ዶክተር አብይ አህመድ ወደ አማራ ህዝብ ከመሄዱ በፊት በደንብ መዘጋጀት የሚገባው ነገር መሆኑን ማጤን እጅግ መልካም ነው !
ዶክተር አብይ አህመድ ወደ አማራ ህዝብ ከመሄዱ በፊት በደንብ መዘጋጀት የሚገባው ነገር መሆኑን ማጤን እጅግ መልካም ነው !
ይሄ ህዝብ በአፍ እና በወሬ ካሰለቹት ብዙ አሰርት አመታት አልፎታል አሁን ወሬን ሰንቆ ቀቢጽ ተስፋን ቋጥሮ ይሄን ቦታ መርገጥ ህዝቡን መናቅ እንደሆነ ሊገነዘብ ገባል
፡፡ ብዙ የብዙ ብዙ ያልተመለሰላቸው ጥያቄዎች ሲደመር የብዙ ሚሊዮን ደም ሀዘን በሰፈነበት ከተማ አውርቶ መመለስ ከባድ አደጋ ነው!
አማራ እጅግ የግፍ ግፍ የተፈጸመበት አገር ነው! ያም ሆነ ይህ ለመመለስ መዘጋጀት ያለበት ጉዳይ ፡
1ኛ የህልውናችንን ጉዳይ ማስከበር ወንጀል አለመሆኑን እና በነጻነት ለህልውናችን(ለአማራነታችን)
መቆም እንደምንችል በተግባር ሲያሳየን
2ኛ የተዘረፉ ባህሎቻችን ቅርሶቻችን እና የአባቶቻችን
ባድማ የሆኑት መተከል ፣ወልቃይት ጠገዴ ፣ራያ፣ እና ሌሎቹም
3ኛ አዲስ አበባ ታሪካዊ ባለይዞታነቷ የኦሮምያ ነውና ለኦሮምያ ልዩ ጥቅም የሚለውን
ተረት ተረት አቁሞ የአማራ ታሪካዊ ቦታ ከመሆኑ አንጻር ማንም ከአማራ ህዝብ የተለዬ ልዩ ጥቅም ትክክል እንዳይደለ ሲያረጋግጥ
4ኛ በአማራነታቸው የተሰየፉ እና ለመብታቸው ስለታገሉ ስለማንነታቸው ስለታገሉ ወህኒ
ቤት ተዘፍቀው የሚኖሩ አማሮች አንድም ሳይቀር መፍታት ከቻለ ፡፡
5ኛ በአማራ ክልል ውስጥ ሆነው በኢንቨስተር ስም ህዝቡን ለባርነት የዳረጉ ድርጅቶችን
ማስቆም ሲችል እና የህዝቡን ተጠቃሚነት ሲረጋግጥ(ብር እርሻ፣አየሁ እርሻ እና ሌሎቹም)
6ኛ ታሪካዊ ቅርሳችን ጭስ አባይ ወደነበረበት ተመልሶ ታሪካዊ ይዘቱን እንደጠበቅ
ለሀይል ምንጭነት ማዋል ሲችል!
7ኛ ለዘመናት በመብራት እጦት የሚደናበሩ ከተሞች ተጠቃሚነትን ሲችልና መንገዶች
በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሰሩ ሲያደርግ
8ኛ በዛፍ ስር የሚማሩ የአማራ ተማሮች ቤት ውስጥ መማር ሲችሉ……..
9ኛ በተለያየ ጊዜ በአካባቢያቸው ለም መሬት እያለ እየተፈናቀሉ በበረሀ ለተበተኑ
የአማራ ልጆች ካሳ ክሶ ወደነበሩበት መመለስ ሲችል (ለምሳሌ የአየሁ እርሻ ልማት ማህበረሰቦች)
እና ሌሎቹም ናቸው ከዚህ በዘለለ ግን ዝም ብሎ መለፍለፉ ትርጉም አልባ እና ህዝብን
ንቀት ነው! ለአማራ ህዝብ ኢትዮጵዊነትንና አንድነትን መስበክ ለአንበሳ ስጋ መብላት እንደማስተማር ነውና ጠንቀቅ ይበል !
https://www.facebook.com/gojam.mereja/

Comments