አየሁ እርሻ ልማት ከ13000 ሺህ ሄክታር እንደሚደርስ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
- Get link
- X
- Other Apps
አየሁ እርሻ ልማት ከ13000 ሺህ ሄክታር እንደሚደርስ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
ይህ ድርጅት
ግን ከመንግስት ይዞታ ወቶ ለሜድሮክ ሲሸጥ መንግስት የሸጠው
በ6688 ሄክታር
ለም መሬት
ብቻ ነበር!!
ታዲያ ቀሪው ሄክታር መሬት ከየት መጣ!!?
1ኛ የአርሶ አደሩን የከብት ማሰማሪያ መሬቶች በመቀማት
2ኛ የአርሶ አደር እና ተቋማት የእርሻ መሬቶችን በመቀማት
3ኛ በመንግስት በነበረ ሰአት ወንዝ ዳር ያሉ እና ለተሽከርካሪ ምቹ ያልነበሩ ተራራማ እና ገደላማ ቦታዎችን በእርሻ ልማቱ ተቀጥረው የሚሰሩትና እና የአካባቢው ነዋሪዎች ይጠቀሙበት የነበረባቸውን መሬቶች በመቀማት
አሁንም ድረስ ግን ግብር የሚከፍለው በዚህ ዓመት የከፈለውን የግብር መጠን ማወቅ እንደተቻለው 1,719,641ብር ብቻ ነው :: ይህም ማለት መንግስት እንደሸጠለት በነበረው የሄክታር ይዞታ ብቻ መሆኑ ነው። በአንድ ሄክታር ወደ 257.1234 ብር ማለት ነው::
በነገራችን ላይ አምበር በሚባል ከአየሁ እርሻ ራቅ ያለ ሌላ ቦታ ያሉ እና ምንም ምቹ ሁኔታ በሌለበት ቦታ እጅግ በረሃማ የእርሻ ቦታም አለ። ታዲያ ለቀን ሰራተኛ ከምሳ ጋር ተችሎ 80 ብር እየከፈሉ ያሰራሉ እኩል 251 ብርም በሄክታር ግብር ይከፍላሉ። የአየሁ እርሻ ጋር አወዳድሩት እንግዲህ።
ፍትሀዊ የግብር አጣጣል ነው ወይ? የሚለውን ለመለየት አየሁ ለቀን ሰራተኛ የሚከፈለውን ከ15-20ብር ማየት ብቻ በቂ ነው:: የአምሐራዎቹ የአምበር ግን ከነምሳ 80 ብር ይከፍላሉ። እኩል ግብርም ይጣልባቸዋል።
መነሳት ያለባቸው ጥያቄዎች
1ኛ ይህንን ግብር የጣለው የወረዳ ባለሙያ የቀን ጅቦች አስገድደውት ወይም ልዩ ጥቅም አግኝቶ ካልሆነ ይህንን እንዲህ የ6.1234 ብር ብቻ ልዩነት የተፈጠረበት ግብር በቂ ነው ብሎ ካሰበ ከምን አንፃር እንደሆነ ቢያስረዳን?
2ኛ ድርጅቱ ወደ ግል የዞረው በ1991ዓ.ም ስለሆነ እና በግብር ስርዓታችን የተጭበረበረ ግብር በከፍተኛው ዋጋ ከነወለዱ መክፈል አለበት ስለሚል
ፍትሀዊ ባልሆነው የግብር ሁኔታ እንኳ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ተጭበርብሯል::(ወለዱን ሳይጨምር)
ለ19 ዓመታት ነው የተጭበረበረው። ስለዚህ ቅጣቱ በግምት ቢሰላ ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ይሆናል። በድምሩ ከ50ሚሊየን ብር በላይ መሆኑ ነው::
ይህ ደግሞ የፈረሰውን የድኩና ት/ቤት በህንፃ ለመገንባት እና የአየሁ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃን የቤተሙከራ እና ቤተመፅሀፍ ለማሟላት ከበቂ በላይ ነው:: ስለዚህ ወረዳው ሃብቱን አስመልሶ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ አለበት?
3ኛ አየሁ ከእነ ከፍተሌ ወርቅ ሜዳ እና አምበላ ጋር ክልሉ የፈቀደውን የንዑስ ማዘጋጃ ቤት ያለ አግባብ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተከለከለችው በቀን ጅቦት ተፅዕኖ እንደሆነም ይታወቃል:: ስለሆነም ከተማዋ ቢበዛ 312 ሄክታሩን ስለማትሸፍን። ክልሉ በተፅዕኖም ቢሆን የወሰነውን ውሳኔ የሻረው ለጥፋቱ ማካካሻ ይሆን ዘንድ ይህችን ቦታ ለከተማው ንዑስ ማዘጋጃ ቤት(ለሚቋቋመው) ትቶ ተጨማሪ 6000ሄክታሩን ጨምሮ በተጠና እና ለአምሐራው ባለሀብት እርሻ ልማቱ የሚሰጥበትን መንገድ እንዲመቻች እጠይቃለሁ።
=//=መዝገቡ ማንመክቶ=//=

Comments