መንግስታችን 70000000(ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ለሎቢስ የጠበቆች ኩባንያ እንደከፈለ ከወደ ቪኦኤ

መንግስታችን 70000000(ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ለሎቢስ የጠበቆች ኩባንያ እንደከፈለ ከወደ ቪኦኤ

ኤች አር 128ን እንዲቀር ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ሎቢስ ለሚባል የጠበቆች ኩባን ያ በወር 41 ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ሽ ብር ለተከተታይ አስራ ስምንት ወራት እየከፈለ ሲከራከር ቢቆይም እንኳን ወጣቶቹ ለቆሙበት አላማ ፍሬ እንዲያፈራ እጅግ ስለታገሉ ማሸነፍ ችለዋል ፡፡  በምግብ እና በኢንፍራስትራክቸር ችግር በምትሰቃይ ሀገር ውስጥ ሰው በድርቅ ሰበብ የረሀብ ጦር እየገረፋቸው  የኛ መንግስት ይሄንን ያክል ገንዘብ እና የሀገር ሀብት እንዲህ ያፈስሳል፡፡
እንዲህ ነው እንግዲህ ለህዝብ ማሰብ

ውሣኔው እንዳይፀድቅ ለማስተጓጎል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰባት መቶ ሚሊየን ብር በላይ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ማውጣቱን ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ተናገሩ፡፡
በካሊፎርኒያ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ሳንበርናርዲኖ የሕግ ፕሮፌሰሩ ዓለማየሁ ገብረማርያም ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባያደረጉት ቃለምልልስ ኤችአር128 የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እርምጃዎችን ወደ መውሰድ እንዲያመራ የሚያደርገው ከሆነ በግለሰቦች ላይ ሊያነጣጥር እንደሚችልና በመብቶች ረገጣዎች ላይ እጃቸው አለ የሚባሉ ሰዎች ከታወቁ የአሜሪካ መንግሥት አሁንም ቢሆን ተግባራዊ በሆነው ማግኒትስኪ ሕግ መሠረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ኤችአር128 ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ናቸው የሚባሉ ለውጦችን ያደናቅፋሉ ብለው እንደማያስቡና እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከያዟቸውና እያንፀባረቋቸው ካሉ አቋሞች ጋር የሚደጋገፉ ናቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ አመልክተዋል።
‘ኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ አጋርና የአካባቢዋም የምጣኔ ኃብት ዕድገት፣ የሰላምና የፀጥታ መሪ መሆኗን ብንገነዘብም አልለቃት ያለው የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎቿ፤ በሲቪሎች ላይ በመንግሥቷ የሚካሄድ ሁከቷ፤ የጋዜጠኛነት ነፃነቶችን ማፈኗ፤ በዴሞክራሲያዊ መርኆች ጋር ፊትለፊት በሚጣረስ መንገድ ላይ መቆሟ፤ ሕገመንግሥቷን መጣሷ ያንን ሁሉ ከንቱ ያደርገዋል’ - ይላል የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን ያፀደቀው የውሣኔ ሰነድ 128።

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!