Posts

Showing posts from January, 2018

///እደግ እደግ ብለን ያሳደግነው ቀጋ ዘንበል ዘንበል አለ እራሴን ሊወጋ ፡፡////

///እደግ እደግ ብለን ያሳደግነው ቀጋ ዘንበል ዘንበል አለ እራሴን ሊወጋ ፡፡//// ስላበላናቸው በሉን ! ከጠላት በደማችን ስለጠበቀናቸው ደመኛቸው አደረጉን ! ስላኮራናቸው አሳፈሩን ! እኛ እኮ ለነሱ ዘመድ ብቻ ሳንሆን ህይወታቸውም ነን ! እነሱ እኮ አሁንም እኛ ከተውናቸው የሉም !   እንዳይራቡ ብለን   ዘመናችንን ሙሉ ነጭ ጤፍ ጭነን ያበላናቸው አልበቃ ብሎ በረሐው ሀሩሩ እንዳያቃጥላቸው ዛፍ ያስፈልጋቸዋልና አፈር ጭነን ለምለም ልናደርጋቸው ሞከርን ! ውኃ እንዳይጠማቸው ብለን ከተከዜ ሲሻገሩ ይሁን አልን ! ይሄ ሁሉ ተረስቶ ቤታችንን እያፈረሱ በየጎዳናው ጣሉን በየጥሻው ቀበሩን ! ይሄንን ግን ልናልፈው አንችልም ! ወንድሜ እኔን እየገደለ እራሱን የማኖር ፍላጎት ካለው ከጠላትም ጠላቴ ነው ፡፡ ከባዳ ጠላት የወንድም ይከብዳል ምክንያቱም የወንድም ጠላት ማንነትህን በደንብ ያውቃልና እንደ ባዕድ አይደለም ስለዚህ አሁን እንደ ድሮው ወንድሜ ነው ብዬ አልልም !   ትግራይ አማራን መበቀል ሳይሆን ማክበር እና መኩሪያ ወንድሜ ነው ማለት ነበረበት !   አሁን ግን አማራ ባጎረሰ በትግራይ ውሾች ተነከሰ! እደግ እደግ ብለን ያሳደግነው ቀጋ ዘንበል ዘንበል አለ እራሴን ሊወጋ ፡፡   እንዳለው ዘፋኙ እኛም እየደገፍን ባጀገንናቸው ውሾች ተነከስን! ይሄን ስል ግን ሚዛናዊ ትግሬ የለም እያልሁ አይደለም ፡፡ አዝናለሁ በሰዶም እና በገሞራ ውስጥም ሎጥ ነበረና መርከብ ሰርቶ ህዝቡን የሚጠብቅ ኖህም ነበረና ፡፡ እንደዚህ ለይቼ እንዳልናገር አምላክ አይደለሁም፡፡ ዜዶ ነኝ

በሬውን አረዱት ከቀንበሩ ፈተው ሞፈሩን ፈለጡት የስጋ መጥበሻ ዝም ብሎ ማየት ነው የዚን መጨረሻ !

በሬውን አረዱት ከቀንበሩ ፈተው ሞፈሩን ፈለጡት የስጋ መጥበሻ ዝም ብሎ ማ የት ነው የዚን መጨረሻ !   እያልን የበደልን ጽዋ አብዝተን ተጎነጨን ! ለም መሬት እያለን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ እትብታችን የተቀበረበትን ቦታ ጥለን ተሰደድን፤ምርቱ   የአማራን ህዝብ አይደለም ኢትዮጵያን የሚያጠግብ ሆኖ ሳለ ተራብን ፤የንነገስታት ዘር ሆነን ሳለ ባርያ አገልጋይ ሊያደረጉን ጣሩ፤ ይሄም ሁሉ ሆኖ ግን አልጠፋንም ይሄም ሁሉ ሆኖ ግን በአባቶቻችን የተገነባ ታላቅ ስነ ልቦና አለን፤ በየትኛውም ዩኒቨርስቲ ባለምጡቅ አዕምሮ ሁነን እያለ እንደ እውቀት ድሀ ቆጠሩን ይህም ሆኖ እያለ ግን በስቃይ እና በድህነትም አልፈን ተምረን በየዩኒቨርስቲዎች የዋጫ ክብር ባለቤት ነን ! እና እንዴት አይነት ድፍረት ነው ይሄን ህዝብ ለማጥፋት መሞከር ፈጽሞ የማይቻል እውነት ! ይሄ ህዝብ ድሮም አሁንም ለወደፊትም በአለት ግርግዳ የተገነባ ጠንካራ ሀውልት ነው የኢትዮጵያ መሰረት ነው ፡፡ ተወደደም ተጠላም አማራ የኢትዮጵያ   የማእዘን ድንጋ ነው፡፡ (ዘላለም በላይነህ)

#አማራ--ይድመቅ--ኢትዮጵያ--ትድቀቅ--ብሎ--የሚያስብ--ስብዕና--የለውምም--አይኖረውምም

#አማራ--ይድመቅ--ኢትዮጵያ--ትድቀቅ--ብሎ--የሚያስብ--ስብዕና--የለውምም--አይኖረውምም ግብረ ገብነት ምግባራቸው የሆኑ ሰዎች በውስጣቸው   ታላቅ እምነት አለ ይህ እምነት ደግሞ ጽናትና ብርታት ሲደመር ማስተዋልና ማገናዘብ ዋና መርሐቸው ሆኖ አዕምሮቸውን ነጻና የህሌና ህግን ለመጣስ ድፍረት የሌላቸው እንዲሆኑ   ያግዛቸዋል ፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ለሀማኖታቸው ተገዥ ናቸው ሀይማኖታቸውንም የሚከተሉት ከቤተሰብ እንዲሁ በመወለድ ስለወረሱት ሳይሆን አንብበው መርምረው አምነውት ተቀብለውት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በአዕምሮአችን ውስጥ የሚመላለሰው ነገር መጥፎ ከሆነና ፍርሀት የሚፈጥርብን ሲሆን እራሳችንን ለመከላከል ስንል በዙ ጥፋቶችንና ብዙ ከእውነታ የራቁ አውሬነት ባህሪያቸው የሆነ ነገሮችን እናደርጋለን ፡፡ አንዲህ አይነት ስህተት ውስጥ ከገባን ደግሞ እራስ ወዳድነታችን እንጅ ሀገር፣ወገን፣ትውልድ ትዝ አይለንም፡፡ እራሳችንን ከምንሰራቸው ፍርሐት ከፈጠራቸው ነገሮች ለመሸፈን ከዘራናቸው መጥፎ ነገሮች እያጨድን እና እየወቃን ትውልድ እንገድልበታለን ፡፡ አሁን አሁን ይሄን ስርአት የሚመሩትና ጅራቶቹ ገና ከደደቢት በረሐ ሲነሱ በማኒፌስቶአቸው እንደገለጹት አንድ ሀይልን አማራን ጠላት አድርገው በመደጋገም በዚህ ብሄር ላይ እጅግ የመረረ ፍርሐት የፈጠራቸው ጥላቻዎች ገዝፈው ይታያሉ፡፡ ትግራይ በተጨነቀች ጊዜ ቀድሞ የሚደርስ አማራ መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ ጭፍን ጥላቻን ፈጥሮ ህዝቡ ትግላቸውን እንዲያጧጡፍ ማድረግን መረጡ፡፡ በወቅቱ በኤርትራ በወያኔና በኢሀፓ ሲደመር በደርግ የተፈጠረው መርመስመስ ጥሩ አጋጣሚ ሆነላቸው፡፡ በወቅቱ ህዋሀት ከሽሬ ማልፍ አልቻለም ነበር   ተደባብሶ እንጅ አሸሸ ገዳሜ ብሎ ያመጣቸው እና ያስቀመጣቸው እንዲህ ለጥፋት የተዘ...

ለአየሁ ልጆች እና ለአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አመራሮች

ለአየሁ ልጆች እና ለአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አመራሮች ውድ የአየሁ እና አካባቢዎ ልጆች   እንደምን አላችሁ እንደሚታወቀው በባለፈው ማህበር ለማቋቋም ወሬው ተዛምቶ ብዙ ልጆችም እጅግ ተደሰትን አሁን ግን ህጋዊ ፈቃድ በማግኜት እና ባለማግኜት በተፈጠረው መጓተት ምክንያት ሁሉም ሰው ቀዝቀዝ ያለ መስሏል ፡፡ ሆኖም ይሄ ማህብር ሲቋቋም ማህበሩን ለማቋቋም የተሰየሙትን ሰዎች ብቻ ያስፈጽሙ ብሎ መጠበቅ ትክክል አይደለምና ሁላችንም ተጽኖ መፍጠርና ወረዳው ማለትም አየሁ ጓጉሳ ወረዳ ፈቃዱን ይሰጠን እና ህጋዊነቱን በሰላም እና ያለምንም መተዛዘብ ይፈቀድልን ዘንድ መግፋት አለብን፡፡ ምክንያቱም በአመራር ቦታ ላይ ቁጭ ያሉ ሰዎች የማህበረሰቡን ችግር እና የወጣቶችን ቅን ስሜት መረዳት እንዳለባቸው ይሰማኛል፡፡ ከዚህ ባሻገር በውስጣቸው ያሌለ እና ያልሆነ ፍራቻ እና ጥርጥር አስበው የሚያጓትቱት ትክክል እንዳልሆነ ልናስረዳ ይገባል ፡፡ አመራር ላይ ቁጭ ያሉት ሰዎችም ቢሆኑ ከዚህ ማህበረሰብ የወጡ በዚህ ችግር ውስጥ ያለፈ አሁንም እያሳለፈ ያለ ቤተሰብ ያላቸው እና የተገኙ በመሆናችው እራሳቸው ከኛ ከጠያቂዎቹ ባሻገር ሊያስፈጽሙልን እንደሚገባ ደጋግምን እንጠይቃለን ጠይቀናልም ፡፡ በተደጋጋሚ በስልክም ሆነ በሌላ መንገድ ስንጠይቃችሁ የምትሰጡን መልስ አጥጋቢ ባለመሆኑ እንደታስቡበት እና እንድታስፈፅሙልን እንጠይቃለን፡፡ ዘላለም በላይነህ የአየሁ ልጅ

****ለአሉላ አባ ነጋ ለዶጋሊው ንጉስ የተጻፈ ደብዳቤ**

Image
****ለአሉላ አባ ነጋ ለዶጋሊው ንጉስ የተጻፈ ደብዳቤ** // በ18 79 አንድ ቁጡ የዛር ፈረስ የመሰለ ኢትዮጵያዊ ጅግና ከትግራይ ተነሳ የጥልያንን ጅቦችም አሳፍሮ ወንድ የወንድ ልጅ አራቸውን አብልቶ ኢትዮጵያዊነት ወኔውና ጀግነት ምን እንደሚመስል አሳያቸው አስተማራቸው ጀግናው አሉላ አባ ነጋ ይህ ጀግና እንዳሁኖቹ የእሳት ልጅ አመድ የወገኑን ደም ለማፍሰስ እና ከርሱን ከወገኖቹ የሚያስበልጥ ሳይሆን እራሱን ለሀገሩ እና ለክብሩ ለወገኑ አሳልፎ የሚሰጥ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዚህ አሉላ በተወለደበት ታሪክ በሰራበት ‹‹ አሉላ አባ ነጋ የወንዶች ወንድ ነው   ያውም ሰማዕት ደምጹ እንደነጎድጓድ አይኑ እንደመብራት ያስፈራ ነበረ ዶጋሊ ሲዘምት ›› የተባለለት ምርጥ ነበር፡፡ ይድረስ ለጀግናችን   ስጋህ ከምድር በታች   ታሪክህ ከምድር በላይ ላለኸው ጀግናው አሉላ አባ ነጋ የውነት በልጆችህ ብንከፋም ብናፍርም ብናዝንም ባንተ ደም ግን እንኮራለን ! ምክንያቱም እንደአሁኖቹ ልጆችህ ባንዳ አይደለህምና ፣እንዳሁኖቹ ሀገርህን አሳልፈህ ለባዕድ የምትሸጥ ሳትሆን እራስህን ለሀገርህ አሳልፈህ የምትሰጥ ጀግና ነህ፡፡ ኣኛም ታሪካችንን ጀግናችንን እናወድስ ዘንድ የተፈጠርን የኢትዮጵያ ልጆች በባንዴራው ስር ለመሞት የተዘጋጀን በደማችሁ ያቆያችኋትን ባንዴራ ልንሞትላት ተዘጋጅተን የጠፈጠርን ነንና ልባችን አይደነግጥም ፡፡ ግን ልጆችህ ይችን ሀገር ሊያጠፉ   የጠላትህን ደም ባፈሰስህበት መሬት ተማምለው የወገኖችህን ደም እንደቫምፓየር ባከበርኸው በታቦቱ ስፍራ   እየመጠጡን ነውና አጥንትህ ይውቀሳቸው ብያለሁ ፡፡   ለማንኛውም ነፍስህን በገነት ጀግንነትህን በልጆችህ ውስጥታሳድር ዘንድ አጠይቅሀ...

ይሰማል ሸዋ! ይሰማል የእምዬ ልጆች! ዜዶ ነኝ ጎጃሜው….

Image
ይሰማል ሸዋ! ይሰማል የእምዬ ልጆች! ዜዶ ነኝ   ጎጃሜ ው…. እያጉረመረመ እያጉረመረመ   ያ ጎጃሜ ልቤ   ሸዋ ላይ ከረመ በሸዋ ልጅ ፍቅር በደብረ ሲናዋ ወደቀና ልቤ   ከዘረ ጀግናዋ የምኒሊክ ወኔን ካባቷ ዋጅቼ የበላይን ቁጣ ከራሴ ቀድቼ በፍቅር ላሰክራት ይችን የሸዋ ልጅ እንከራተታለሁ ተይዤ እጅ ከፈንጅ ‹‹አንተ የበላይ ዘር ጅንኑ ጎጃሜ ደረቴ ላይ እደር ጠቶቼ ላይ ተኛ ልበልህ ደግሜ ›› እያለች በዜማ ወኔና ስሜቴን እንድታሞካሸው ዝናሬን አጥብቄ ሲና ላይ ልክረመው፡፡ (አቦ ሸዋ በጀግንነትም በፍቅርም ነው እንዴ የሚያሸንፈው !) (ዘላለም በላይነህ)

እርጅናን አምኖ የማይቀበል ትውልድ ጊዜ ባገነነው ውሸት እውነትን ለመጨፍለቅ ሲታገል አገር ይገድላል ትውልድ ቀብራል !

እርጅናን አምኖ የማይቀበል ትውልድ   ጊዜ ባገነነው ውሸት እውነትን ለመጨፍለቅ ሲታገል አገር ይገድላል ትውልድ ቀብራል ! እርጅናውን አምኖ የማይቀበል አንበሳ ጅብ ሲያሯሩጥ እራሱ ይበላል ! ለጅቦችም አምበሳነትን አስደፍሮ ለቀጣዩ የአንበሳ ተውልድ ፈተና ጥሎ ያልፋል! ሀገር በአሮጌው መሰረትነት   አዲስ አቋምና ግድግዳ አድርጋ ብትገነባ   ፋኖስ እና ብርጫቆ ማለት ነበሩ፡፡   አሁን ግን ሀገራችን ላይ እርጅና እና ወጣትነት ትግል ውስጥ ስለገቡ ንፋስና ብርጭቆው የተሰበረ ፋኖስ ሆነዋል! አንደኛው ከአንደኛው በባህሪም እንዳይስማሙ የተፈጠሩ መስለዋል (የሰውነት ባህሪ) ሁሉም ነገር ወቅት እና ጊዜ አለው ብረት ከዛገ እና ብል ከበላው በኋላ ምሶሶ ቢሆን ከእንጨት በቀደመ ፍጥነት አፈር ይጎርደውና ለህንጻው መውደቅ ምክንያት ይሆናል ፡፡ ጠንቃራውን እና ለቤቱ ውበት የተሰደሩትን ሌላም ሌላም ነገሮች ከንቱ አድርጎ መሰረት አልባ ያደርግና   የተደረመሰው ህንጻ   የሚል ያጋራ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡   ኢትዮጵያ ሀገራችን   ዘረኝነት እና መነጣጠልን አላማ አድርገው በተነሱ አዛውንቶች ተጠምዳ አባያነት የገነነበት ወጣት እያሳደገች ቁልቁለቷን ቀጥላለች! ይህ ነው የከፍታ ዘመን !!!! የሰው ልጅ እድሜው እየበሰለ እሳትነቱን እያቀዘቀዘ በሄደ ቁጥር ድሮ ድሮ አስተዋይ እና እራስ ወዳድነቱን እየተወ ሀገር እና ትውልድን ያስብ ነበር! አሁን ግን   ሀገራችን በእነ ብቻ እንብላው ተከባ   ትውልድ ማሰብ የሚባለው ታላቅ ሀሳብ በጫት እና በሽሻ ተከልሎ ልክ እንደጥርሳቸው ጭንቅላታቸውም ከበለዘ አመታት አስቆጥሯል!! እንዲህ ነው እንግዲ ትውልድ ማሰብ! የሚፈልጉትን ለማድረግ ሆዳቸውን የሚጋፋ ከመጣ የመብራቱ ...

እርምሽን!!!

Image
አንዳንዴ  የሆነ ! ህልም የመሰለ እውነት ይገጥምህና  እንደመራህ እንጅ እንደመራኸው መጓዝ ታቆማለህ ! ህይወት ግን አጋጣሚዋ ሲገርም ፡፡ ሰዎች ስንባል በቃ በፊታችን ላይ የተደገሰውን ድግስ አልታዬን ብሎ ማማረር የህይወታችን አንድ አካል ነው፡፡  ሁሌም ትልቅ ፀሐይ የመሰለ ብርሐን ፊታችን ላይ ተደቅኖ አይናችን ላይ ያለው ቅርቡ  የወጣትነት መነጸር ይጋርደንና ማስተዋል አንችልም፡፡ ወገቧ እንደ አንዝርት የሾር ኮረዳ ባዬን ቁጥር የአይናችን ማነጣጠሪያ ከልጀቱ አረማመድ ጋር እንጅ ከቀልባችን መሆኑን ይዘነጋል፡፡ ካስፈለገም በዳሌዋ ፈገግታ ገልመጥ አድርጋን ካለፈችም ዜብራ ላይ ቆመን   በባለሀብት ገንዘብ ቀልቧ የጠፋ  እንስት ከቤቷ ግድግዳ የሰቀለችው መስታወት ይመስል  አስር ጊዜ በመኪናዋ መስታወት ፊቷን እየተመለከተች በምታሽከረክረው ቪትስ ፍትፍት ልንሆን እንደርሳለን!(አልዋሸሁም አይደል እያንዳንድሽ) ይሄ ሁሉ ግን መጨረሻውን መገመት ያዳግታል!  በዚህች አቅማዳ በማትሞላ እድሜዬ( እድሜህ እህል ነው እንዴ በአቅማዳ የሚሰፈር እንዳትሉኝ ማገናኜትደስ ስለሚለኝ ነው!)ስንቱን ውጣ ውረድ አየሁት አንዱም ግን የሆነው የለምክንያት አልነበረም፡፡ መጥፎው አስተምሮህ ያልፋል ጥሩው ደግሞ አበርትቶህ አንድ እርምጃ እንድትራመድ ወደፊት ይጎትትሀል፡፡ በዚህ ሁሉ ትግል ግን ውሳኔ ! ከባዱ እና ቆራጥነትን የሚጠይቅ ነው ፡፡ እኔ ደግሞ ለውሳኔ የሚቀድመኝ ሁሉ ያለ አይመስለኝም ፡ በቃ መወሰን ደስ ይለኛል፡፡ ታዲያ ውሳኔዬ ሁሉ ግን አንዳልጸጸትበት ለአፍታም ቢሆን መገናዘብን አልረሳም ፡፡  አንዳዴ ግን ድንገት ውስጥህ ሰው በናፈቀበት ሰአት ! በቃ የእውነ አንተነትህ እንዲሰማህ የሚያደርግህ...

ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?

Image
ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል? ( ዲ/ ን ዳንኤል ክብረት) ... የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል ‹ጸረ መንግሥት ዝማሬ ያሰሙ ነበር›፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹ድንጋይ ይወረውሩ ነበር› የሚሉት ምክንያቶች የጸጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ጥይት እንዲተኩሱ የሚያበቁ ሕጋዊና ሞራላዊ ምክንያቶች አይደሉም፡፡ ማንኛውም ጸጥታን የማስከበር ሥራ መከናወን ያለበት ሰላምን በሚያሰፍን፣ የሰዎችን ሕይወትና ንብረት በሚጠብቅና ተመጣጣኝ የሆነ ኃይልን ለመጠቀም በሚፈቅድ ሁኔታ መሆን አለበት፡፡ በኃይል የሚፈታ ችግር እንደሌለ መንግሥት ራሱ ከማናችንም በላይ የሚያውቀው ነገር ነው፡፡ የዛሬውን መንግሥት የመሠረተው ኢሕአዴግ ወደ በረሓ እንዲገባ ያደረገው ደርግ ችግሮችን ሁሉ በውይይት ሳይሆን በኃይልና በኃይል ብቻ ለመፍታት በመፈለጉ መሆኑን በየግንቦት ሃያ በዓሉ ስንሰማው ኖረናል፡፡ ለሰው የሚጠላውን ኃጢአት ራሱ ከመሥራት በላይ ውድቀት የለም፡፡ በዓሉ የአንድ ቀን በዓል ነው፡፡ ቢታገሡት ያልፍ ነበር፡፡ ሌላ ችግር ይከሰታል ተብሎ ከተጠረጠረና መረጃ ከተሰበሰበ እንኳን አያሌ የችግር መፍቻ አማራጮች ነበሩ፡፡ ‹የጸጥታ ችግርም› ‹የጸጥታ ኃይሎች›ም እኛ ሀገር ብቻ አይደለም ያሉት፡፡ ባለ ሥልጣኖቻችንም ለልምድ ልውውጥ በየሀገሩ ሲሄዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ምነው ታድያ የተሻለ አማራጭ መማር አቃታቸው? በዓሉ ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ ዐቅመ ደካሞች፣ ነፍሰ ጡሮች፣ አካል ጉዳተኞች ሳይቀሩ የሚታደሙበት በዓል ነው፡፡ እንዴት ነው ወደነዚህ ሁሉ የሚተኮሰው? እንዴትስ ነው ‹ችግር ፈጠሩ› የተባሉትን አካላት ከሌሎች ለመለየት የሚቻለው? ጥይቱስ እንዴት ነው ከ9 ዓመት ሕጻን የሚጀምረው?...

ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ

Image
ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ ( ዘላለም በላይነህ ) አንዳንዴ የቴዎድሮስ ካሳሁንን ዘፈን አጋነናችሁት የሚል ሰው እሰማለሁ እኔ እየቆየሁ ዘፈኑን ባደመጥሁት ቁጥር እይታዎቹ ይገርሙኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ዘፈኑ ግጥም መራቀቅ እንጅ ስለርዕሱ አስተውለን የማናውቅ ብዙዎቻችን ነን፡፡ ርእስ ሀይል አለው ርእስ አንባቢን አድማጭን የመሳብ ሀቅሙ ከባድ ነው፡፡ ጸሐፊ ግጥሙን ጽፎ ሲጨርስ ርእስ በማጣት የሚያምጥበት ጊዜ ብዙ ነው ፡፡ ለጸሐፊ ከባዱ ነገር ከጽሁፉ ይልቅ ርእሱ ይመስኛል፡፡ ምክንያም የጣፈውን ጽሑፍ ባንድ ቃል ወይም አርፍተ ነገር ማስፍር ነውና ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር = ማር እስከ ጧፍ እነዚህን አቻ ቃሎች እስኪ በታየኝ ልክ እንያቸው ፡፡ ፍቅርን ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ስንት ፈግታ ታታሪዋ ንብ ከብዙ ነገሮች ውህድ ፈጥራ በምትቀምመው ማር ሲመስለው - ለፍቅር በሚከፈል መስዕዋትነት ውስጥ ያለውን ሂደት ደግሞ ሰፈፉ ቀልጦ ለብዙዎች ብርሀን በመሆን እራሱን አመድ በሚያደርገው ጣፍ መሰለው ፡፡ ለፍቅር በተከፈለ መስዋዕትነት መቃብር መውረድን ደግሞ ጧፍ ሆኖ ለሌሎች ብርሀን መሆንን ማር ከነደደ በኋላ አመድ ምንም የማይጠቅም ያበቃለት ጉዳይ መሆኑን አመሰጠረበት ፡፡ ለዚህም ነው ቴዎድሮስ ካሳሁን ይችላል የሚሉ ድምጽች የበረከቱት፡፡ እሽሸው ገዳዬ በበዛበት ሰአት እንዲህ በግጥም ጥበብ በሰምና ወርቅ የጎለበተ የሙዚቃን እረቂቅነት የሚያሳይ ዛፋኝ ለምን አናድንቅ ! እስኪ አንድ ዘፈን ጥሩልኝ ...