የህብረተሰቡ ሁነኛ ግፊት የፈጠራቸው ጀግናዎች
የህብረተሰቡ ሁነኛ ግፊት የፈጠራቸው ጀግናዎች
---------------------------------------------------------

የህብረተሰቡ ሁነኛ ግፊት የፈጠራቸው ጀግናዎች ማህበረሱን እንደከለላ ተጠቅመው መስዋዕት ለመሆን አይዳዱም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች የህብረተሰብ ችግርን ለመፍታት ለህብረተሰቡ ወግኖ መንግስትን መቃወም ማለት እጅግ መራራ እና እራስን እንደይስሐቅ መስዋዕትነት ማቅረብ ነው ( ሁለቱም በጎ ነገርን እና ታዛዥነትን ያቀፉ ምሳሌዎች ስለሆኑ ነው የተጠቀምሁባቸው)
ብዙዎች፣ በመረጡትና ማህበረሰቤ ተጎድቶበታል፣ እዚህ ላይ ፍትህ ያስፈልጋል፣ ይሄ ማህበረሰብ እኮ እኔን እና መሰሎችን ያስገኜ ነው፣ የሚለው ግዙፍ አመለካከት እንደ ሻማ ባውስጣቸው ሲንቦገቦግ የራስን ጥቅምና እራስን ወደጎን በመተው ለዚህ ግዙፍ እና የተከበረ መህበረሰብ ዘበኛ ይቆማሉ፡፡ እኒህ ሰዎች ደግሞ ‘ኀብረተሰባዊ ጀግኖች’ ናቸው ። ማኅበረሰቡም እንዲህ ላሉት ጀግኖች በግልፅ ሊያጨበጭብ እና ዘበኛ ሊቆምላቸው ይገባል። ምክንያቱም፣ ማኅበረሰቡ ለራሱ የሚከራከሩለትን ሰዎች የማያበረታታና የማያመሰግን፣ እንዲሁም ተገቢውን ክብር ማይሰጥ ከሆነ፣ በጊዜ ሂደት ስለወገናቸው የሚከራከሩ ሰዎች ሊጠፉና ሊነጥፉ ይችላል።
ይህ ደግሞ ለአንድ ሀገር ህልውና ከባድ ዝቅጠት ነው፡፡ ማህበረሰብ ባለው ማህበረሰባዊ አስተምህሮና መስተጋብር ጀግናዎቹን ፈጥሮ እና ቀምሮ ማለፍ ይችላል ፡፡ ሁሉም ነገር ከማህበረሰብ አያመልጥም ከሰማይ በመለኮት ከተሰጠ በስተቀር፡፡
አሁን አሁን የአማራ ወጣቶች ለዘመናት የደረሰባቸውን ግፍና በደል ለመቃወም አፍንግጠው በመውጣት ለህልውናቸው መቆም ሁነኛ ነገራቸው አድርገውታል ፡፡ ይህ ማህበረሰብ በሀይማኖታዊውም ሆነ በአለማዊው ልእልናው ከፍ ያለና ጠንካራ ስነ ልቦና ያለው ማህበረሰብ በመሆኑ ይሄንን ማህበረሰብ ጥያቄዎቹን መልሶ ወደነበረበት ወደፈለገው ለማድረስ ታላቅ ጥንካሬንና እውቀትን የሚጠይቅ ነው፡፡ ይሄንን ለማድረግ ደግሞ የራሱ ልጆች በራሳቸው ማንነት መነሳትና እራሳቸውን አደራጅተው የራሳቸው ጀግኖችን መፍጠር ሁነኛ ነገር ነው፡፡
በዚህ ግዜ ማህበረሰቡ እራሱ የፈጠራቸውን ጀግኖች ጥብቅ ክትትልና ከለላ ከቆመ እጅግ አስፈሪና ተከባሪ ሆነው ቀድመው ለማህበረሰቡ የሚሞቱ ውድና ታሪካቸውን አካባሪ ልጆች መፍጠሩ ቀጣይነት ያለው አብይ ጉዳይ ይሆናል ፡፡
እንደ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየሱስ ያሉት ጀግኖቻችን ያቀጣጠሉት ችቦ አብርቶ አሁን ሁሉንም ግዮናዊያን አዳርሶ አማራኒዝም ሞቨመንትን እያቀጣጠለ ባለበት ሰአት ሁሉም የአማራን ህልውና ከዚያም አልፎ የኢትጵያን መጻኢ እድል ለመወሰን የፈለገ እነዚህን ህዝባዊ ጀግኖች የመጠበቅ እና ሌላ ጀግና የመፍጠር ሀላፊት አለበት፡፡ ሁሉም በመረጠውና በሚመቸዉ በችሎታውና በፍላጎቱ ጀግና መሆን ይችላል ፡፡ አማራነት ታላቅ ማንነት ነው ይህ ህዝብ ለኢትዮጵያ ባለውለታና ፈጣሪ ነው(መስራች) ፡፡ እርሱ በመሰረታት ኢትዮጵያ እርሱ አንገት ደፍቶ የሚሄድበት መንገድ በፍቱም በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
ዘረኛ እና ከፋፋይ በሚል ከአንገት በላይ ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ጀሮ መስጠት እሰፈላጊ ጉዳይ አይደለም ፡፡ ምክንያቱም አመራነትን ማቀንቀን ዘረኛነት ስላልሆነ እነዚህን የአመለካከት እና የትርጉም ችግር ያለባቸው ምንዱባን ብለን እናልፈቸዋለን ፡፡
ውድ ግዮናዉን ሆይ በውስጥህ ያለውን አለመግባባት እየፈታህ እራስህን እንደንስር ነጥቀህ መውጣትና የራስህን ማንነት በራስህ መወሰን ያባቶቻችህን ታሪክመጠበቅና የቀድሞ ታላቅነትህን ማስመለስ ግዴታህ ነውና ፡፡ ወደፊት ሳታፈገፍግ ተራመድ እንራመድ፡፡
ያንተ ድምጽ ያሚያስበረግጋቸው መንፈሶች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ እራሰህን አንድ አድርገህ እርስበእርስህ ተደጋግፈህ እስከሞት ድረስ ወደኋላ እንዳታፈገፍግ ፡፡ አማራ የሰውን ክብር አይነካም የራሱንም አያስነካም የሰውን ማንነት አይዘልፍም ለሚዘልፉትም መድሀኒት አለው ፡፡ በወሬ የተገነባች ሀገር ሳይሆን በተግባር የቆመች ሀገር ይዞ መራመድ አላማችሁ አላማችን ይሁን እላለሁ ፡፡
አማራ ታሪኩን ያድሳል፡፡ ክብር ስለአማራነት እና ስለኢትዮጵያዊነት ለተሰው አባቶቻችን ፡፡

Comments