ምነው በወልድያ ሲሆን እጃቸው ለቅጣት ፈጠና ሸም ነው!

ምነው በወልድያ ሲሆን እጃቸው ለቅጣት ፈጠና ሸም ነው!



በአንድ ሀገር ውስጥ ያለ ህግ እውነተኛ እና አድሎአዊነት ከሌለው አንድ አይነት ይሆናል ፡፡ አሁን በወልድያ ከነማ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሁሉንም የእስፖርት ቤተሰብ የሚያበሳጭ ነው ምክንያቱም ድርጊቱ ትክክል ባይሆንም እንኳ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ክለቦች ውስጥ እጅግ የመረረ የጥል ጊዜ ማለትም በደርቢ ጨዋታም ሆነ በሌሎቹ ተስተናግደዋል፡፡በወልዲያ ላይ የተላለፈው ቅጣት ሌላ አላማ ያለው በሚመስል መልኩ ነው እንደእኔ አመለካከት ደግሞ ሆን ተብሎ ክለቡን ለማፍረስ የተደረገ ሴራ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ የመቀሌ ደጋፊዎች የባህርዳር ከነማን ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ሲደበድቧቸው ከሜዳ ውስጥ አፍነው እንዳይወጡ ሲያደርጓቸው ለምን አልተቀጡም? የውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ደጋፊዎች የፋሲልን ደጋፊዎች ሲደበድቧቸው ለምን አልተቀጡም? የቡና እና የጊዮርጊስ ደጋፊዎች ለዘመናት ሲደባደቡ ለምን አልተቀጡም፡፡ ሁለቱ ደርቢ የትግራይ ክለቦች ማለትም የመቀሌ እና የውልዋሎ ደጋፊዎች ተደባድበው ስንት ደም ሲፋስስ ንብረትም ሆነ ሌሎች ጉዳቶች ሲከሰቱ ለምን አልተቀጡም ፡፡ አሁን ወልዲያ ላይ ሲደርስ እጃቸው የዘረመው ፡፡ ይሄ አውቆ የአማራ ክለቦች እቆጠቆጡ እና ብቅ ብቅ እያሉ በመምጣታቸው አይናቸው ደም ስለለበሰ ጉዟችንን ለማቀጨጭ የተገመደ ሴራ ስለሆነ ሁሉም አማራ ወላ የፋሲል ሆነ የወልድያ ደብረብርሀን ሆነ የጣናው ሞገድ ሊቃወመው እና የወልድያቅጣት እንዲነሳ የማድረግ ሀላፊነት አለበት! ስትለፈልፉ እና ስትቀላውጡ የነበራችሁ ጋዜጠኛች ዛሬ ነው እንዴ በኢትዮጵያ ክለቦች ውስጥ ግጭት የተጀመረው ያኔ የት ነበራችሁ ፡፡ እውነተኛ የሙያ ፍቅር ቢኖራችሁ ኖሮ ከብዙ አንግል ትመለከቱ ነበር ፡፡ ይሄን ስል ጥሉን መደገፌ አይደለም ህጉን እና ቅጣቱን ግን አብዝቼ እቃወማለሁ ፡፡ ህግ ከተባለ ለሁሉም እኩል ነው፡፡ እራሱን ማደራጀት ያቃጠው ፌደሬሽን እድሉን አገኜሁ ብሎ እጁን ሲያስረዝም ዝም ማለት እውነት ስህተት ነው፡፡
1. ወልድያ በዚህ አመት የሚያደርጋቸዉ ዉድድሮች በሙሉ ከ500 ኪ. ሜ ርቀት በላይ እንዲያደርግ
2. 250 000 ብር ቅጣት
3. የሸህ አላሙዲ ስታዲየም በዚህ አመት ምንም አይነት ዉድድር እንዳያደርግ
4. ብሩክ ቃልቦሬ 1 አመት እና 10 ሺህ ብር
5. አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደ ጊዮርጊስ አንድ አመት እና 20 ሺህ ብር ተቀጥተዋል

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!