ስለአየሁ እርሻ ልማት የጉልበት ብዝበዛ መኖር ስናወራ በልብ ወለድ አይደለም
*መዝገቡ ማንመክቶ ግድግዳ*
ስለአየሁ እርሻ ልማት የጉልበት ብዝበዛ መኖር ስናወራ በልብ ወለድ አይደለም
አየሁ እርሻ ልማት በ1973ዓ.ም. ነበር ከመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት አንዱ በመሆን የተቋቋመው:: ያኔ የቀን ሰራተኛ በ1.9ብር የቀን ክፍያ ይሰሩ ነበር::ታዲያ ይህ ገንዘብ በወር 57ብር መሆኑ ነው::ቤተሰቦቻችን ይነግሩን እንደነበረው ወሩን ሙሉ ከሰሩ ወደ 50ብር ገደማ ይደርሳቸው ነበር::ያኔ በግ እና ፍየል ከ50ሳንቲም እስከ 1.25ብር , 50ኪሎ ጤፍ ከ5-8ብር ,ሌሎች ወጭዎችም እንዲሁ ቀላል እንደነበሩ እና ህብረተሰቡ ደስተኛ ኑሮ ይኖሩ እንደነበር የጊዜውን መለዋወጥ እና አሁን ያጋጠማቸውን የምሽት ስቃይ(በስተርጅና ድህነት)በቁጭት ያጫውቱናል::
በሰማኒያዎቹም በ3.5ብር ሰርተዋል በዘጠናዎቹ መግቢያም 4ብር ደርሶ ነበር::ነገር ግን ህብረተሰቡ ኑሮው እንዳሁኑ ዳገት አልሆነበትም ነበር::ምክንያቱም ከብት በማርባት , እርሻ ልማቱ የማይጠቀማቸውን የወንዝ ዳር እና ተራራማ ቦታዎችን(ለመኪና ምቹ ያልሆኑ መሬቶች)በማረስ እና በአነስተኛ ንግድ በመሰማራት ተጨማሪ ድጎማ ያገኙ ስለነበር ነው::ከ1991ዓ.ም በኋላ የአየሁ እርሻ ልማት አላሙዲ ገዛው ተባለ እና ደምወዙም 5ብር ሆነ::ህብረተሰቡ በወቅቱ አልተከራከረም::ከላይ እንደገለፅኩት ተጨማሪ የገቢ ምንጮች ነበሩት እና::ችግሩ የተፈጠረው ከ1993ዓ.ም በኋላ ነው::የኢንቨስትመንት ህጉ በአሰሪው በኩል ያለው ግዴታ ሳይሆን በሰራተኞች በኩል ያለው መተግበር ጀመረ::
አስቡት መንግስት ለ17ዓመት በእርሻ ልማቱ ክልል ውስጥ ቢሆኑም እንኳ በመኖሪያ ቦታነት ሰጥቷቸው በራሳቸው ገንዘብ እና ጉልበት የገነቡትን ቤት ስፈልግ ነገ አስወጥቸ አባርራችኋለሁ ከብት በግ ፍየል እና ዶሯችሁን ካላጠፋችሁ ተባሉ(አይገርምም በሀገራችን ህግ መሬት የመንግስት ነው መንግስት እንኳ በከተማ ያለን የመኖሪያ ቦታ ከቀማ ትክ እና ተገቢውን ካሳ ሰጥቶ ነው)::
ታዲያ እርሻው ለምን አትሉኝም?...
እራሱ መንግስት ነበራ(የሸሁ አይደለም የምንለው ብዙ ማሳያዎች ስላሉን ነው)
ከዚህ ጊዜ በኋላ መነገድ አይቻልም,ማረስ አይቻልም ከእርሻ ልማቱ የቀን ስራ ውጭ ተከራይቶ ማረስ ከብት ከአካባቢው አርሷደር ማስጠጋት አይቻልም....በቃ አይቻልሞች በጅምላ ተለቀቁ::ከ20ዓመት የደስታ ህይወት ባንዴ ወደ ጨለማ አይገርምም?....
እሽ ይሁን ለምን ተገቢውን ክፍያ ሰጥቶ አቅርቦቶችንም እራሱ አሟልቶ ቤትም ሰርቶ ሰጥቶ እኔ ግዴታየን ተወጥቻለሁ እናንተም ግዴታችሁን ተወጡ ካለያ ሌላ አማራጭ ፈልጉ ማለት ይችል ነበር::ለነገሩ ይህ ቅን እሳቤ ቢኖራቸው ኑሮ ሀገራችን እንዲህ ከድህነት ወለል በታች አትቀመጥም ነበር::
የአየሁ የመብት ተሟጋቾች የተነሱት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር::
ልጆችም እየደረስን ስለነበር በየ አገኘነው አጋጣሚ ለምን ማለት አበዛን?....
ከዛም የቀን ክፍያ ወደ 6ብር አደገ::ይገርማችኋል የአካባቢው ገበሬ ምሳ ችሎ 20ብር ይከፍላል::ታዲያ ለምን አይተውትም አትሉኝም?አይችሉማ?...የኖሩበትን ቤት ጥለው መሄድ አለባቸው::ልጅ አለ ትዳር አለ...እንዴት ይበተናል ከ20ዓመት በኋላ ወደየትስ ይሸሻል?....
ክርክሩ ስለበዛ በሰፈራ ስም አማራጭ በማሳጣት እያፈናቀሉ የማህበረሰቡን የመታገል ሀይል አዳከሙት::ይሁን እንጅ ልጆቻቸው ደርሰን በየ አገኘነው የመንግስት መድረክ ሁሉ መጮህ ጀመርን::የሚገርመው የኛው አመራሮች ችግሩ እንዳለ እያወቁም በሚሰፈርላቸው ድርጎ እኛን ያሸማቅቁናል ይሰድቡናል....ኧረ ስንቱ....
ብቻ በመጠኑም ቢሆን ለውጥ አየን ከ2003ዓ.ም. በኋላ የቀን ክፍያ 12ብር ሆነ::አይ ባርነት ገበሬው እኮ ምሳ ችሎ ከ50 እስከ 60ብር ይከፍል ነበር::አይ እነ ግፍ አይፈሬ....
ለነገሩ የዘከርነው ታቦት ቅዱስ ገብርኤል ዱአ ያደረግንበት መስጊድ ብቻቸውን ጎን ለጎን ቁመው ሳንሞት እንዲህ መግቢያ መውጫ አጥተው ሲቸገሩ አየን::ገና የዚህ የዋህ ህዝብ እንባ እስር ቤት ሲገቡ ያሳየናል::
አሁን ደግሞ እነ ነውር ጌጡ ጥሩ ነገር እንደሰሩ ውል አስይዘው በቀን 24ብር ክፍያ ይቀጥራሉ::አይገርሟችሁም?...ሽሮ እኮ እዛው አየሁ 20ብር ነው?...እንደዚያ ስትሰቃይ ውለህ በቀን አንዴ ብቻ?ከ30ዓመት በላይ የኖሩ ሰዎች ደግሞ በቀን አንዴም አይታሰብም ቤተሰብ አላ...ልጅ ርቦት እያየ በምን አንጀት አንድ ጉራሽስ ይጎረሳል?....
ታዲያ መንግስት በአስቸኳይ መላ ሊያበጅለት ይገባል እላለሁ::

Comments