የህዉሀት የበላይነት ይቁም እንዳልነው በቅርብ ቀን የኦህዴድ የበላይነት ይቁም ብለን መሰለፍ መዘጋጀት ይመስለኛል ፡፡
የህዉሀት የበላይነት ይቁም እንዳልነው በቅርብ ቀን የኦህዴድ የበላይነት ይቁም ብለን መሰለፍ መዘጋጀት ይመስለኛል ፡፡
ፈረስን ጋላቢው ካልመራው ልጓሙን አጥብቆ በሚገባው ሰአት ካልለቀቀውና ካልያዘው ግቡን አይመታም ገደልም ገብቶ ብዙ ጉዳት ያደርሳል ፡፡ ይሄንን ስል ምንለማለት ፈልጌ ነው በ1983 ጀምሮ ኢሀዴግ መንበረ መንግስቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ህዝብ የደርግ የሀይል ጫና በዝቶበት ስለነበር ወያኔን እንደ አዲስ ፀሐይ እንደሚያወጣ ጠበቀ በመጀመሪያዎቹ አመታትም ቀስ በቀስ አፉ ቅቤ ልቡ ጩቤ እየሆነ እንደባብ በልቡ እየሄደ ቁልፍ ቁልፍ የስልጣን ቦታዎችን ተቆጣጠረ ከዚያም በኋላ ህዝብን እያደቀቀ ለ27 አመታት ቀለደብን ፡፡
ከላይ ያለውን ለመጥቀስ የፈለግሁት አሁን በዶክተር አብይ ዘመነ ኢህአዴግ መንግስት (ያው የኢሀዴግ ሹመኛ ስለሆነ ሌላ ስም መስጠት ስለማልችል ነው) ከመካከላቸው ወጥቶ ላለፉት ጥቂት ወራት ህዝቡን በደስታ እስኪሰክር ድረስ አድርጓል ሆኖም ግን አሁን ላይ ህዝቡ መስሜት ከመናጥ ወጥቶ ሊመለከተው የሚገባ ጊዜ ይመስለኛል የኢትዮጵያ ህዝብ ደሙን ለሀያሰባት አመት ያፈሰሰው የተሸለ ዶሞክራት አመራር ለማምጣት እንጅ ፣ከወሬ እና ከአፍ ያልዘለለ ኢትዮጵያዊነትን ለማየት አይደለም ፡፡ ስለዚህ አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር ቀስበቀስ አቅጣጫውን እያሳተ ከኢትዮጵያዊነት እየለቀቀ ወደዘረኛነት እያዘነበለ ይገኛል ፡፡
ፕሬዚዳንት
ጠቅላይ ሚንስትር
ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር
መከላከያ ሚንስትር
የአየር ሀይል አዛዥ
ምክትል ኢታማዦር ሹም
የወታደራዊ ኦፕሬሽን አዛዥ
የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ
የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን በጣም ቁልፍ ቁልፍ ስልጣን ለአንድ ብሄር መሰጠቱ ምን ያህል ተገቢ እንዳልሆነ አገነዘባለሁ፡፡
መችም ኢትዮጵያዊነትን የሚዘምር መሪ ይሄንን ማድረግ ተገቢ አይደለም ሁሉም ይሄ ነገር በዚህ ከቀጠለ ሌላ ሀያ ሰባት አመት ከመነ እነትና ወደ ዘመነ እንትና ተሸጋግረን ሌላ የደም ማእብል ሊያፋስስ የሚችል ይመስለኛል ፡፡ ይሄ ደግሞ ካሁኑ ልጓም ሊበጅለት የሚገባና ተገቢ ያልሆነ ነው ሁሉም ኢትዮጵያን ናፋቂ ኦሮሞውም ሆነ አመራው ሌላውም ሌላውም ሊገታው እና ሊያስተካክልው የሚገባ ጉዳይ ነው
ሙላቱ ተሾመ~ ፕሬዚደንት
2~ አቢይ አህመድ~ ጠቅላይ ሚኒስትር
3~ ወርቅነህ ገበየሁ~ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
4~ሞቱማ መቃሳ ~ መከላከያ ሚኒስትር
5~ ጌታሁን መኩሪያ ኩማ~ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር።
6~ ኡመር ሁሴን ~ በሚኒስትር መአረግ የገቢዎች ዳይሬክተር።
7~ብርሃኑ ፀጋዬ ~ ጠቅላይ አቃቢ ህግ
8~ ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ~ የአየር ሀይል አዛዥ ።
9~ ብርጋዴር ጀኔራል ደግፌ ቤዲ ~ የአአ ፖሊስ አዛዥ
10~ ስለሽ በቀለ ~ የውሃ፣ የመስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ።
11~ በቀለ ጀኔራል ቡላዶ ~ የሜቴክ ዳይሬክተር
12~ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ~ መከላከያ ሚኒስትር ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ።
13~ ደመላሽ ገ/ሚካኤል ~ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ።
14~ ታከለ ኡማ ~ የአዲስአበባ ከንቲባ ።
የህዉሀት የበላይነት ይቁም እንዳልነው በቅርብ ቀን የኦህዴድ የበላይነት ይቁም ብለን መሰለፍ መዘጋጀት ይመስለኛል ፡፡
ስለዚህ ህዝብ ከስሜት እና በመንጋ ከመነዳት ወጥቶ ልጓም ሊያስተካክል ይገባል
በአዴን አሁንም እንቅልፍ ላይ ስለሆነ እንዳትቀሰቅሱት
(ዘላለም በላይነህ)

Comments