አዲሱ የኦህዴድ ተወካይ ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስተር መመረጣቸው እና የደመቀ መኮነን ከምርጫ እራሳቸውን የማግለል ጉዳይ ፖለቲካዊ አንድምታው፡፡ አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን እራሰቸውን ካገለሉ ማግስት ኢትዮጵያችን ምጥ በሚመስል መልኩ ጠቅላይ ሚኒስተሯን ለመሾም ስትጨነቅ ሰንብታ አሁን እንደምንም ሰው እንቅልፍ በወሰደበት ከሌለቱ አምስት ሰኣት ላይ ይፋ ሆኗል ፡፡ እንደምናውቀው ከውጭም ሆነ አገር ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ኦሮሞ አገር መርቷል የሚባለውን ታሪክ ስም ብቻ የፈለጉ እስኪመስል ድረስ ዶር አብይ………..ይ እያሉ ከወዲያም ከወዲህም ሲያስተጋቡ መክረማቸው ይታወቃል ፡፡ኢሀዴግም ይሄን ፍላጎታቸውን እውን አድርጎላቸዋል፡፡ እንደሚመስለኝ አቶ ደመቀ መኮነን እራሳቸውን የማግለሉ ጉዳይ ለመመረጥ በህገ መንግስቱ ላይ ታላቅ ድጋፍ የ ነበረው ምክትል የነበረው ደመቀ በመሆኑ ይሄንን ህግ ተከትለው ቢመርጡት የኦሮሞ ብሄርተኛች ሊፈጥሩት የሚችሉትን ተቃውሞ ከግምት ውስት በማስገባት ምክትሉ እራሱን እንዲያገል እና የኦሮሞዎችን ልብ እንደማብረጃነት ሊጠቀሙት በማሰብ የተቀነባበረ ይመስላል ምክንያቱም በዚህ የውጥረት ሰአት አቶ ደመቀ ቢመረጥ የኦሮሞ ብሄርተኞች ከእሳት ላይ ገለባ እንደመጨመር ስለሚመስላቸው የአማራው ብሄርተኞች የስርአት ለውጥን እንጅ በኢሀዴግ አጠራር ስር ነቀል ተሀድሶው ብዙም እንደማያስጨንቃቸው በመገንዘብ የግድ ዶክተር አብይ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመጡ ተገደዱ ፡፡ ዋነው ቁምነገር ለአማራውያን ዶክተር አብይ መመሩጡ ወይም ደመቀ መመረጡ ትርጉም ያለው ፍሬ ነገር አይደለም ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም በሚለው ብሂል ! ቁምነገሩ 1፡- ዶክተር አብይ የኦነግን እቅድ ለማሳካት ከነጃዋር ጋር ያለው ግልቢያ የጀርባ አጀንዳ ካደረጉና የ...