ለኢንጅነሩ ግድያ ከእነ ክንፈ ዳኘው ውጭ ሌላ ሀይልን መጠራጠር ከባድ ይመስለኛል

ለኢንጅነሩ ግድያ ከእነ ክንፈ ዳኘው ውጭ ሌላ ሀይልን መጠራጠር ከባድ ይመስለኛል



የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ #ከሳሊኒ ኮንስትራክሽንና ከብረታትብረት ኢንጅነሪንግ ሃላፊው (የቀድሞው) ክንፈ ዳኘው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አመላካች መረጃዎች እየወጡ ነው።
ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ባለሙያ ብቻ ሳይሆን ፖለቲከኛም ጭምር ሆኖ ብዙ ጉዳዮችን አፍኖ ይሰራ እንደነበር ለመናገር የውስጥ አዋቂ መሆን አይጠይቅም።ሌብነት ባይከላከል እንኳን ሌቦችን አያውቅም ወይም ሲሰርቁ አያይም ማለት አይደለም።ሲሰርቁ ብቻ ሳይሆን ሲጣሉም ጭምር ያውቃል።ፕሮጀክቱ ደግሞ የሀገሪቱ የአንድ ዓመት ሙሉ በጀት ይፈስበታል ተብሎ የሚታሰብ 80/90 ቢሊዮን ፕሮጀክት ነው።የእነ ክንፈ ዳኘው ብረታብረት ኢንጅነሪንግ ብዙ ገንዘብ የተበጀተለት ሲሆን ስራውን ሳይሰራም ገንዘቡ ወጭ ተደርጎለታል።
የአባይ ግድብ ስራ በጣሊያኑ #ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ዋና ተቋራጭነትና በመከላከያ/ብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ Sub contractorነት እየተሰራ ያለ ነው።ይሁንና ዋና ኮንትራክተሩና ሰብ ኮንትራክተሩ በስራ ምክንያት ሜቴክ የሳሊኒን ስራ እያጓተተ እንቅፋት በመሆኑ፣ በክፍያ እና በሌሎችም አለመግባባታቸው፤ ሜቴክ ጥራት ያለው እቃ ባለማቅረቡ ከጥራት ተቆጣጣሪዎች ጋር ሲወዛገቡ ነው የቆዩት። ይህንን ጉዳይ ደግሞ ኢንጅነር ስመኘው እንዳያወጣው ይልቁንም / ደብረጽዮን እየሸመገለ በውስጥ ማለቅ እንዳለበት ይነገረው ነበር።ዋና ተዋናዮቹም ክንፈ ዳኘውና / ደብረጽዮን ነበሩ።
ከእነዚህ አለመግባባቶች ጋር ተያይዞ የዛሬ ዓመት ሳሊኒ ኮንስትራክሽን የስራ ማቆሚያ ደብዳቤ ፅፎ ነበር።
<<......መንግስት ከሳሊኒ ኮንስትራክሽን ጋር ባለው የክፍያ ስምምነት መሰረት ለግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት የሚውል ወጭ ገንዘብ በብር እና በውጭ ምንዛሪ መክፈል ሲገባው በገንዘብ እጦት ምክንያት እዳውን መክፈል አልቻለም በመሆኑም ሳሊኒ ኮንስትራክሽን በውሉ መሰረት ግንባታውን ማቋረጡን ለመንግስት ይገልፃል>> በሚል በፅሁፍ አሳውቋል።
ሜቴክ ከግድቡ ግንባታ የተወሰኑ የብረታ ብረት እና ኤሌክትሮሜካኒካል ስራዎችን እንዲያስፈፅም ያለምንም ጨረታ ነበር የተሰጠው።በዚህ ሂደት በቢሊዮኖች ሚቆጠር ክፍያ ቢፈፀምለትም የወሰደውን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት አልቻለም። ይህም ለግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት መጓተት ተጨማሪ ኪሳራ እና ወጪ መዳረግ ዋና ምክንያት ሆኗል በማለት ለስራው አፈፃፀም ገንዘብ አለመከፈሉና ሜቴክም ሆን ብሎ እያጓተተበት እንደሆነ ሳሊኒ የዛሬ ዓመት ግድቡን አቋርጠዋለው በሚለው ደብዳቤው ላይ ፅፎት ነበር።
በሌላ ደብዳቤ ደግሞ የዚሁ ቅድመ ተያያዥ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው #ሜቴክ ኮንትራክተር ሆኖ በሚሠራበት የህዳሴ ግድብ (በኢንጅነር ስመኘው ግድብ) ላይ ሜቴክ ከሲቪል ኮንትራክተሩ #ሳሊኒና#ከኮንሰልታንቱ ጋር እንዳልተስማማ እንዲሁም እነሱን ማሳመን ሲያቅተው በእጅ አዙር ባለቤቱን #መብራትሀይልን እነሱን መስማት እንዲያቆም ያስፈራራበት ደብዳቤም ፅፎ ነበር። ከዛም አልፎ መመሪያ ሁሉ የሚሰጥ ደፋር ኮንትራክተር እንደነበር ጥር 4/2008 . የተፃፈው ደብዳቤ ያረጋግጣል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታድያ አደባባይ አይውጣ እንጅ ሜቴክ ያለምንም ጨረታ የወሰዳቸው ግዙፍ የብረታ ብረት ስራ ኮንትራክቶች #በመዘግየት እንዲሁም #በጥራት ጉድለት ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተሉ እንደሆነ፤ሜቴክ የውሀ ማሳለፊያ ቱቦ (bottom outlets) መስመር ስራን ያለምንም ተጫራች ወስዶ ዝቅተኛ ጥራት ያለው ብረት በመጠቀም በመስራቱ የተከላቸው የቱቦ መስመሮች ገና ውሀ ሳይነካቸው ጎብጠው መፈንዳት መጀመራቸውና ይህም ጉዳይ የውዝግብ አካል እንደነበር ከግድቡ መረጃዎች ወጥተው ነበር።
የክንፈ ዳኘው ሜቴክ ሜቴክ፣ ሳሊኒና የኢንጅነር ስመኘው ስራ እርስበርስ የማይግባቡባቸው ብዙ ነገሮች ስለነበሩ / ደብረጽዮን ጣልቃ እየገባ ሸምጋይም፤ ማስጠንቀቂያ ሰጭም እየሆነ ቆይቷል።ሜቴክ በአባይ ግድብ ሰበብ በህገ ወጥ መንገድ የወሰደው ገንዘብ እንዲሁም በስራ ማጓተትና የጥራት ችግር ያለበት ወቀሳ ተዳምሮ ከስኳር ፕሮጀክቱ ዘረፍ ጋር ሂሳብ ተወራርዶ ቀን የሚጠብቁ አመራሮች ያሉበት/የነበሩበት ተቊም ነው።ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ደግሞ ምንም እንኳን እኔ አብዛኛው ስራየን ብጨርስም ሜቴክ የያዘውን መጨረስ ባለመቻሉ ክፍያ እንዳይፈፀምልኝ አድርጎኛል እናም ወደ አለምቀፍ ፍርድ ቤት አቀናለው እያለ መሆኑም ታውቋል።
ይህ ባለበት ሁኔታ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የፖለቲካ ቀውስ ሲገጥመው / አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ እና የእነ ክንፈ ዳኘው የንግድ ድርጅት (ሜቴክ) የሀገሪቱን ሀብት መዝረፉ ሳያንስ ለወደፊትም ስጋት በመሆኑ ግለሰቡን ወዲያኑ ከስልጣኑ አነሳው።የዚህ ትኩሳት እያለ በየመድረኩ በሚናገራቸው ንግግሮች ውስጣቸው ያረረው ተከዜ ማዶዎች መቀሌና ልደታ የማዘዣ ጣቢያ አቋቁመው ሴራዎችን ሲያቀናብሩ ቆዩ።ከቴሌ፣መንብራት ሀይል፣ ደህንነት ተቋም፣መከላከያ፣ፖሊስ ወዘተ ጋር የተቀናጀ በድን በማቋቋም የሰኔ 16ቱን ሙከራ ማድረጋቸው እንደተጠበቀ ሁኖ ሌሎች እስከ መፈንቅለ መንግስት የሚደርሱ እቅዶችንም አስበው ነበር (አስባዋል) ይህንን ጉዳይ / አብይ በደንብ ያውቀዋል።ለነገሩ በየመድረኩም በግልፅ ተናግሮታል።.
በዚህ ገዳይ የቅርብ ትዝታው / አብይ ከምሁራን ጋር አደረገው በተባለው ውይይት ግድቡን አስታኮ የተናገረው ንግግር ከፖለቲካ ኪሳራው ይልቅ የገንዘብ ድልቦችን የቀድሞው የሜቴክ አመራሮችን እና ደብረጽዮንን የሚነካ ነበር።ይህ ግልፅ መልዕክት ነበር።ከዚህ ቀን ጀመሮ ሰሜነኞቹ <</ አብይ ላይ የግብፅ ተላላኪ>> <<ኢንጅነር ስመኘው ችግር ሊገጥመው ነው..>> ወዘተ የሚል ወሬ ማስወራት ጀመሩ።በዚሁ ሂደት ኢንጅነር ስመኘው የግድቡን ጉዳይ በሚዲያ ይፋ እንዲያደርግ ተመቻቸ።እንግዲህ እነዚህ ቀድሞውንም ለራት ተዘጋጅተናል ብለው የሚያስቡት የሜቴክ ሰዎችና የህወሃት የስልጣንም የገንዘብም ደላሎች ደም ፍላታቸውና ጭንቀታቸው አይሎ ያንን ለክፉ ቀን አዘጋጅተውት እየጠቁበት ያለውን የደህንነት ጣምራ ቡድን አንቀሳሱት ማለት ነው።ስለሆነም ኢንጅነር ስመኘው በሚዲያ ቀርቦ የዶ/ አብይን ሀሳብ የሚያጠናክርና ምናልባትም ከገፉበት እነ ክንፈን ለእስር የሚያበቃ መረጃ ከማውጣቱ በፊት ያላቸው ብቸኛ ምርጫ / አብይን ሳይሆን ኢንጅነር ስመኘውን በተገኘው አጋጣሚ መጨረስ ነው።ለዚህ ደግሞ ኢንጅነሩም ተመቻችቶ የቀረበላቸው ይመስላል።ያለ አጃቢ ያለ አሸከርካሪ ራሱ እየነዳ ተገኘ።ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አደባባዩ አካባቢ ያኩ ካሜራዎችም ከጥቅም ውጭ ተደርገዋል።በአ. ሰልፍ በድሮን ጭምር ሲቀረፅና ሲጠበቅ የነበረው አካባቢ ዛሬ የመንገድ ዳር ካሜራ እንኳን የለውም።እናም ለሚሽናቸው የተመቻቸ አጋጣሚ ሆነ።የሆነው ሆኖ በእኔ እምትነ ሰውየው የትም ቦታ ቢሆን የትናንትን እለት እንዳያልፍ ያቀዱ ይመስለኛል።ምክንያቱም ስጋታቸው ከጉዞው በፊት በሚኖረው የሚዲያ ብሪፊንግ መረጃውን ሊያወጣ ይችላል የሚል ነውና በየትኛውም ጊዜና ቦታ አጥፍቶ ከመጥፋት ወደኋላ አይሉም ብየ አምናለው።
ሲጠቃለል ለኢንጅነሩ ግድያ ከእነ ክንፈ ዳኘውና ደብረጽዮን ቡድን ውጭ ሌላን መገመት አዋጭ አይመስለኝም።አንዳንዶች የምንጊዜም ጠላታችን ግብፅን ገምተዋል።መገመታችን ባይከፋም ግብፅ ዛሬ ይህንን ርምጃ የምትወስድበት ልዩ ምክንያት ግን የለም።ስለዚህ ምርመራውም ይሁን መላ ምቱ ወደሜቴክ ቢያተኩር ጥሩ ነው ባይ ነኝ።
ህወሃቶች ግድያውን ከዶ/ አብይና ከግብፅ ጋር ብቻ ለምን ማቆራኘት ፈልጊ? የሚለውም ሌላ ማስረጃ ይመስለኛል።


Ayalew menber

Comments

Popular posts from this blog

How Eritrea's Assab port became a major UAE naval base

አንድ ህዝብ የሶስት ቋንቋ ባለቤትና ፈጣሪ (አገውኛ ፣አማርኛ ፣ግዕዝ) እኖይሱሳ ኮንኬ እኖጂ ሌጌፅንስ!