በቦታው የነበረ ምስክር በውስጥ መስመር የላከው!



በቦታው የነበረ ምስክር በውስጥ መስመር የላከው!
(ሙሉቀን ተስፋው )
ለምን እዉነት አይነገርም፡፡ የኢንጂነር ስመኘዉ በቀለ አሟሟት ለእኛ ለተራዎቹ ግለሰብ ግልፅ የሆነው ለመንግስት እና ለሚዲያ ለመግለፅና ለመዘገብ አስቸጋሪ የሚሆንበት ምክንያት የትም አያደርስም፡፡እኔ በራሴ ያየሁትና የሠማሁት ------------------
1.
ጧት መስቀል አደባባይ ስፖርት የሚሰራ ጓደኛዬ ከጧቱ 1:30 ድረስ ምንም እንዳልነበር ( መኪናዉ?) 
2. 2
00 ቢሮ ስገባ ሌላዋ ጓደኛዬ (ከበቅሎ ቤት በመስቀል አደባባይ ያለፈች) የህዳሴዉ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ሞቷል እያሉ ሠዎች ከበዋል ብላ ደወለችልኝ 
እኔም ወዲያዉኑ በመሄድ 2:30 ደረስኩ :: ስደርስ አንድ ፌደራል ፖሊስ ከጥቀቂት ሰዎች ጋር ከበው ቆመዋል፡፡
እኔ ስደርስ ደም አየፈሠሠ ነበር ሰዉነቱ በጠም ጠቁሯል መኪናውም ተቆልፏል መኪናው ስር ጓንት ወደቋል ደምም አለ ፡፡ፖሊሱም ወዲያው ደወለ፡፡ ብዙ ፖሊስ ሲመጣ እኛንም አባረሩን መኪናዉን ሠብረዉ አስከሬኑ ወጣ፡፡አንድ ስፖርት የሚሠራ ልጅ አይቻለሁ እያለሲየወራ ዝም በል ብለው በፓሊስ መኪና ተወስዷል፡፡ ሌላም የመንገድ ተዳዳሪ ትንሽ ልጅ ያለቅሳል፡፡ ምንሆነህ ብየ ስጠይቀዉ "ትላንት ልብስ ሰጥቶኝ ነበር ዛሬም ጫማ አመጣልሀለሁ ብሎኝ ነበር "አለኝ፡፡በዚህ ሁሉ ግር ግር አስከ 530 ቆይቶ federal police በሚል አምቡላንስ አስከሬኑ ተወስዷል፡፡
እኔን በጣም ያበሣጨኝ ነገር ቢኖር ከዛ በኗላ ሠዉ በደሙ ለይ ሢረማመድ አንድ civil የለበሰ እና የሬድዮ መገናኛ የያዘ ሠዉ ላይ ጮህንበት ለምን ቦታዉ አይከለከልም ስለዉ ደነገጠ አሰፈላጊውን መረጃ ወስደናል በቂ ነዉ ይታወቃል አለኝ፡፡ እኛ ይህ መረጃ ሢኖረን ፖሊሠ ኮሚሽኑ ሲቀባጥር አዘንኩ ለዛም ነዉ ይህን መረጃ የለኩልህ፡፡

********
በተፈጠረው የአናርኪዝም ሥርዓት ከዶ/ ዓቢይ በላይ ተጠያቂ የሚሆን አካል አይታየኝም!

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም ጠሚ ዓቢይን የመግደል ሙከራ ተደረገ፤ መርማሪ ከውጭ መጣና ምርመራው ተጠናቀቀ፡፡ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ቢባልም ታፍኖ ቀረ፡፡ ዛሬ እዚያ ቦታ ላይ ከራሱ የአገሩን ጥቅም አስቀድሞ በሚሠራው ኢንጅነር ስመኘው ላይ ግድያ ተፈጸመ፡፡ ለዚህም ሌላ ኤፍቢአይ ሊገባ ይችላል፤ ነገ ሌለው ይቀጥላል፡፡ አናርኪዝም ይህ ነው፡፡ ሥርዓት አልበኝነት ነገሠ ማለት አገሪቱ እንደገና የሕወሓት ማፍያዎች ሆነች ማለት ነው፡፡
ጠሚው ብዙ ደሳስ የሚሉ ቃላትን ይናገራሉ፡፡ መሬት ላይ ግን በተግባር ዜጎች ይፈናቀላሉ ይገደላሉ፡፡ ወንጀለኞች መቀሌ መሽገዋል እየተባለ ምንም እርምጃ መውሰድ አለመቻል፤ በቃላት ብቻ አስተካክላለሁ የሚሉት ፍልስፍና የትም ድረስ የሚያስጉዝ አይደለም፡፡
በሁለት ቀናት ውስጥ 6 እስር ቤቶች ሲቃጠሉ የአገር ባለውለታዎች በአደባባይ ሲገደሉ ከዚህ በላይ አናርኪዝም የለም፡፡

******
አደራ!!
***
ውድ ወንድማችንን በነብሰ-ገዳዮች ተነጥቀናል፤ የወንድማችን መገደል ሁላችንም ሀዘንና ቁጣ ውስጥ ክትቶናል። በዚህ ምክንያት በዐማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እንደሚደረጉ መረጃዎች እየደረሱን ነው።
የዐማራ ልጆች እንድናስተውል የሚያስፈልገው ቁም-ነገር፣ የወንድማችንን የግፍ ግድያ ለመቃወምና ለማውገዝ ስንወጣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን መሆኑን ነው። አንድም የዐማራ ልጅ መሞት ቀርቶ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም፤ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ራሱንና ወገኑን ነቅቶ መጠበቅ አለበት። ቁጣችንን ያዝ አድርገን ተቃውሟችንና ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እንድናሰማ ይሁን፤ አደራ!!!
ውድ ወንድማችንን ማጣታችን ሳያንስ ሌላ የዐማራ ልጅ ልናጣ አይገባም፤ የእኛ ሞት የጠላቶቻችን ድል ነውና። ራሳችንን ጠብቀን ተቃውሟችንን እናሰማ!!!
#ዐማራ በትግሉ ታሪኩን ያድሳል!!!


Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!