አማራ የሚባል የለም ብለው ማሰብዎ እጅግ ከእውነታ የራቀ ምክንያተ ቢስ መሆኑን ተገንዝበው ህዝቡን ደፍረዋልና ይቅታ መጠየቅ አለበዎት!
ፕሮፌሰር ለምን ተመካ ብላችሁ እንቧ ከረዬ ምትሉ ሁሉ እስኪ የእሳቸውን መከላከያ ሀሳብ ተረጋጋ መንፈስ ማቀረብ ይቻላል መሳደብ ያላማወቅ መልክት ነው፡፡
(ዘላለም በላይነህ)

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!