አብይ ፍሬውን ለቀማ
ዘራቸውን ይተክላሉ አብይ ፍሬውን ለቀማ
ነፋስ የገባው ገለባ ፍሬ አልባ ዋግ የበላው መሆኑን ወገን ሳይሰማ
ምን አይንት መስገብገብ ነው ይሄ ነው እንዴ መሰረቱ
ዘሩን በደንብ ሳይተክሉ በፍሬው ላይ መሟገቱ
ውሃ ሳያዘጋጁ ፈሰሱን ሳይሸነሽኑ እርከኑን ሳይደለድሉ
የነገ ተስፋው ቀጭጮ መንምኖ እያያችሁት
ገና ከእንጭጩ ቁጭ ብሎ ከፍሬው ተመኛችሁት
በሉ እንግዲህ እንየው የዘመናት ፉጨቱን
አራት ምሶሶ ተተክሎ መቆም ከተሳናችሁ
ያው ለምስል ካልሆነ ምኑን kፌሬው በላችሁ፡፡
Comments