የግፍ ያለሽ "ጊዜ ለኩሉ


=//=በነቃጥበብ ሽፈራው=//=
የግፍ ያለሽ "ጊዜ ለኩሉ
የአየሁ እርሻ ልማት የማንም ይሁን የማን ብዙ የሚያሳስብ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ለረጅም ዘመናት በነዋሪዉና በወዛደሩ ላይ የሚፈጸመዉ ግፍና በደል ነዉ የሚያሳዝነዉ። እኔ በአየሁ እርሻ ልማት ስኖር የታዘብኩትን ጥቂቱን ለመግለጽ እሞክረሰለሁ።በአየሁ እርሻ ልማት 20 በላይ ንጹህ የዉሀ ምንጭ ከመኖሩም በላይ መሬቱ ለም የሰጠትን ሁሉ
የሚያበቅል ሕብረተሰቡ እጅግ ታማኝና ደግ የሰዉ ንብረት የማይነካ ሌብነትን የሚጠየፍ
ለሀይማኖቱ ጽኑ ቢሆንም ተፈጥሮ የለገሰችዉን ሀብት ተጠቅሞ ሀብት ማፍራት ቀርቶ የአንገቱ ማስገቢያ ደሳሳ ጎጆ ቤት ሰርቶ ከዝናብና ከጸሀይ ቤተሰቡን
እንዲከላከል አይፈቀድለትም። ማጋነን ሳይሆን በምድሯ ያለ ሃቅ ነው። እድሜ ልክ እንደ አብርሃም በድንኳን መገፋት የአየሁ ኗሪና ወዛደር እጣ ፋንታው ነዉ:: ይህ ብቻ አይደለም ግፉ። በቀን የሚከፈለዉ የጉለበት ዋጋው ራሱ እንኳን ቤተሰብ ለማስተዳድር ይቅርና ለአንድ ሰው የረባ ቁርስ እኳን አይሆንም።
የህጻናት ጉልበት እጅጉን የሚበዘበዝበትም ከአየሁ እርሻ ልማት በላይ ሌላ ቦታ ያለ አይመስለኝም። አየሁ አርሻ ልማት ለኗሪውና ለወዛደሩ መብራት አይፈቀድም።የአየሁ እርሻ ልማት ኑዋሪዎች በወዛደርነት የሚሰሩት 99% ከመቶዎሹ የአካባቢዉ ተወላጅ ናቸው። የአየሁ ወዛደር ጉልበቱ እጅግ በወረደ ክፍያ በእርሻ ልማት ባለሃብቶች ተበዝብዞ ሲያልቅ አፈናቅለው
በማያዉቀዉ በርሀ ምንም መሰረተ ልማት ባልተሟላበት ሳይሆን በሌለበት ለወባና ለተለያዩ ተያያዥ በሽታዎች ክፍት ለሆነ ቦታ ሆን ተብሎ በበሽታ እንዲሞቱ አስፍረዋቸዋል።
እኔ እንኳን የማስታውሰዉ አራት ዙር አሳዛኝ ሰፈራዎች ተካሂደዋል። 3ኛው ዙር መፈናቀል የኔም አጣ ፉንታ ደርሶኝ እድሜ ልኬን ያፈራሁትን መኖሪያ ቤቴንና ድርጀቴን ያለህግ አግባብ በእብሪት በዶዘር አፈራርሰውብኝ ለስደት ተዳርጊያለሁ::
የሚያሳዝነዉ የዚህ ግፍ ዋና ተዋናይና አስፈፃሚዎች የገንዛ ወንድሞቻችንና አብሮ አደግ ወገኖቻችን መሆናቸዉ ነዉ።
ሁሌም በየቀኑ የቤቴንና የድርጅቴን ፍርስራሽ ባድማየን ሳይ በዛዉ ልክ የአየሁ ወዛደርና ነዋሪ ግፍና ስቃይ ይታወሰኛል! አሁን ግን ቱታውን ለብዙ አመት የቀንና የለሌት ልብሱ አደርጎ የተቃጠለ በቆሎ በልቶና አብልቶ ከሚያገኛት የቀን ጉልበቱ ዋጋ ቀንሶ ያስተማራቸዉና ያሳደጋቸዉ ወጣቶች የአባቶቻችን ግፍና ስቃይ በአባቶቻችን ይብቃ ከአየሁ ምደር ግፍ ይወገድ በማለት ተባብረዉ ምንም እንኳ ምላሽና መፍትሔ ሰጭ አካል እስካሁን ባይገኝም ድምጻቸዉን አጉልተዉ እየጮኹ ስለሆነ አንድ ቀን በአየሁ ምድር ፍትህ ይገኛል የሚል ተስፋ አለኝ።
"
ጊዜ ለኩሉ"!!
ፍትህ ለአየሁ ነዋሪዎች!


Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!