ዋይ በሉ ሄዳችሁ



አለምነው ይላሉ ሀዘን ቤት አጥልቶ
ዋይ በሉ ሄዳችሁ ተሹሟል በፎቶ
እንደዚህ ነው ወዳጅ አንጀት አርስ ሹመት
በቁሙ የሞተን በሙት ቤት ማስቀመጥ 
አንደበት ሰንብቶ ቤት ከተቀመጠ
የሞተን ለሙታን ቅድሚያ ካልተሰጠ
ሸታዉ አገር ቢያውድ ቢረብሽ ቀየውን
ማን ቤት ይቀመጣል ታቅፎ ሙታንን


Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!